Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየአፍሪካ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜና የሊዲያ ታፈሰ ብቃት

የአፍሪካ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜና የሊዲያ ታፈሰ ብቃት

ቀን:

በጋናው ሐሳስካስ ሌዲስና በደቡብ አፍሪካው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ መካከል ዓርብ ኅዳር 10 ቀን 2014 ዓ.ም. የተደረገውን የአፍሪካ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ በዋና ዳኝነት ያጫወተችው ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ፣ በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ብቃቷ ተመስክሯል፡፡ እንስቷ የግብፅ ዋና ከተማ በሆነችው ካይሮ ለዚህ ዕድል መብቃቷ እንዳስደሰታት ተናግራለች፡፡

ለሁለት ሳምንት በግብፅ አስተናጋጅነት ሲካሔድ የቆየው የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ ከትናንት በስቲያ ፍጻሜውን አግኝቷል (ቀድመን ለኅትመት በመግባታችን ውጤቱን መያዝ አልቻልንም)፡፡ የዓለም ዋንጫን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን በዋና ዳኝነት በመምራት የብቃት ጣሪያ ላይ የደረሰችው ሊዲያ ታፈሰ፣ ይህን የፍጻሜ ጨዋታ እንድታጫውት በካፍ የእግር ኳስ ዳኞች ኮሚቴ የተመረጠችው በሙሉ ድምፅ መሆኑ፣ ይህም ካፍ በኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ ዳኞች ላይ ምን ያህል እምነት እያሳደረ መምጣቱን የሚያሳይ ስለመሆኑ ጭምር የዘርፉ ሙያተኞች ይናገራሉ፡፡

ሊዲያ ውድድሩንና የግብፅ ቆይታዋን አስመልከቶ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሰጠችው አስተያየት፣ ከኳታር በቀጥታ ወደ ግብፅ ካይሮ እስከበረረችበት ጊዜ ድረስ ቆይታዋ እጅግ አድካሚ እንደነበር፣ እንዲያም ሆኖ ግብፅ እንደገባች በቫር የታገዘ ሥልጠና በክፍል ውስጥ መስጠት መቻሏን ጭምር ተናግራለች፡፡

የሻምፒዮንስ ሊጉ ጨዋታ ከተጀመረ በኋላ ደግሞ በሞሮኮና በናይጀሪያ ክለቦች መካከል የተደረገውን ጠንካራ ፉክክር እንዳጫወተች የተናገረችው ሊዲያ፣ ጨዋታ የመምራት ብቃቷን አስመልክቶ የካፍ ዳኞች ኮሚቴ ‹‹ጠንካራ ዳኛ አለችን›› በሚል ሙሉ ነጥብ የሰጣት ስለመሆኑ ጭምር አስረድታለች፡፡ ሌሎች ጨዋታዎችን በዋናና ረዳት ዳኝነት እንዳጫወተች የተናገረችው ሊዲያ፣ ለተጨማሪ ስኬቶች ጠንክራ እንደምትሠራ ገልጻለች፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...

ግለሰብ ነጋዴዎችን በአስገዳጅነት የንግድ ምክር ቤት አባል ለማድረግ ያለመው ረቂቅ አዋጅ ተከለሰ

በምትኩ የንግድ ተቋማት በአስገዳጅነት የንግድ ምክር ቤት አባል ይሆናሉ...

አሳርና ተስፋ!

ከቱሉ ዲምቱ ወደ ቦሌ ጉዞ ልንጀምር ነው፡፡ ገና ከመንጋቱ...