Saturday, December 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሰበብ የትራፊክ ሕግን የሚጥሱ አካላት ላይ ዕርምጃ ይወሰዳል ተባለ

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሰበብ የትራፊክ ሕግን የሚጥሱ አካላት ላይ ዕርምጃ ይወሰዳል ተባለ

ቀን:

በአገር አቀፍ ደረጃ የታወጀውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሰበብ በማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ ሕግን የሚጥሱ አካላት ላይ ዕርምጃ ይወሰዳል ተባለ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ አረጋዊ ማሩ ለሪፖርተር እንደነገሩት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መነሻ አድርጎና በሰበብ አስባቡ የትራፊክ ሕጉን የሚጥሱ አካላት ላይ አስተማሪ ዕርምጃዎች መወሰድ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ የትራንስፖርት ቢሮ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ባለፈው ሳምንት፣ እንዲሁም በተያዘው ሳምንት የመጀመሪያ ቀናት ውይይቶች ተደርገዋል፡፡

ከአገሪቱና የከተማዋ ነባራዊ የፀጥታ ሁኔታ ጋር ተያይዞ በከተማዋ ውስጥ ያለውን የትራንስፖርት ሁኔታ እንዴት ተደራሽ ማድረግ እንደሚቻል፣ ተገልጋዮች በተለያዩ ተርሚናሎች በሚያደርጓቸው ረዣዥም ሠልፎችና በሚኖሩበት አካባቢ የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር ሊደረጉ በሚገባቸው ቅድመ ዝግጅቶች ላይ ሰፊ ውይይቶች እንደተደረጉ ተገልጿል፡፡ በውይይቱ ላይም ከአጎራባች ኦሮሚያ ክልል የመጡ የፀጥታ አካላትና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት መሳተፋቸው ታውቋል፡፡

 ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም ጋር ተያይዞ ማኅበረሰቡ በጊዜ ወደ ቤቱ መግባት ስለሚፈልግ፣ የተሽርካሪዎች እጥረት እንዳያጋጥም ምን መሠራት አለበት? የሚለውን ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶች እንደተደረጉ የገለጹት አቶ አረጋዊ፣ በተለይም በከተማዋ ውስጥ ከትርፍ በላይ የሚጭኑ፣ ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ፣ አቆራርጠው የሚጭኑና በአጠቃላይ የትራንስፖርት ደንብ የሚተላለፉ አካላት ላይ አስተማሪ ዕርምጃ የመውሰዱ ሒደት ተጠናክሮ የሚቀጥል እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

በተለይም ከኮድ-1- እና ኮድ-3- ተሽከርካሪዎች ጋር ተያይዞ በስፋት የሚታየው ጥሰት የሕግ ጥሰት እንደሆነ ያስታወቁት የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ፣ ይህም በምሽትና እንደ እሑድ ባሉ ቀናት ተጨማሪ ክፍያዎችን ማስከፈልና እንዲሁም ከታፔላ ውጪ መሥራትን ይመለከታል ብለዋል፡፡

የትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጥባቸው አካባቢዎች የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር ከሚመለከታቸው አካላት በጋራ ተቀናጅቶ በሚሠራባቸው ጉዳዮች ላይ በተደረጉ ውይይቶች፣ ከስምምነት ላይ እንደተደረሰም አቶ አረጋዊ ገልጸዋል፡፡

አንዱ ከተሽከርካሪዎች ጋር ተያይዞ የፀጥታ ችግር ከሚፈጠርባቸው መንገዶች የባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ተጠቃሽ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም በየሠፈሩ ውስጥ የሚገቡ ተሽከርካዎች ምክንያት በሥጋት ምንጭነት የሚጠቀሱበት አጋጣሚም እንዳለ ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም ከዋናው መስመር ወጥተው በሚሠሩትና ከተፈቀደላቸው መስመር ወጥተው በሚንቀሳቀሱት ላይ ትራፊክ ፖሊሶችና የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ፣ እንዲሁም በትራንስፖርት ቢሮ ሥር የተደራጁ የቅርንጫፍ ባለሙያዎችም ይህንን ቁጥጥር እንዲያከናውኑ አቅጣጫ መሰጠቱን አቶ አረጋዊ አስረድተዋል፡፡

የባለ ሦስት እግር ተሸከርካሪዎች ወይም በተለምዶ ባጃጅ ተብለው የሚጠሩት ተሽከርካሪዎች በዋናነት የአገልግሎት ፈቃድ የተሰጣቸው በአጎራባች ክልሎች እንደሆነ ጠቅሰው፣ ከከተማ ውጭ በተለይም የጋራ መኖሪያ ቤቶች በተገነቡባቸው አካባቢዎች ከዋናው መስመር ውጭ በመንገድ ውስጥ ለውስጥ እንዲሠሩ በአማራጭነት የቀረቡ አገልግሎቶች እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በተለይም የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ አገልግሎቱን ብቻ እንዲቆጣጠር ተብለው ወደ ሥራ የገቡ የትራንስፖርት አማራጮች እንደሆኑ ተገልጿል፡፡

ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪዎች ወደ አዲስ አበባ ገብተው እንዴት የትራንስፖርት አገልግሎቱን ይሰጣሉ የሚለው ጉዳይ ከአሠራር አኳያ ከተወሰነ ጊዜ ተጀምሮ በይደር የቆየ ጉዳይ እንደሆነ ያስታወቁት አቶ አረጋዊ፣ ከተፈቀደላቸው መስመሮች ውጭ ወደ ዋናው መስመር ገብተው በሚሠሩት ላይ ግን ዕርምጃዎች እንደሚወሰዱ አስታውቀዋል፡፡ በተጨማሪም በቀጣይ መመርያ ተዘጋጅቶ ወደ አንድ አሠራር እስኪመጣ ድረስ የቁጥጥር ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ ያለው የሕዝብ ብዛት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑን የተናገሩት አቶ አረጋዊ፣ ‹‹ይህንን ሕዝብ ውስን በሆነ የትራንስፖርት አቅም ማስተናገድ በጥሩ ጎኑ የሚጠቀስ ነው፡፡ የትራፊክ ፍሰትን ተመልክቶ በተሠራው ሥራ በተለይም አንፃራዊ በሆነ መንገድ በተለይም የከተማዋ ነዋሪዎች ወደ ሥራ የሚገቡበትን ጊዜን መቀነስ ተችሏል፤›› ብለዋል፡፡ ነገር ግን አሁንም ቢሆን ክትትልና ቁጥጥሩን የበለጠ ሊሠራበት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...