Tuesday, April 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየቀጠለው የመቅደላ ስብስብ ቅርሶችን የማስመለስ ተግባር

የቀጠለው የመቅደላ ስብስብ ቅርሶችን የማስመለስ ተግባር

ቀን:

የታሪካዊ፣ የቁሳዊና መንፈሳዊ ቅርሶች መድበሏ ኢትዮጵያ በተለያዩ ዐረፍተ ዘመናት  በተለያዩ አጋጣሚዎች ያጣቻቸው ቅርሶቿ አያሌ ናቸው። አንደኛው መጥፎ  አጋጣሚ 1860 ዓ.ም. በመቅደላ አምባ ከሚገኝ ቤተ መዘክር በእንግሊዝ ወታደሮች የተዘረፉበት ይጠቀሳል።

መቅደላ ላይ በተሰዉት ዳግማዊ ቴዎድሮስ ከተለያዩ አካባቢዎች ባሰባሰቧቸው ቅርሶች ያደራጁት ቤተመዘክር ዋነኛው የዝርፊያው ሰለባ ነበር።

በመቅደላ ጦርነት በጄነራል ናፒየር ወታደሮች ተዘርፈው 250 በላይ በሆኑ ዝሆኖች ተጭነው የተወሰዱት በብዙ መቶዎች ከሚቆጠሩ ታሪካዊ ቅርሶችና ታቦታቱን ጨምሮ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ንዋየ ቅድሳት በተለያዩ የእንግሊዝ ሙዚየሞችና አብያተ መጻሕፍት፣ እንዲሁም በግለሰቦች እጅ ይገኛሉ፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

እነዚህን የተዘረፉ ቅርሶች ወደ እናት ምድራቸው ለማስመለስ ጥረት ማድረግ የተጀመረው በአፄ ዮሐንስ ፬ኛ ንጉሠ ጽዮን፣ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ዘመን ነው፡፡ አፄ ዮሐንስ ከአፄ ተክለ ጊዮርጊስ ቀጥለው በነገሡበት በ1864 ዓ.ም. በነሐሴ ወር፣ ለእንግሊዝ ንግሥት ቪክቶሪያ በጻፉት ደብዳቤ ‹‹ከመቅደላ የተዘረፉ ቅርሶቻችንና ንዋየ ቅድሳት ይመለሱልን›› ብለው ጠይቀዋል፡፡

 ንጉሠ ነገሥቱ በተለይ የእግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስን ኲርዓተ ርዕሱን (የሾህ አክሊል) የሚያሳየው ሥዕልና የክብረ ነገሥት መጽሐፍ እንዲመለስላቸው መማጸናቸው፣ ይሁን እንጂ በ1865 ዓ.ም. የተመለሰላቸውና የተረከቡት ክብረ ነገሥት ብቻ መሆኑ በታሪክ ተመዝግቧል።

በአፄ ዮሐንስ የተጀመረው ቅርሶችን የማስመለስ ጥያቄ ከመጨረሻው ንጉሠ ነገሥት አፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት እስከ አብዮታዊው መንግሥት፣  ከኢሕዲሪ  እስከ ኢፌዴሪ መንግሥታት ድረስ በተደረጉ ጥረቶች የተመለሱት ቅርሶች ቁጥር ቀላል አይደለም።

ዓምና እና ዘንድሮ ከተመለሱት ቅርሶች መካከል አብዛኞቹ ከሙዚየሞች ሳይሆን በግለሰቦች እጅ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ የመጡት ለጨረታ ለሽያጭ በቀረቡበት አጋጣሚ እንዳይሸጡ በተደረገ ከፍተኛ ጥረት የመጡ ናቸው፡፡

የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ሰሞኑን እንዳስታወቀው፣ በመቅደላ ጦርነት ጊዜ ተዘርፈው በእንግሊዝ በአንድ ወታደር ቤተሰብ ይዞታ ሥርና በቤልጂየም የቅርስ ሻጮች እጅ የነበሩ አሥራ ሦስት ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ቅርሶችን ከ154 ዓመታት በኋላ ተረክቧል፡፡

የቀጠለው የመቅደላ ስብስብ ቅርሶችን የማስመለስ ተግባር

የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተረከባቸው የመቅደላ ቅርሶች እንዴት ተመለሱ?

በዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ዘመን 1860 .. ከመቅደላ አምባ በእንግሊዝ ወታደሮች ተዘርፈው ከነበሩት ተንቀሳቃሽ ቅርሶች መካከል አሥራ ሦስቱን በለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲተረከበው ጳጉሜን 3 ቀን 2013 .. ነበር፡፡

ኤምባሲው በወቅቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው፣ የተረከባቸው ቅርሶች የብራና መጽሐፍ ከነማህደሩ፣ ልዩ ልዩ  መስቀሎች፣ በነሐስ የተለበጠ የንጉሠ ነገሥቱ የጦር ጋሻ፣ ጽዋ፣ የጳጳስ አክሊል፣ የቀንድ ዋንጫዎች ከወራት በፊት ለሽያጭ ቀርበው የነበሩ ናቸው፡፡

ቅርሶቹን ለኤምባሲው ያስረከበው ደግሞ ሻይራዛድ ፋውንዴሽን ቅርሶቹን በእንግሊዝ ከሚገኝ አንድ የጨረታ ድርጅትና ከነጋዴዎችመግዛቱ ነው፡፡ ይህ እንዲፈጸምም ብሔራዊ የቅርስ አስመላሽ ኮሚቴና በለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲሼሄራዛድ ፋውንዴሽን ከተባለ ተቋም ጋር በመተባበር ያደረጉት ጥረት ይጠቀሳል፡፡

እነዚህና ሌሎች ስምንት ቅርሶች ኤምባሲው ባለፈው ጳጉሜን የተረከባቸው ሲሆን፣ ከሦስት ወር ግድም በኋላ በእንግሊዝ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ተፈሪ መለስ አዲስ አበባ በመገኘት ኅዳር 11 ቀን ለቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን አስረክበዋል፡፡

የቅርሶቹን ርክክብ ተከትሎ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የቱሪዝም  ሚኒስትር ናሲሴ ጫሊ በሰጡት አስተያየት፡- ‹‹በሕገ ወጥ መንገድ ከአገር የወጡ ቅርሶችን ከማስመለስ ጎን ለጎን ስለቅርስ ምንነትና ፋይዳው ለሕዝቡ በቂ ግንዛቤ መፍጠር ይገባል፤›› ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...