Saturday, December 3, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰማ

  የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰማ

  ቀን:

  • ሌሎች የክልሉ ባለሥልጣናት በእስር ላይ መሆናቸው ተነግሯል

  የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ኮማንደር ኤዶሳ ጎሹን ጨምሮ፣ የግልገል በለስ ከተማ ከንቲባ አቶ ሀብታሙ ባልዳና የመተከል ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምርያ ኃላፊ አቶ ገበየሁ ጀጎዴ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰማ፡፡

  የባለሥልጣናቱን እስር ለሪፖርተር ያረጋገጡት የክልሉ ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ምሥጋናው ኢንጅፋታ፣ የልዩ ኃይል አዛዡ ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ.ም. በክልሉ በሚገኘው ካማሺ ዞን በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ አስረድተዋል፡፡ የግልገል በለስ ከተማ ከንቲባና የመተከል ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምርያ ኃላፊ ደግሞ መተከል ዞን ውስጥ በተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ውሳኔ እንደታሰሩ ገልጸዋል፡፡

  ምክትል ኮሚሽነሩ ‹‹ያልተጣሩ መረጃዎች አሉ›› በማለት ባለሥልጣናቱ በምን ምክንያት በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ በዝርዝር ከመናገር ተቆጥበው፣ ያሉትን መረጃዎች እየገመገሙ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

  አሁን በቁጥጥር ሥር የዋሉት ኮማንደር ኤዶሳ ጎሹ ከመስከረም 2012 ዓ.ም. ጀምሮ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ልዩ ኃይልን በአዛዥነት ሲመሩ ነበር፡፡

  በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሥር የሚገኙት መተከልና ካማሺ ዞኖች፣ በተለይ ከ2011 ዓ.ም. ጀምሮ በተደጋጋሚ ጥቃትና ግድያ ሲፈጸምባቸው ቆይቷል፡፡

  የመተከል ዞን በኮማንድ ፖስት ሥር የሚተዳደር ሲሆን፣ በዞኑ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ አማራ፣ ጋምቤላ፣ ደቡብና ሲዳማ ክልሎች ልዩ ኃይሎች ተሰማርተዋል፡፡ የመከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የአካባቢው ሚሊሻዎችም የዞኑ የፀጥታ ኃይል አካል ናቸው፡፡

  የክልሉ አስተዳደር ንፁኃን ላይ ጥቃት፣ ግድያና ዕገታ እያደረሱ ያሉት የጉሙዝ ታጣቂዎች መሆናቸውን የሚገልጽ ሲሆን፣ ታጣቂዎቹ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት በተፈረጀው ሕወሓት ድጋፍ ይደረግላቸዋል የሚል ክስ ያቀርባል፡፡

  ከቀናት በፊትም የመከላከያ ሠራዊትና የተለያዩ የፀጥታ አካላት ባካሄዱት ኦፕሬሽን፣ ለግልና ለቡድን ለጥቃት የሚያገለግሉ መሣሪያዎች በክልሉ በሚገኘው ሸርቆሌ ወረዳ በቁጥጥርር እንደዋሉ መገለጹ አይዘነጋም፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...