Saturday, July 13, 2024

[የክቡር ሚኒስትሩ የእጅ ስልክ እየጠራ ነው፣ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ደጋግሞ የሚደውል አንድ የአውሮፓ አምባሳደር ስልክ ነበር]

 • ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር፡፡ 
 • እንዴ! ክቡር አምባሳደር አለህ እንዴ?
 • የት እሄዳለሁ ብለው ነው ክቡር ሚኒስትር? አለሁኝ። 
 • መግለጫ አይቼ አልነበረም እንዴ?
 • የምን መግለጫ ክቡር ሚኒስትር?
 • የውጭ ዜጋ የሆኑ የኤምባሲ ሠራተኞቻችሁ ከአገር እንዲወጡ መወሰናችሁን የሚገልጽ መግለጫ አውጥታችሁ አልነበረም እንዴ ሰሞኑን
 • ክቡር ሚኒስትር የዳበረ ዴሞክራሲ ባለቤት መሆን እኮ ችግሩ ይኼ ነው። 
 • እንዴት?
 • መግለጫ ከማውጣት በዘለለ ማስገደድ አንችልማ
 • እና ዜጋ የሆነው ሠራተኛ አሁንም እዚሁ አዲስ አበባ ነው እያልከኝ ነው አምባሳደር?
 • ትክክል፣ እንደዚያ ነው። 
 • ገባኝ አሁን፣ መግለጫ ያወጣችሁት ልትወጡ አልነበረማ?
 • ዓላማችን እንደዚያ ነበርሌላ ምን ሊሆን ይችላል ብለው ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • ይሆናል እንጂ አምባሳደርለምን አይሆንም?
 • ውጡ ነው ያልነውሌላ ምን ሊሆን ይችላል?
 • ግቡ፡፡

 

 • ይቀልዳሉ ልበል ክቡር ሚኒስትር?
 • የሚገርመውስ ያንተው ድርቅና ው?
 • ምን አሉኝ?
 • ዛሬ ምን ገጠመህምን ልታዘዝ?
 • ክቡር ሚኒስትር የኢንተርኔት አገልግሎት ለእኛ መለቀቅ እንዳለበት ልነግርዎ ነው፣ ሥራ መሥራትም ሆነ ከዋናው መሥሪያ ቤት መገናኘት አልቻልንም።
 • እንዳትገናኙ እኮ ነው የተቋረጠው፡፡
 • ለምን? ከማን እንዳንገናኝ?
 • ከዋናው መሥሪያ ቤት!

[ክቡር ሚኒስትሩ ሰሞኑን የተካሄዱድጋፍ ሠልፎችን ካስተባበሩ የፖለቲካ አመራሮች ጋር እየመከሩ ነው]

 • የዛሬውን ውይይት የጠራሁት ለሁለት ዓላማ ነው። 
 • አንድም በአጭር ጊዜ ውስጥ ሕዝቡ በነቂስ እንዲወጣ በማድረግ የውጭ ጠላቶቻችን መሬት ላይ ያለውን እውነታ እንዲረዱት በማድረጋችሁ ለማመሥገንና በዚህ የተገኘውን ውጤት እንዴት ማጎልበት እንዳለብን ለመተለም ነው።
 • ክቡር ሚኒስትር በአጭር ጊዜ ዝግጅት ይህንን ሁሉ ሕዝብ በነቂስ እንዲወጣና መንግሥትን እንዲደግፍ ማድረግ ቀላል አይደለም፣ ከዚህ አኳያ ሲገመገም ይህንን ያስተባበርን የፖለቲካ አመራሮች በመናበብ ድንቅ ተግባር መፈጸማችን ዕውቅና ቢሰጠው ተገቢ እንጂ መመፃደቅ ሊባል አይችልም።
 • ክቡር ሚኒስትር ከተፈቀደልኝ የተለየ ሐሳብ አለኝ፡፡ 
 • ጥሩ ቀጥል።

 

 • ክቡር ሚኒስትር እንደተባለው ሕዝቡ በነቂስ እንዲወጣ በአጭር ጊዜ ማስተባበር መቻላችን ጥሩ ቢሆንም፣ የተለየ ሙገሳና መደናነቅ ውስጥ መግባት አለብን ብዬ አላምንም።
 • ለምን? 
 • ምክንያቱም ሕዝቡ በዚህ መጠን በነቂስ ሊወጣ የቻለው የፖለቲካ አመራሩ በፈጸመው የማስተባበር ተግባር ስለመሆኑ እርግጠኛ መሆን አይቻልም። 
 • ለምን እንደዚያ አልክ?
 • ምክንያቱም ሕዝቡ እኛ ሠልፎቹን ከማስተባበራችን በፊት ቀድሞ ሠላማዊ ሠልፍ ላይ ነበር።
 • ምን እያልክ ነው? ሕዝቡ የት ነው ሠልፍ የወጣው?
 • ክቡር ሚኒስትር ሕዝቡ ሁሉንም የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመጠቀም የውጭ ጣልቃ ገብነትን ከእኛ ቀድሞ ሲያወግዝ ነበር፣ የዓረብኛ ቋንቋን ጭምር በመጠቀም የውጭ ጫናን እየተቃወመ ነበር። 
 • እህ….
 • ክቡር ሚኒስትር እኛ ቦታውን ቀየርነው እንጂ ሕዝቡ ወጥቶ ነበር፣ ይህን ስል ግን ብንዘገይም ሠልፉን ማስተባበር መቻላችን ቦታ የለውም ማለቴ አይደለም። 
 • ልክ ነው ክቡር ሚኒስትር እኔም በግሌ የምስማማበት ሐሳብ ነው፣ ነገር ግን ሠልፉን ማስተባበር በመቻላችን ደግሞ ተበታትኖ የነበረውን ተቃውሞ ወደ አንድ አደባባይ በማምጣት እውነታውን እንዲረዱት አድርጓል። 
 • ከማብራሪያችሁ የተረዳሁት ሕዝቡ ከአመራሩ ቀድሞ እየሄደ መሆኑን ነው። 
 • ክቡር ሚኒስትር ትክክል ነው፣ ነገሩ መገምገም ያለበት እንደዚያ ነው፣ በተጨማሪም በእነዚህ ሠልፎች ላይ የነበሩ ክፍተቶችንም መመልከት ያለብን ይመስለኛል።
 • እኔም በሁለተኛ ደረጃ አነሳዋለሁ ያልኩት በሠልፉ ላይ የነበሩ ክፍተቶችን መመልከት ነበር፣ ምን ዓይነት ችግሮች ነበሩ?
 • ክቡር ሚኒስትር እርስዎም ሰምተውታል ብዬ እገምታለሁ፣ ከተደረጉት ሠልፎች በዋና ከተማ በነበረው ሠልፍ ሕዝቡ ከገመትነው በላይ የራሱን መልዕክት ይዞ በመውጣት አስደንቆናል፣ ነገር ግን በእኛ በኩል በነበረ የተናጋሪዎች መረጣ ከፍተኛ ችግር መፍጠር የሚችል ስህተት ተሠርቷል።
 • ምንድነው የሆነው?
 • ክቡር ሚኒስትር በዚህ መድረክ ከተሳተፉ የኪነ ጥበብ ሰዎች መካከል ያልተጠበቀ መልዕክት በመተላለፉ ቁጣ ቀስቅሷል። 
 • የተላለፈው መልዕክት ምን ነበር?
 • ወጣቶች ወደ ጦር ግንባር አትሄዱ የሚልና ከሠልፉ ዓላማ ያፈነገጠ ድንገተኛ መልዕክት ነበር። 
 • መልዕክቱን ያስተላለፈው የኪነ ጥበብ ባለሙያ ሌላ ተልዕኮ ነበረው ብላችሁ ታምናላችሁ? ቀድማችሁ ስለግለሰቡ የጀርባ ታሪክና ኔትወርክ ለምን ጥናት አላደረጋችሁም?
 • ክቡር ሚኒስትር ግለሰቡ እንኳ እንደዚያ ዓይነት ሰው አይደለም፣ የታወቀው ስለሰላም በመዘመር በመሆኑ በዚህ ሠልፍ የተጠራውም ለዚሁ ዓላማ መስሎት ሊሆን ይችላል፣ በነገራችን ላይ እርስዎ ጭምር ያበረታቱት አዲስ የኪነ ጥበብ ባለሙያ ነው። 
 • ማነው?
 • አድናቂዎቹ ዲሽታ ጊና ብለው ነው የሚጠሩት፣ ስህተቱ ከተፈጠረ በኋላም መፀፀቱን እንደገለጸ ሰምቼያለሁ።
 • ክቡር ሚኒስትር ስህተቱ ቢፈጠርም፣ በስህተት የተላለፈው መልዕክት በሕዝብ ላይ የፈጠረው ቁጣ ደግሞ ያልታሰበ ጠቃሚ ዕድል በመሆኑ በጉዳዩ ላይ ብዙ መጨነቅ ያለብን አይመሰለኝም። 
 • ምን ማለትህ ነው? ያልከው መልካም አጋጣሚ ባይከሰትስ ኖሮ እንዴት መጨነቅ አይገባንም ትላለህ?
 • ክቡር ሚኒስትር የተለየ ሐሳብ አለኝ፡፡
 • እሺ ቀጥል።
 • አሁን የተናገሩት ባልደረባ እንደዚህ ዓይነት ስህተት ትልቅ ቀውስ ውስጥ ሊያስገባ እንደሚችል በሚገባ የተረዱት አልመሰለኝም፣ ስለዚህ ትኩረት ሰጥትን መነጋገርና ተጠያቂነትን ማስፈን ካልቻልን ተመሳሳይ ችግር ውስጥ አለመግባታችንን እርግጠኛ መሆን አንችልም። 
 • አሁን በቀረበው ሐሳብ እስማማለሁ ክቡር ሚኒስትር፡፡ 
 • ስለዚህ ምን ይደረግ ነው የምትሉት?
 • መጠየቅ አለበት?
 • ማን ነው የሚጠየቀው? 
 • የውስጣችን ዲሽታ ጊና! 

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የሰብዓዊ መብት ጉዳይና የመንግሥት አቋም

ሰኔ ወር አጋማሽ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ከፍተኛ የሰብዓዊ...

ከሰሜኑ ጦርነት አገግሞ በሁለት እግሩ ለመቆምና ወደ ባንክነት ለመሸጋገር የተለመው ደደቢት ማክሮ ፋይናንስ

በኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ በቀዳሚነት ስማቸው ከሚጠቀሱት ውስጥ ደደቢት...

የታመቀ ስሜት!

የዛሬ ጉዞ ከመርካቶ በዮሐንስ ወደ አዲሱ ገበያ ነው፡፡ ታክሲ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ በችግኝ ተከላ ፕሮግራም ላይ ሳይገኝ ከቀረው አንድ የተቋማቸው ባልደረባ የሆነ የተቃዋሚ ፓርቲ አባልን አስጠርተው እያናገሩ ነው]

ለምንድነው በዚህ አገራዊ ፋይዳ ባለው ፕሮግራም ላይ ያልተገኘኸው? ክቡር ሚኒስትር ህሊናዬ አልፈቀደልኝም። መቃወምና መተቸት ብቻ ውጤት የሚያመጣ መስልዎህ ከሆነ ተሳስተሃል። አልተሳሳትኩም ክቡር ሚኒስትር? ቆይ የመጀመሪያ ዓመት የችግኝ ተከላ...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላነጋግርህ የፈለኩት ክቡር ሚኒስትር፡፡ እርስዎማ ቀጠሮ መያዝ አያስፈልግዎትም፣ ምን ገጠመዎት? እኔማ ምን ይገጥመኛል አንተኑ ልጠይቅህ እንጂ? ምን? እውነት ለመናገር የማየው ነገር አሳስቦኛል፡፡ ይንገሩኝ...

[ክቡር ሚኒስትሩ በቢሯቸው ሆነው ከአማካሪያቸው ጋር ስለወቅታዊ ጉዳዮች እየተነጋገሩ ነው]

ትናንት የሆነውን ሰሙ ክቡር ሚኒስትር? አልሰማሁም፣ ምን ሆነ?  ኬንያውያን የአገሪቱን ፓርላማ ጥሰው መግባታቸውን አልሰሙም? ኧረ አልሰማሁም።  የፓርላማውን በር ጥሰው ገብተው አንደኛውን ክፍል በእሳት አያያዙት፡፡  ምንድነው ምክንያቱ?  የአገሪቱ መንግሥት ያቀረበው አዲስ...