Sunday, March 3, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኢሰመኮ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በኋላ የታሰሩ ዜጎች አያያዝና የጤና ሁኔታ አሳስቦኛል አለ

ኢሰመኮ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በኋላ የታሰሩ ዜጎች አያያዝና የጤና ሁኔታ አሳስቦኛል አለ

ቀን:

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀበት ጥቅምት 23 ቀን 2014 .. ጀምሮ፣ ከአዋጁ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር የዋሉ ሰዎችን አያያዝ፣ የእስርና የታሳሪዎችን ሁኔታ ለመከታተልሚያስችለው መረጃ ማሰባበሰብ አለመቻሉን ጠቁሞ፣ ለመጎብኘት በቻለባቸው መቆያ ቦታዎች የጤና አገልግሎት የሚያገኙበት ሥርዓት አለመዘርጋቱንምንም ዓይነት የኮሮና ወረርሽኝ መከላከያ ጥንቃቄዎች አለመደረጉ እንዳሳሰበው አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ኅዳር 8 ቀን 2014 .. ባወጣው መግለጫ እንደገለጸው፣ በተለይ በፌዴራል ደረጃ በአዲስ አበባና በድሬዳዋ ከተማ የክትትል ቡድኖች በማሰማራት ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ በቂርቆስና በየካ ክፍላተ ከተሞች የሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎችንና ማቆያዎችን ጎብኝቷል፡፡ ታሳሪዎችንና ቤተሰቦቻቸውን አነጋግሯል፡፡ በክፍለ ከተማና በወረዳ ደረጃ ካሉ ከፖሊስ አባላትና አመራሮች ጋር ውይይት በማድረግ መረጃዎችን ማሰባሰቡንና የሚቀርቡለትን ጥቆማዎችና አቤቱታዎች መሠረት በማድረግ መረጃዎችን እንዳጠናቀረ ገልጿል፡፡

የታሰሩ ሰዎችን ብዛት በሚመለከት የተሟላ መረጃ ለማግኘት አለመቻሉን የገለጸው ኮሚሽኑ፣ በአንፃራዊነት የተሟላ መረጃ ያገኘው ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ብቻ መሆኑንና በወቅቱ (ኅዳር 2 ቀን 2014 .ም.) በክፍለ ከተማው ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ 714 ሰዎች መታሰራቸውን፣ ከእነዚህም ውስጥ 124 ሴቶች እንደነበሩ ለማወቅ መቻሉን ጠቁሟል፡፡ በሌሎቹም ክፍላተ ከተሞች በተመሳሳይ ሁኔታ ተጠርጣሪዎች እየታሰሩ በመሆኑ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ይታሰራሉ የሚል ግምት እንዳለውም አክሏል። በደረሰው መረጃ መሠረት በድሬዳዋ ከተማም እስከ 300 የሚደርሱ ሰዎች መታሰራቸውን አስረድቷል፡፡ የተወሰኑ ሰዎች በሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት መረጃ መሠረት የሚታሰሩ ቢሆንም፣ አብዛኞቹ ግን ከኅብረተሰቡ ተገኘ በተባለ ጥቆማ መሠረት በቁጥጥር እንደሚውሉና ከመካከላቸው የትግራይ ተወላጆች የሆኑ ሰዎች ብዛት ከፍተኛ መሆኑን ኮሚሽን ካገኘው መረጃ ማወቁን አስታውቋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የአዲስ ከተማ፣ የልደታ፣ የጉለሌ፣ የቦሌና የአራዳ ክፍለ ከተማ ኃላፊዎች ከበላይ ትዕዛዝ ካልመጣላቸው እንደማይሰጡና እስረኛም ማስጎብኘት እንደማይችሉ ገልጸው ምላሽ በመስጠታቸው፣ ኮሚሽኑ በአዋጅ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት እንዳይወጣ ምክንያት መሆናቸውንም ገልጿል፡፡ ባደረገው ክትትል ለማረጋገጥ እንደቻለው ሰዎችን በቁጥጥር በማዋል ረገድ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መተግበር ባለበት መንገድ  የሰብዓዊ መብት መርሆዎችን ባከበረ መልኩ አለመተግበሩን አስረድቷል።

ኮሚሽኑ ብሔር ተኮር እስር ስለመከናወኑ የሕግ አስከባሪ አካላትን ጠይቆ ያገኘው ምላሽ፣ ‹‹ሰዎች የሚያዙት በብሔራቸው ምክንያት ሳይሆን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሠረት ተጠርጥረው እንደሆነና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጁት ሁለቱም ድርጅቶች ብሔር ተኮር ድርጅቶች ከመሆናቸው አኳያ የሚያዙ ሰዎች የአንድ ብሔር ሊመስሉ ይችላሉ›› መሆኑን አስታውቋል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከሽብር ቡድኖች ጋር ይተባበራሉ ተብለው ምክንያታዊ በሆነ መንገድ የተጠረጠሩ ሰዎችን ይዞ የማቆየት ሥልጣን ለሕግ አስከባሪ አካላት መሰጠቱንና የተባሉት ቡድኖች ብሔር ተኮር ድርጅቶች መሆናቸውን ኢሰመኮ እንደሚገነዘብ ጠቁሞ፣ በጥቆማ ላይ የተመሠረቱ እስሮችን በተመለከተ የጥቆማዎቹ መነሻ የሰዎቹ የብሔር ማንነት አለመሆኑን ለማረጋገጥ፣ ምክንያታዊ ጥርጣሬ ስለመኖሩ ለማጣራት በቂ ጥረት እየተደረገ አለመሆኑን አክሏል፡፡

በተለያዩ አካባቢዎች ዕድሜያቸው 60 ዓመት በላይና የ80 ዓመት የሆኑ ወንዶችና ሴቶች አረጋውያንን ጨምሮ፣ በማጥባት ላይ የሚገኙ ሴቶች፣ በታሳሪዎች ቤተሰቦችና በሌሎች ታሳሪዎች የአዕምሮ ሕመም እንዳለባቸው አልያም ተከታታይ ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ስለመሆናቸው የሚነገርላቸው ሰዎችም በቁጥጥር መዋላቸውን የኮሚሽኑ የክትትል ቡድኖች መመልከታቸውን በመግለጫው አካቷል፡፡ 

በአብዛኛው በቁጥጥር ሥር የሚውሉ ሰዎች በመጀመሪያ በአቅራቢያ ወደሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች የሚወሰዱ ሲሆን፣ ብዛታቸው እየጨመረ ሲመጣ በየክፍለ ከተማው በሚገኙ ሁለገብ ወጣት ማዕከላትና አንዳንድ የትምህርት ማሠልጠኛዎች ተወስደው እንዲቆዩ እንደሚደረግ ኮሚሽኑ ማወቁን አስረድቷል፡፡ ከአዲስ አበባ በተለምዶ ‹‹አባ ሳሙኤል›› ተብሎ በሚጠራው ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግበት ማረሚያ ቤት የተወሰዱ ሰዎችም እንዳሉ ለማረጋገጥ መቻሉንና ቤተሰቦቻቸው የት እንደታሰሩ ገና ለማወቅ ያልቻሉ ሰዎች አቤቱታም እንደደረሰው ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡ 

አንዳንዶቹ የማቆያ ጣቢያዎችና ሥፍራዎች በጣም የተጣበቡ፣ በቂ መፀዳጃ የሌላቸውና በቂ አየርና ብርኃን የማያገኙ መሆናቸውን፣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አረጋውያንና የአዕምሮመምተኛ መሆናቸው የተገለጸ ሰዎችን ጨምሮ 241 ሰዎች ስፋቱ 20 ሜትር አሥር ሜትር በሚገመት አንድ የወጣቶች ሁለገብ አዳራሽ ተይዘው በግቢው ያለውን ብቸኛ መፀዳጃ ቤት ለመጋራት መገደዳቸውን በምሳሌነት ጠቅሷል፡፡ በአንዳንድ ጣቢያዎች ሴቶችና ወንዶች በአንድ ክፍል ውስጥ ተቀላቅለው መታሰራቸውንና በክፍሉ ውስጥ የአዕምሮ መረበሽ የሚታይባቸው ሰዎችም እንደሚገኙ መመልከቱን ኮሚሽኑ አብራርቷል፡፡

የአብዛኛዎቹ ታሳሪዎችም ቅሬታ፣ የተያዙት በብሔራቸው ምክንያት እንደሆነ እንደሚያምኑና የተጠረጠሩበትና የተያዙበትን ምክንያትም እንዳልተነገራቸው  ለኮሚሽኑ አስረድቶ፣ ነገር ግን ታሳሪዎች በማቆያፍራዎች በጥበቃ ላይ በተሰማሩት የፖሊስ አባላትም ሆነ በተያዙበት ወቅት ምንም ዓይነት ድብደባ ወይም አካላዊ ጥቃት እንዳልደረሰባቸው ኮሚሽኑ ያነጋገራቸው ታሳሪዎች እንደገለጹለት አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ ጉብኝት ባደረገባቸው የተወሰኑ ቦታዎች የሚሠሩት የፖሊስ አባላትም በተቻላቸው አቅም ታሳሪዎችንና ቤተሰቦቻቸውን በአግባቡ ለማስተናገድ ጥረት እያደረጉ ቢሆንም፣ የታሳሪዎቹ ብዛት የእስር ሁኔታውን በአግባቡ ለማስተዳደር እንዳስቸገራቸው  መመልከት መቻሉንም አክሏል፡፡

በአንዳንድ ክፍላተ ከተሞች አረጋውያንንና ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ከእስር መለቀቃቸው አበረታች መሆኑን ጠቁሞ፣ ከእስር የመፍታትና የማጣራትደቱ ወጥ አለመሆኑን፣ በአንዳንድ ክፍላተ ከተሞች በዕድሜያቸውበሕክምና ምክንያት የተለቀቁ ሰዎች ‹‹የተለቀቃችሁት ከኮማንድ ፖስቱውቅና ውጪ ነው›› በሚል ተመልሰው መታሰራቸውን ኮሚሽኑ ማረጋገጡን አውስቷል፡፡

በጥቆማ ብቻ የተያዙ ሰዎችን ጉዳይ በመመልከት አዋጁ በሚጠይቀው መሠረት ምክንያታዊ ጥርጣሬ መኖሩን የሚያረጋገጥ፣ መረጃ ያልተገኘባቸውንበቁጥጥር የዋሉ አረጋውያን፣ የሚያጠቡ እናቶችና የጤና ችግር ያለባቸውን ሰዎች በአፋጣኝ ከእስር እንዲለቀቁ፣ ማንኛውም እስር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መንፈስ በመረዳት በተመጣጣኝነት፣ በጥብቅ አስፈላጊነታቸውና ከመድልዎ ነፃ በሆነ መንገድ እንዲከናወን፣ ለዚህም የሚመለከታቸው አካላት ጥብቅ ክትትል እንዲያደርጉ፣ በተለይም የሚያዙ ሰዎች ሁሉ የታሰሩት በምክንያታዊ ጥርጣሬ መሠረት ብቻ መሆኑን የሕግ አስከባሪ አካላት እንዲያረጋግጡ ኮሚሽኑ ምክረ ሐሳብ መስጠቱን በመግለጫው አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...