Friday, December 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየተጠናቀቀው የፕሮጀክት አሠልጣኞች ሥልጠና

የተጠናቀቀው የፕሮጀክት አሠልጣኞች ሥልጠና

ቀን:

የሴቶች ወጣት ብሔራዊ ቡድን የአሸናፊነት ጉዞ በዑጋንዳ

ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ዕድገት መቀጨጭ በትልቁ ምክንያት ተደርጎ ከሚነገረው መካከል ተመጋጋቢነት ያለው የታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክትና ለፕሮጀክቱ የሚመጥን ዕውቀት ያላቸው አሠልጣኞች ሥልጠና ጉዳይ አንዱ ነው፡፡ ይሁንና ሁሉም ችግሩን በችግርነቱ ከማውራት ባለፈ መፍትሔው ላይ ሲሠራ እምብዛም ሳይታይ በመቆየቱ፣ እግር ኳሱ መራመድ ተስኖት ቆይቷል፡፡

ይሁን እንጂ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በቅርቡ ባደረገው የመፍትሔ እንቅስቃሴ በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች ላቋቋማቸው የታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክት ያዘጋጀው የአሠልጣኞች ሥልጠና  አከናውኗል፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የልህቀት ማዕከል ከጥቅምት 23 እስከ 26 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ በሰጠው ሥልጠና ሠላሳ ሠልጣኞች ተሳትፈዋል፡፡

በመዝጊያ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ ሥልጠናው በኢትዮጵያ እግር ኳስ ለዓመታት ሲነገር የቆየው ምናልባትም በወረቀት ካልሆነ በተግባር ያልተሞከረው የፕሮጀክት ሥልጠና ዕውን የሚሆንበት አጋጣሚ ነው ሲሉ መግለጻቸው ታውቋል፡፡ ሠልጣኞች ቁጭት ብቻ ሳይሆን በሥልጠና ያገኙትን ዕውቀት ከነበራቸው ልምድ ጋር በማቀናጀት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉ ታዳጊዎችን ማፍራት እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል፡፡

በሌላ በኩል በዑጋንዳ አስተናጋጅነት እየተካሔደ በሚገኘው የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ (ሴካፋ)፣ ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት በታች ሴቶች የእግር ኳስ ሻምፒዮና ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ወጣት ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የአሸናፊነት ጉዞውን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ የጂቡቲ፣ የኤርትራና የታንዛኒያ አቻዎቹን በአሸናፊነት እየመራ ይገኛል፡፡ በአሠልጣኝ ፍሬው ኃይለ ገብርኤል የሚሠለጥነው ብሔራዊ ቡድኑ፣ በዑጋንዳ ጅንጃ ከተማ በሚኖረው ቆይታ የመጀመሪያዎቹን አምስት ጨዋታ ማድረግ ሲጠበቅበት፣ እስካሁን ሦስቱን በድል አጠናቋል፡፡ አስቀድመን ለኅትመት በመግባታችን ውጤቱን ማካተት ባንችልም ቡድኑ አራተኛውን ጨዋታ  ጥቅምት 27 ቀን 2014 ዓ.ም. ከብሩንዲ አቻው ጋር  ተጫውቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...