Wednesday, December 6, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት አራት ወራት 123 ቢሊዮን ብር ግብር መሰብሰቡን አስታወቀ

ተዛማጅ ፅሁፎች

በአገሪቱ የተቀሰቀሰው ጦርነት በፈጠረው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት የላቀ ነው የተባለ 123 ቢሊዮን ብር ባለፉት አራት ወራት ተሰበሰበ፡፡ ግብር ከፋዮች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ኃላፊነታቸውን ሳያጓድሉ በመወጣታቸው ገቢዎች ሚኒስቴር አመሠግኗል። 

ገቢዎች ሚኒስቴር በአራት ወራት 123.96 ቢሊዮን ብር የሰበሰበ ሲሆን፣ ይህም 2013 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አፈጻጸፈሙ 16.3 ቢሊዮን ብር ወይም 15.2 በመቶ የላቀ ነው ተብሏል። 

ሚኒስቴሩ ከሐምሌ 2013 ዓ.ም. እስከ ጥቅምት 2014 ዓ.ም. ባሉት አራት ወራት ውስጥ 133.38 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ የነበረ ሲሆን፣ የተሰበሰበው 123.96 ቢሊዮን ብር ከዕቅዱ አኳያ ሲመዘን 92.9 በመቶው መሳካቱን ያሳያል። 

ይህ ስኬታማ አፈጻጸም ሊመዘገብ የቻለው ግብር ከፋዮች በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ሰበቦችን ሳያቀርቡ ኃላፊነት በመወጣቸውና የግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤቱራተኞች ከምንጊዜውም በላይ በቁርጠኝነትና ያለረፍት በመሥራታቸው እንደሆነ ሚኒስቴሩ አመልክቷል።

በአገሪቱ ውስጥ በተፈጠረው ጦርነትና የተለያዩ ግጭቶች ምክንያት አራት ግብር ሰብሳቢ ቅርንጫፎች ምንም ሳይሠሩሌሎች ቅርንጫፎችም በተገደበ እንቅስቃሴ ውስጥ ሆነው የተሰበሰበ ገቢ እንደሆነ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

‹‹በአገሪቱ በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት ገቢን ለመሰብሰብ በማያመች ሁኔታ ውስጥ የተሰበሰበ ገቢ በመሆኑ አፈጻጸሙ የተሻለ ሊባል የሚችል ነው፡፡ በተጨማሪም አፈጻጸሙ በዚህ ወቅት ግብር ከፋዮቻችን ብዙ ሰበቦችን ሳያቀርቡ ለአገራቸውና ለሕዝባቸው በማሰብ በወቅቱና በትክክለኛው ጊዜ ግብራቸውን አሳውቀው በመክፈላቸው እንዲሁም የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮችናራተኞችም ከምንጊዜውም በላይ የዕረፍት ጊዜያቸውን ጨምረው በመጠቀምና የገቢ ምንጮችን በዝርዝር በማየት፣ እንዲሁም በቁርጠኝነትና በትጋት ከልብ መሥራት በመቻላቸው የተገኘ ውጤት ነው፤›› ብሏል፡፡ 

በተጠቀሱት አራት ወራት ውስጥ ከተሰበሰበው 123.96 ቢሊዮን ብር ውስጥ 80.8 ቢሊዮን ብሩ የተገኘው ከአገር ውስጥ ታክስ ሲሆንከውጭ ንግድ ታክስና ቀረጥ ደግሞ 43.1 ቢሊዮን ብር መሆኑን የገቢዎች ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

በቀጣይም የተሻለ በመሥራት አገሪቱ ይህንን አስቸጋሪ ወቅት እንድትሻገር የበለጠ ርብርብ እንዲደረግ የገቢዎች ሚኒስቴር ጥሪውን አስተላልፏል።

‹‹ኢትዮጵያውያን ለአገራቸው ሕይወታቸውን ለመስጠት በወሰኑበት በዚህ ጊዜ፣ ግብር ከፋዩ ማኅበረሰብ ለሚወዳትገሩ ተገቢውን ግብር በተገቢው ጊዜ በመክፈል ግዴታውን እንዲወጣ እያስታወቅን፣ ግብር ከፋዩ ማኅበረሰብ ግብር እንዳይከፍል መቀስቀስና ማሸበር ፈጽሞ ክልክል ነው፤›› ሲል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምርያ ዕዝ ጥቅምት 26 ቀን 2014 ዓ.ም. ባሳለፈው የመጀመሪያ ውሳኔው ማሳሰቢያ መስጠቱ ይታወሳል።

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች