Friday, July 19, 2024

[ክቡር ሚኒስትሩ አንድ የውጭ ስብሰባ ተካፍለው ወደ አገር ቤት እንደተመለሱ ቢሮ ገብተው ከአማካሪያቸው ጋር እየተነጋገሩ ነው]

 • እንኳን ደህና መጡ ክቡር ሚኒስትር፡፡ 
 • እንኳን ደህና ቆየኸኝምን አዲስ ነገር አለ?
 • ሁሉ አዲስ በአዲስ ሆኗልከየትኛው ልጀምርልዎት ክቡር ሚኒስትር?
 • ተው እንጂይኼን ያህል?
 • አዎ! እንዲያውም ከዋናው ልጀምርልዎት!
 • እሺጥሩ፡፡ 
 • አንድ ብለው ይቁጠሩ እንግዲህ… 
 • እሺአንድ፡፡ 
 • ካሳጊታን ተቆጣጥረናል፡፡ 
 • ጤነኛ አይደለህም?
 • ጤነኛ መሆኔን
 • ምን አጭሰህ ነው የመጣኸው
 • ምንምደስታ አጭሶኝ ይሆናል ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • በል ወደ ቁም ነገሩ ተመለስና ተፈጠሩ ያልካቸውን አዲስ ነገሮች ተናገር።
 • ቅድም እንደጠቀስኩት አንዱ ካሳጊታን መቆጣጠራችን ነው፡፡
 • ይህ ሰው ምን ነክቶታል ዛሬ
 • ክቡር ሚኒስትር እርስዎ ካሳጊታን ስላላወቁ የእኔ ጤነኛነት መጠርጠር የለበትም፣ ተገቢ አይደለም።
 • ለምን እንቆቅልሽ ታድርግብኛለህ? ለምን ግልጽ አድርገህ አትነግረኝም?
 • እንደዚያ ይሻላል፣ አሁን እነግርዎታለሁ ክቡር ሚኒስትር።
 • እኮ በላ….
 • ይኸውልዎት ክቡር ሚኒስትር ካሳጊታን የተቆጣጠርነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ግንባር ከዘመቱ በኋላ ነው። 
 • የቱ ጠቅላይ ሚኒስትር?
 • የባሰ አታምጣ አሉ!?
 • እንዴት… እንዴት ነው የምትናገረው አንተ?
 • እንዴ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሲዘነጉ ምን ልበል ታዲያ?
 • እኮ የቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ነው የምትለው? ስንት ጠቅላይ ሚኒስትር ባለበት ዓለም ስለየትኛው እንድምታወራ እንዴት ማወቅ እችላለሁ?
 • ብዙ ጠቅላይ ሚኒስትሮች ቢኖሩም እኝህኛውን ሊዘነጉ አይገባም ነበር፡፡ 
 • እኮ የትኛው? የቱ በምን ልወቀው?
 • ወደ ጦር ግንባር የዘመቱ አልኩ አይደለም እንዴ ክቡር ሚኒስትር? 
 • እና ብትልስ?
 • ሌላ ወደ ግንባር የዘመተ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚያውቁ ከሆነ ይንገሩኝ?
 • አላውቅም፡፡
 • እኮ፣ ታዲያ እንዴት የትኛው ጠቅላይ ሚኒስትር ይሉኛል?
 • ታዲያ እሱ ከአፍጋኒስታን ጋር ምን አገናኘው?
 • አላልኩም…
 • ከካዛኪስታንም ቢሆን ያው ነው፡፡
 • እንደዚያም አላልኩም፡፡
 • ጤነኛ አይደለም እንዴ ሰውዬው? ታዲያ ምንድነው ያልከው?
 • ካሳጊታ!
 • የት ነው እሱ?
 • እዚሁ ነው። 
 • የት ነው እዚሁ ማለት? 
 • የአፋር ክልል ድንበር ላይ ነው…
 • ምን?
 • ስነግርዎት!? አፋር ክልል ከአማራ ክልል በሚዋሰንበት አካባቢ ያለ ከፍታ ቦታ ነው። 
 • እና ይህንን ነው አዲስ ነገር ያልከኝ?
 • አዲስ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ የታሪክ መዝገብ ከፍ ያለ ቦታ እንደሚኖረው አልጠራጠርም፣ ምክንያቱም በጦር ሜዳ እየተመዘገበ ላለው ድል መሠረት ነው።
 • ግን…
 • ሌላ አዲስ ነገር መኖሩን አሁን ተገነዘብኩ፡፡
 • ምንድነው እርሱ?
 • እርስዎ ከዚያው አካባቢ መጥተው ካሳጊታን አለማወቅዎ፡፡
 • ከዚያ አካባቢ ብመጣስ? ሁሉን ተራራና መንደር የማወቅ ግዴታ አለብኝ እንዴ? እንዴት ላውቅ እችላለሁ? 
 • እኔማ ሚኒስትር ስለሆኑ ብዬ ነው… 
 • ሚኒስትር ብሆንስ?
 • ያው የአገሪቱን ሕዝብ አኗኗርና አካባቢዎችን ማወቅ ይጠቅማል ብዬ ነው። 
 • ማወቅ ይጠቅማል ብዬ ነው ይለኛል እንዴ ደግሞ? እንኳን እዚህ መሥሪያ ቤት ተመድቤ ይቅርና እዚያ የተመደቡትም አያውቁትም፡፡ 
 • የት የተመደቡት፡፡
 • ማዕድን ሚኒስቴር?

[ወደ ጦር ግንባር ሳይሄዱ የመንግሥትንለታዊ ተግባር በመፈጸም ላይ የሚገኙት ክቡር ሚኒስትር፣ የግንባር ውሎውን የተመለከተ መረጃ ከፀጥታ ጉዳዮች አማካሪው እየተቀበሉ ነው]

 • ክቡር ሚኒስትር በሁሉም ግንባር የተሠለፈው ጦር ከፍተኛ መነቃቃት ውስጥ በመሆኑ በየግንባሩ ከፍተኛ ድል እየተመዘገበ ነው፣ በተለይ በሁለት ቁልፍ ቦታዎች የተመዘገቡ ድሎች ጦርነቱን በአጭሩ ለማጠናቀቅ ወሳኝ ናቸው።
 • እነዚህ ቦታዎች የትኞቹ ናቸው? 
 • አንደኛው የካሳጊታ ኮረብታ ሲሆን፣ ሌላኛው ደግሞ በወሎ በኩል ለበርካታ አካባቢዎች ማዕከል የሆነው የጋሸና ግንባር ነው። 
 • እና የእነዚህ ቦታዎች መያዝ ጦርነቱን በአጭር ለማጠናቀቅ ያስችላል ነው የምትለኝ?
 • እንዴታ፣ የካሳጊታን ኮረብታ ላይ መሽጎ የነበረው የጠላት ኃይል በኮረብታው አቅራቢያ የሚገኙ ከተሞችን በቀላሉ የተቆጣጠረው ቁልፍ ቦታ ላይ ስለመሸገ ነው። 
 • እንደዚያ ነው?
 • አዎ ክቡር ሚኒስትር፣ በዚህ ሥፍራ ጠላት ድባቅ ከተመታ በኋላ በዙሪያው ያሉ ከተሞችን እስከ ባቲ ድረስ በሁለት ቀናት ወስጥ በቀላሉ በእኛ ቁጥጥር ሥር ወድቀዋል፣ በጋሸና አካባቢም እንደዚያ እንደሚሆን ይጠበቃል።
 • ጋሸናን በቁጥጥር ሥር ብናውል ማለትህ ነው? ምን ይጠበቃል?
 • ጋሸና በቁጥጥር ሥር ገብቷል ማለት ይቻላል ክቡር ሚኒስትር፣ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ሥር ሲውል ማለት የእኛ ኃይል በሁሉም አካባቢ በሙሉ አቅሙ ሲገባ ማለት ነው፣ ይህ ከሆነ በዙሪያው ያሉ ከተሞችም ጉዳይም ያበቃል።
 • የትኞቹ ከተሞች?
 • ጋሸና ሙሉ በሙሉ ከተያዘ በዙሪያው ያሚገኙት ከወልዲያ እስከ ደሴ ያሉ አካባቢዎች በቀላሉ ነፃ ይሆናሉ፣ ለዚህ ነው አለቃ በአካባቢው ላለው የጠላት ኃይል መልዕክት ያስተላለፉት።
 • እጅ እንዲሰጡ ያሉትን ማለትህ ነው?
 • አዎ ክቡር ሚኒስትር፣ በእነዚህ ከተሞች ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለብንና ለዚህም ቀድመን መንቀሳቀስ እንደሚጠበቅብን ይሰማኛል።
 • ምንድን ነው ሥጋትህ? ከምንድነው የምንጠነቀቀው?
 • ክቡር ሚኒስትር በእነዚህ ከተሞች ጠላት ሲገባ በከተሞቹ ውስጥ ለረዥም ጊዜ ነዋሪ የነበሩ ግለሰቦች ያልተገባ ባህሪ አሳይተዋል በሚል፣ ስሜታዊ እንቅስቃሴና ጥቃት እንዳይደርስ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ አለበት። 
 • ትክክለኛ ሥጋት ነው፣ የጠላት ኃይል ራሱ እንደዚያ ዓይነት ጥቃት እንዲፈጸም ሊያበረታታ ስለሚችል ቀድሞ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል፣ ስለዚህ በቀጣይ የፀጥታ ኮሚቴው ስብሰባ ላይ ትኩረት እናደርግበታለን። 
 • አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

አቶ ሰብስብ አባፊራ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

ከአዋጅና መመሪያ ውጪ ለዓመታት ሳይካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ...

ቀጣናዊ ገጽታ የያዘው የኢትዮ ሶማሊያ ውዝግብ

ከአሥር ቀናት ቀደም ብሎ በተካሄደው የፓርላማ 36ኛ መደበኛ ስብሰባ፣...

የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በዓረቦንና የጉዳት ካሳ ክፍያዎች ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ መጣሉን ተቃወሙ

በአዲሱ ተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ውስጥ የኢንሹራንስ ከባንያዎች ለሚሰበስቡት...

የዘንድሮ ነገር!

ጉዞ ከስድስት ኪሎ ወደ ካዛንቺስ፡፡ ከእንጦጦ በኩል ቁልቁል እያስገመገመ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ የቅርብ ወዳጃቸው ከሆነች አንድ ባለሀብት የተደወለላቸውን ስልክ አንስተው በኮሪደር ልማቱ ላይ የምታቀርበውን ቅሬታ እየሰሙ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እኔ የኮሪደር ልማቱ ላይ ተቃውሞም ሆነ ጥላቻ እንደሌለኝ የሚያውቁ ይመስለኛል? በዚህ እንኳን አትታሚም።  የእውነቴን ነው ክቡር ሚኒስትር። አውቃለሁ ስልሽ? ለኮሪደር ልማቱ አዋጡ ሲባልም ያለማመንታት አምስት ሚሊዮን...

[ክቡር ሚኒስትሩ በችግኝ ተከላ ፕሮግራም ላይ ሳይገኝ ከቀረው አንድ የተቋማቸው ባልደረባ የሆነ የተቃዋሚ ፓርቲ አባልን አስጠርተው እያናገሩ ነው]

ለምንድነው በዚህ አገራዊ ፋይዳ ባለው ፕሮግራም ላይ ያልተገኘኸው? ክቡር ሚኒስትር ህሊናዬ አልፈቀደልኝም። መቃወምና መተቸት ብቻ ውጤት የሚያመጣ መስልዎህ ከሆነ ተሳስተሃል። አልተሳሳትኩም ክቡር ሚኒስትር? ቆይ የመጀመሪያ ዓመት የችግኝ ተከላ...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላነጋግርህ የፈለኩት ክቡር ሚኒስትር፡፡ እርስዎማ ቀጠሮ መያዝ አያስፈልግዎትም፣ ምን ገጠመዎት? እኔማ ምን ይገጥመኛል አንተኑ ልጠይቅህ እንጂ? ምን? እውነት ለመናገር የማየው ነገር አሳስቦኛል፡፡ ይንገሩኝ...