Sunday, September 25, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዓለምኢኮዋስ በማሊና ጊኒ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ጣለ

  ኢኮዋስ በማሊና ጊኒ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ጣለ

  ቀን:

  የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማኅበረሰብ (ኢኮዋስ) አባል አገሮች መሪዎች በማሊ እና በጊኒ ላይ አዲስ አካባቢያዊ ማዕቀብ መጣላቸውን አስታውቀዋል፡፡

  የኢኮዋስ አባል አገር በሆነችው ማሊ፣ በዘጠኝ ወራት ጊዜ ውስጥ ሁለት ጊዜ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት መደረጉንና በሌላዋ አባል አገር ጊኒ መፈንቅለ መንግሥት መካሄዱን ከጅምሩ ያወገዘው ኢኮዋስ፣ አገሮቹ ላይ ማዕቀብ የጣለው መፈንቅለ መንግሥቶቹ እንደተከናወኑ ከወራት በፊት ነው፡፡ የኢኮኖሚና የጉዞ ማዕቀብ ሲጥል ያስቀመጠው ቅድመ ሁኔታ ደግሞ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መደረግ አለበት የሚለውን ነበር፡፡

  ሆኖም ይህ በተፈለገው መጠን ባለመከናወኑ የኢኮዋስ አባል አገሮች መሪዎች ባሳለፍነው እሑድ ባካሄዱት ስብሰባ፣ ከዚህ ቀደም በአገሮቹ ላይ የጣሉትን ማዕቀብ ያጠናከሩ ሲሆን፣ አዳዲስ ማዕቀቦችንም ጥለዋል፡፡

  በማሊና በጊኒ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከተካሄደ በኋላ አገሮቹ በወታደራዊ መንግሥት እየተመሩ መሆኑን ያስታወሱት መሪዎቹ፣ ሁለቱም አገሮች ወደ ዴሞክራሲያዊ የሥልጣን ሽግግር ይመጡ ዘንድ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ እንዲያሳወቁም ጥሪ አቅርበው ነበር፡፡

  ኢኮዋስ በማሊና ጊኒ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ጣለ

   

  15 አባል አገሮች የታቀፉበት ኢኮዋስ፣ ከዚህ ቀደም በአገሮቹ ላይ ማዕቀብ ሲጥል፣ ማሊ እ.ኤ.አ. በጥር 2022 ምርጫ እንድታካሂድ ጥሪ አቅርቦ ነበር፡፡ ነገር ግን መጓተት በመታየቱ ማዕቀቡን ለማጠናከር ወስኗል፡፡

  በጋና ዋና ከተማ አክራ ከነበረው ጉባዔ በኋላ የኢኮዋስ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ጆን ክላውድ ካሲ የሰጡትን መግለጫ ጠቅሶ የኬንያው ኔሽን እንደ ዘገበው አገሮቹ በታቀደው መሠረት ምርጫ ለማካሄድ የሚችሉበትን ሁኔታ አላመቻቹም፡፡

  በሁለቱም አገሮች የሚገኙ መፈንቅለ መንግሥት አድራጊዎችና ቤተሰቦችን ጨምሮ የጉዞና ገንዘብ እንዳያንቀሳቅሱ ገደብ መጣሉንም አስታውቀዋል፡፡

  በማሊ ምርጫን ለማካሄድ የሚያስፈልገው ዝግጅት መጓተቱን፣ በዚህም ምክንያት ከነበረው ማዕቀብ በተጨማሪ በግለሰቦች ላይ ማዕቀብ መጣሉንም ገልጸዋል፡፡

  በጊኒ ከሁለት ወራት በፊት ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት መካሄዱን ተከትሎ፣ ኢኮዋስ አገሪቱን ከቡድኑ፣ ግለሰቦችንና ቤተሰቦቻቸውን ደግሞ የጉዞና የገንዘብ ዝውውራቸው ላይ ገደብ መጣሉ ይታወሳል፡፡

  ከዚህ በተጨማሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የጊኒ ፕሬዚዳንት የነበሩት የ83 ዓመቱ አልፋ ኮንዴ ከቤት ውስጥ እስራት እንዲፈቱ ጠይቋል፡፡

  የመፈንቅለ መንግሥት አድራጊዎች 13 ሚሊዮን ሕዝብ በሚኖርባት ጊኒ ምርጫ እንዲያካሂዱና ለዚህም የጊዜ ሰሌዳ እንዲያሳውቁ በኢኮዋስ ተጠይቀው የነበረ ቢሆንም ፕሬዚዳንት ኮንዴን ያስወገደው በኮሎኔል ማማዴ ዶምቦያ የተመራው ቡድን፣ ግልጽ አድርጎ ባላስቀመጠው የሽግግር ጊዜ አገሪቷን ወደ ሲቪል መንግሥት እንደሚመራ ቃል ገብቶ ነበር፡፡ ሆኖም ቃሉን በመፈጸም ላይ እመርታ ባለመታየቱ ማዕቀቡን ለማጠናከር ተገደናል ሲል ኢኮዋስ አስታውቋል፡፡

  የማሊና የጊኒ መፈንቅለ መንግሥት አድራጊዎች በተሰጣቸው ጊዜ ምርጫ ካላከናወኑም በቀጣይ ወር በሚኖረው የኢኮዋስ ጉባዔ ሌሎች ማዕቀቦች የሚጣሉ ስለመሆኑም ተናግሯል፡፡

  በጊኒ የብሔራዊ የዕርቅና የልማት ኮሚቴ ሁሉም አባላት ላይ ማዕቀቡ የፀና ሲሆን፣ በማሊ የሽግግር ሒደቱን ባጓተቱ የተለያዩ ግለሰቦች ላይ ደግሞ የኢኮኖሚ፣ የጉዞና ገንዘብ የማንቀሳቀስ ገደብ ተጥሏል፡፡

  የጊኒ ወታደራዊ መሪዎች ፕሬዚዳንታዊና የሕግ አውጭዎች ምርጫ እንዲያካሂዱና ሥልጣን በስድስት ወራት እንዲያስረክቡ በኢኮዋስ ማሳሰቢያ ከመሰጠቱ በተጨማሪ፣ የብሔራዊ ኮሚቴ አባላት ለፕሬዚዳንትነት እንዳይወዳደሩ ገደብ ጥሏል፡፡

  ወታደራዊ ክፍሉ በመጀመርያ እ.ኤ.አ. በነሐሴ በ2020 በኋላም በግንቦት 2021 ሥልጣን በተቆጣጠረባት ማሊ፣ ምርጫ ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው በጥር 2022 ቢሆንም፣ የሽግግር መንግሥቱ ይህን የጊዜ ሰሌዳ አያሳካም ሲሉ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንትና የኢኮዋስ ልዩ መልዕክተኛ ጉድላክ ጆናታን ተናግረዋል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በኢትዮጵያ ላይ የቀጠለው የምዕራባውያን ጣልቃ ገብነት

  ምዕራባውያን አገሮች በኢትዮጵያ ላይ ጠንካራ ጫና ማሳደራቸውን ቀጥለዋል፡፡ በዲፕሎማሲም...

  የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የድጎማ በጀት ለፖለቲካ ሥራ ማስፈጸሚያ እንደሚውል የሚያሳይ ሪፖርት ቀረበ

  ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚደረግ የበጀት ድጎማ ከመደበኛው ሥራ ይልቅ ከዋናው...

  መንግሥት የሥራ ግብር ምጣኔን እንዲቀንስ ተጠየቀ

  የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) መንግሥት የሠራተኛውን የኑሮ ጫና...

  የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የአመራሮች ምርጫና ቀጣይ ዕቅዶቹ

  የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ሲጠበቅ የነበረውን...