Monday, March 4, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ከሕዝብ የደረሰኝ የመብት ጥሰት አቤቱታ የለም አለ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ከሕዝብ የደረሰኝ የመብት ጥሰት አቤቱታ የለም አለ

ቀን:

ከተቋቋመ ሁለት ሳምንታት የሞላው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ፣ በአዋጁ አፈጸጸም ወቅት በደል ደረሰብኝ ብሎ የቀረበ የኅብረተሰብ ክፍል እንደሌለ አስታወቀ፡፡

የአስችኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5/2014 አፈጻጸም የሚከታተለውና የሚቆጣጠረው ሰባት አባላት ያሉት መርማሪ ቦርድ፣ ሐሙስ ኅዳር 9 ቀን 2014 ዓ.ም. ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የመርማሪ ቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ለማ ተሰማ ቦርዱ ከተመሠረተ ጀምሮ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ ከብሔራዊ አደጋ መከላከል ኮሚሽንና ከሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አመራሮች ጋር የቅርብ ክትትልና ምክክር ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቀዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ይሁን እንጂ አዋጁ በፓርላማ ከፀደቀ በኋላ በአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ አካባቢዎች በሚደረገው የሕግ ማስከበር ዘመቻ፣ ከሕወሓት ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል በቁጥጥር ሥር ከሚውሉ ዜጎች መካካል፣ አልፎ አልፎ ከሕግ ውጪ እየታሰሩ መሆናቸውን ስለሚነሳው ቅሬታ ቦርዱ ከግለሰቦች ምንም አቤቱታ እንዳልደረሰው አስረድተዋል፡፡

መርማሪ ቦርዱ ከዓርብ ኅዳር 10 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በሚያደርገው የመጀመርያ የመስክ ጉብኝት ወደ ተለያዩ አካባቢዎች በመሄድ፣ ከቤትና ንብረታቸው ተፈናቅለው በመጠለያ የሚኖሩ ዜጎችን፣ በጦርነቱ በደረሰባቸው ጉዳት የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው የሚገኙ ዜጎችን የክትትል ሁኔታ፣ እንዲሁም በአዋጁ አፈጻጸም ምከንያት በሕግ ቁጥጥር ሥር የዋሉ ዜጎችን ለማየት በአፋርና በአማራ ክልሎች እንደሚንቀሳቀስ ተናግረዋል፡፡

 በጉብኝታቸው ወቅትም በተጠቀሱት አካባቢዎች መስተካከል የሚገባቸው ጉዳዮች ካሉ ዕርምጃ እንዲወሰድ አስተያየት መስጠት፣ ከተለያዩ አካላት ለዜጎች እየተደረጉ ያሉ ድጋፎችን ማየት፣ እንዲሁም በጉብኝቱ ወቅት የሚታዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ካሉ እንዲቆሙና በመብት ጥሰት የሚጠረጠሩ አካለት ካሉም ለፍርድ የሚቀርቡበት ሁኔታ ማመቻቸትና በቀጣይ መሰል ክስተቶች እንዳይከሰቱ የማሳሰብና ሁኔታዎችን የማመቻት ሥራ ይከናወናል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከአራት ቀናት በፊት የመብት ጥሰቶችን አስመልክቶ ለቦርዱ ይፋዊ ደብዳቤ ማቅረቡን የገለጹት አቶ ለማ፣ ተፈጸመ የተባለውን የመብት ጥሰትና ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በቁጥጥር ሥር የዋሉ ግለሰቦችን አያያዝ በተመለከተ የእስር ሁኔታ ለመከታተል የሚያስችል መረጃ ለመሰብሰብ በአዋጅ የተሰጠውን ኃላፊነት ለመወጣት አለመቻሉ እንዳሳሰበው የገለጸውን ጉዳይ፣  በመስክ ምልከታ ወቅት የሚታይ ይሆናል ብለዋል፡፡

ቦርዱ በመስክ በሚያደርገው ምልከታ ጉዳዩን አጣርቶ ኮሚሽኑ ተከልክሎ ከሆነ ትክክል ባለመሆኑ መጎብኘት እንዳለበት፣ ለሚመለከተው የፍትሕ አካል በማስረዳት ማሳሰቢያ ይሰጣል ሲሉም አስረድተዋል፡፡

በተመሳሳይ የፍትሕ አካላት ዜጎችን ማንነትን መሠረት አድርገው በቁጥጥር ሥር እያዋሉ ነው ስለተባለው ጉዳይ፣ ‹‹እንዲህ ዓይነት አስነዋሪ ተግባር ተፈጽሞ ከሆነ በምንም ዓይነት ሁኔታ የሚታለፍ አይደለም፣ በሕገ መንግሥቱ መሠረት ለፍርድ የሚቀርቡበትን ሁኔታ እናመቻቻለን፤›› ብለዋል፡፡

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም ወቅት ሊደርሱ የሚችሉ ችግሮችን ማንኛውም ግለሰብ በቦርዱ የጥቆማ መስመሮችና ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመምጣት ቅሬታቸውን ማቅረብ እንደሚችል የገለጹት ሰብሳቢው፣ ጥቆማን መሠረት አድርጎ ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን ማጣራት እንደሚደረግና ሕጋዊ ዕርምጃ እንደሚወሰድ ገልጸዋል፡፡

የሰብዓዊ መብት ጥሰትን በተመለከተ መንግሥት ከሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በመነጋገር አብሮ የሚሠራ መሆኑን አክለው ገልጸዋል፡፡ ‹‹ይሁን እንጂ በፓርላማና በሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን መካከል መብቶች ጉዳይ ልዩነት ይፈጠራል ብለን አናምንም፤›› ያሉት አቶ ለማ፣ ነገር ገን ሁለቱ አካላት በሚለያዩበት ጉዳይ ተለያይተው በሚመሳሰሉበት ደግሞ ተነጋግረው ይሠራሉ ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...