Tuesday, February 27, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ400 በላይ ሠራተኞቹን ማገዱ ተገለጸ

ተዛማጅ ፅሁፎች

የባንኩ ቦርድ የመጨረሻ ውሳኔ ለማሳለፍ ቀጠሮ መያዙ ተጠቁሟል

የታገዱት ሠራተኞች የኅዳር ወር ደመወዝ ታግዷል ተብሏል

33 ሚሊየን በላይ ደንበኞች ያሉት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 66 ቅርንጫፎች የሚሠሩ 422 ሠራተኞቹን በደንብ ጥሰት ጠርጥሮ ማገዱ ተገለጸ፡፡

ግዱ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ ለሠራተኞቹ ያልተገለጸ ሲሆን፣ ተግባራዊ የሆነው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ይህን ያህል ቁጥር ላቸ ራተኞች መታገድ፣ በባንኩም ሆነ በዘርፉ የተለመደ እንዳልሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ የሠራተኞቹ የኅዳር ወር ደመወዝም መታገዱ ታውቋል፡፡

ሠራተኞቹ የታገዱት ባንኩ ላልፈቀደው ሌተር ኦፍ ክሬዲት የመርከብ ጭነት ክፍያ ለደንበኞች በመፈ በመጠርጠራቸው መሆኑ ተጠቁሟል።

አንዳንድ ራተኞች ደግሞ ያስፖራ አካውንት ለከፈቱ ደንበኞች፣ ከተገልጋዮቹ የውጭ ምንዛሪ ሒሳብ በመቀነስ፣ የመርከብ አገልግሎት  ክፍያዎችን መፈጸም ቢኖርባቸውም፣ በተቃራኒው በብር አስገብተው ባንኩ በዶላር እንዲከፍል በማድረግ በመጠርጠራቸው እንደሆነ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የባንኩ ኃላፊዎች ለሪፖርተር ገልጸዋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሰኔ 17 ቀን 2002 .ም. ያወጣውን መመርያ በመጥቀስ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማናቸውም በኢትዮጵያ ንግድ መርከብ ተጭነው ለሚገቡ የገቢ ዕቃዎች የሚከፈል የጭነት ክፍያ፣ በውጭ ምንዛሪ እንዲሆን በተመሳሳይ ወቅት ለሠራተኞቹ ትዕዛዝ አስተላልፎ ነበር።

ሠራተኞችም የውጭ ምንዛሪውን ተመጣጣኝ ገንዘብ ከደንበኞች ላይ በመሰብሰብ፣ በኢትዮጵያ ንግድ መርከብ ድርጅት ስም በተከፈተው ሒሳብ ገቢ እንዲያደርጉና  ድርጅቱ ወደሚፈልገው አገር ባንክ በውጭ ምንዛሪ እንዲያስተላልፉ ታዘው ነበር።

ነገር ግን የጭነት ክፍያዎችን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል መፈጸም የሚችሉት፣ በባንኩ በኩል ከውጭ ዕቃ እንዲያስመጡ ፈቃድ (Foreign Exchange Permit) የተሰጣቸው መሆኑ ተጠቁሟል።

የንግድ ባንክ ኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ የአብስራ ከበደ ለሪፖርተር  ለቀረበላቸው ጥያቄ ሙሉ መረጃ ለመስጠት ገና መሆኑን ጠቁመው፣ ጥፋት መፈጸሙ የሚረጋገጠው የማጣራት ሒደቱ ሲጠናቀቅ እንደሆነ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የባንኩ ከፍተኛ ሥራ ኃላፊ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ምንም እንኳን ጉዳዩ እየተጣራ ቢሆንም ሠራተኞች ስለመመርያው ያላቸው ዕውቀት አነስተኛ መሆን ለተፈጠረው ክፍተት ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡  

ይሁን እንጂ ስህተቱ በኦዲተሮች ከተረጋገጠ አስተዳደራዊ ዕርምጃዎች ሊወሰዱ የሚችሉበት ዕድል እንዳለ ተናግረዋል። ነገር ግን በቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ የሚመራው የንግድ ባንክ ቦርድ፣ በጉዳዩ ላይ በዚህ ሳምንት ወሳኔ እንደሚሰጥ ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ዕግዱ ግርታ እንደፈጠረባቸው ሪፖርተር ያነጋገራቸው ሠራተኞች ገልጸው፣ ‹‹አፈጻጸማችሁ አመርቂ ነው ተብለው ጉርሻ (ቦነስ) በተሰጠን ወራት ውስጥ መታገዳችን ተገቢ አይደለም፤›› ብለዋል።

አንድ በቦሌ ክፍለ ከተማ የሚገኝ ቅርንጫፍ የሚሠሩ ገንዘብ ከፋይ (ቴለር) ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ዕግዱን ለምን እንደተሰጣቸው በተቀበሉት ደብዳቤ ላይ በግልጽ አልተቀመጠም፡፡ ‹‹በታገድን በቀናት ውስጥ ከሌላ ቅርንጫፎች በመጡ ሠራተኞች መተካታችን እንባረር ይሆን የሚል ሥጋት ውስጥ ከቶናል፤›› ብለዋል።

ከ60 ሺሕ በላይ ቋሚና ጊዜያዊ ሠራተኞች ያሉት ንግድ ባንክ በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመርያ ሦስት ወራት 6.8 ቢሊየን ብር ትርፍ ያስመዘገበ ሲሆን፣ 30.5 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ አግኝቷል። ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ትርፉ የ122 በመቶ ዕድገት ሲያሳይ ገቢው በ92 በመቶ አድጓል።

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች