Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናሕወሓት  የኮምቦልቻ  ከተማ መሠረተ ልማቶችን መዝረፉና ማውደሙ ተገለጸ

ሕወሓት  የኮምቦልቻ  ከተማ መሠረተ ልማቶችን መዝረፉና ማውደሙ ተገለጸ

ቀን:

ከሁለት ሳምንት በፊት በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ውስጥ በሚገኙ ከተሞች ሰርጎ የገባው የሕወሓት ኃይል፣ በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኙ መሠረተ ልማቶችን መዝረፉንና ከዝርፊያ የተረፉትን ደግሞ እንዳወደመ የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዲ ሁሴን ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ምንም እንኳ መጠኑን በግልጽ ለማስቀመጥ የማይቻል ቢሆንም፣ በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኙ የግልና የመንግሥት ድርጅቶች ስለመዘረፋቸው መረጃው ደርሷቸዋል፡፡

ከተዘረፈው የሕዝብና የመንግሥት ሀብት በተጨማሪ ታጣቂዎቹ ወደ ከተማው ሲገቡ፣ ሕዝብ የሚጠቀምባቸውን መሠረተ ልማቶችች እንደ ትምህርት ቤትና የጤና ተቋማት መዝረፋቸውንና ማውደማቸውን ገልጸዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የሕወሓት ታጣቂዎች ከአንድ ወር በፊት ከአዋሽ-ኮምቦልቻ-ወልዲያ ሃራ ገበያ በ1.7 ቢሊዮን ዶላር በሚገነባው የምድር ባቡር ፕሮጀክት 268 ዶዘሮች፣ ኤክስካቬተሮች፣ የጭነት መኪኖችና ሌሎች ማሸነሪዎችን መዝረፋቸውንና በርካታ ሀብት ማውደማቸው መገለጹ ይታወሳል፡፡ 

በደቡብ ወሎ ዞን ከተሞች እየተካሄደ ባለው የህልውና ዘመቻ አስተዋጽኦ አድርገዋል የተባሉ ምሁራንን፣ ባለሀብቶችን፣ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮችንና ደጋፊዎችን ወይም ይደግፋሉ ብሎ የጠረጠሯቸውን በሙሉ እየለዩና እየመረጡ ማሰራቸውን፣ ከዚያም አልፎ በአደባባይ እንደ ረሸናቸው አቶ አብዲ አስታውቀዋል፡፡

ከሁለት ሳምንት በፊት የሕወሓት ታጣቂዎች ወደ ደሴና ኮምቦልቻ ከተሞች በገቡበት ወቅት፣ ከ100 በላይ የኮምቦልቻ ወጣቶችን አሠልፈው እንደጨፈጨፉ መንግሥት ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡

አብዛኞቹ የምሥራቅና የደቡብ ወሎ ወረዳዎች በሕወሓት ታጣቂዎች በቁጥጥር ሥር እንደሚገኙ የገለጹት ዋና አስተዳዳሪው፣ በቅርብ ጊዜ በነበረው ውጊያ የጦርነት ሕግ በሚፈቅደው መሠረት እየተዋጉ እንደነበርና አሁን እየተካሄደ ያለው ውጊያ ግን ከሠለጠነ ተዋጊ ጋር ሳይሆን ከሕዝብ ጋር በመሆኑ፣ የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ራሱን እንዲጠብቅ ጥሪ እየቀረበለት ነው ብለዋል፡፡

በተደረገው ጥሪ መሠረት ምንም እንኳ ወጣቱ የሕወሓትን ወረራ ለማስቆም ያለው ተነሳሽነት ከፍተኛ ቢሆንም፣ ወደ አገር መከላከያ ወይም በክልል ልዩ ኃይል  ውስጥ ገብቶ ለመሳተፍ የሚታየው እንቅስቃሴ እምብዛም እንዳልሆነ በመጥቀስ ወጣቱ፣ ዕድሜው የደረሰና ጤናው የሚፈቅድለት ሁሉ ተገቢውን ሥልጠናና ትጥቅ አሟልቶ እንዲዋጋ ጥሪ አድርገዋል፡፡

በተጨማሪም ባለሀብቶች ለአገር መከላከያና ለልዩ ኃይል የጀመሩትን የሀብት ማሰባሰብ ሥራ እንዲቀጥሉ፣ ምሁራን ጦርነቱ ለምን እንደተጀመረና ለምን እየተካሄደ እንደሆነ ለሕዝቡ ትክክለኛ መረጃ በመስጠት እንደ አገር መግባባት እንዲፈጠር እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

በሌላ በበኩል ሪፖርተር ያነጋገራቸው የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተስፋው ባታብል፣ በዞኑ በየአካባቢው ጦርነት እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የሕወሓት ታጣቂዎች ከዞኑ ዘርፈው የወሰዱትን ሀብት ለማጣራት፣ እንዲሁም አጠቃላይ የሕዝቡ የኑሮ ሁኔታ ምን እንደሚመስል ለማወቅ አልተቻለም ብለዋል፡፡

በጦርነቱ ምክንያት ከቀዬአቸው ተፈናቅለው ከነበሩ ዜጎች የተወሰኑት እየተመለሱ እንደሆ፣ ተፈናቅለው ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ለሠፈሩትም ሆነ በቁጥጥር ሥር በዋሉ ቦታዎች የሰብዓዊ ዕርዳታ እየቀረበ አለመሆኑን ዋና አስተዳዳሪው አክለው ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...