Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የአሜሪካና የእንግሊዝ ኤምባሲዎችን ማብራሪያ ጠየቀ

የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የአሜሪካና የእንግሊዝ ኤምባሲዎችን ማብራሪያ ጠየቀ

ቀን:

ከ22 በላይ የፓለቲካ ፓርቲዎች አባል የሆኑበት የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምከር ቤት፣ ሕወሓትን በመደገፍና በከተማዋ ውስጥ ሽብርን በመንዛት ተንቀሳቅሰዋል ያላቸውን የአሜሪካና እንግሊዝ ኢምባሲዎች ማብራሪያ ጠየቀ፡፡

ምክር ቤቱ ማክሰኞ ኅዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም. ለሪፖርተር በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በዋናነት ግንባር ቀደም ሆነው በአሸባሪነት የተሰየመውን ሕወሓት ቡድን እየደገፉ ነው ላላቸው አገሮች፣ ኤምባሲዎችም ሆኑ መንግሥቶቻቸው፣ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሽብርን ከመንዛት እንዲቆጠቡ ማሳሰቢያ መላኩን ገልጿል፡፡

የምክር ቤቱ ሰብሳቢና የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ አበበ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ሁለቱ አገሮች በዋናነት የተመረጡት የሕወሓትን የሐሰት ፕሮፓጋንዳና መረጃ በመንዛት፣ ዜጎቻቸው ከአዲስ አበባ ለቀው እንዲወጡና ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ቅስቀሳ ሲያደርጉ በመቆየታቸው ነው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

እነዚህ አገሮች ከኢትዮጵያ ጋር ጥልቅ የሆነ ወዳጅነት እያላቸው ሐሰተኛ መረጃ በመንዛታቸው ሌሎችም አገሮች በተመሳሳይ እንቅስቃሴ እንዲሳተፉ ቅስቀሳ እያደረጉ በመሆናቸው፣ ከይፋ የወዳጅነት ወደ ይፋ ባላንጣነት እያመሩ እንደሆኑ አቶ ሙሉጌታ አስረድተዋል፡፡

በሌላ በኩል የእነዚህ አካላት የሽብር መረጃ የከተማውን ነዋሪዎች ለማሸበር ሆን ተብሎ የሚሠራጭ በመሆኑ፣ ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ለማሳሰብ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከአሜሪካም ሆነ ከእንግሊዝ ጋር ያላት ግንኙነት በጣም ወዳጅ ከሚባሉ አገሮች መካከል የሚመደብ እንደሆነ፣ በተለይም ሽብርን በመዋጋት ረገድ ከሁለቱ አገሮች ጋር ኢትዮጵያ ስትጫወተው የነበረው ሚና ትልቅ ሆና ሳለ፣ ሕጋዊ የሆነውን የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ ጎን በመተው በአገሪቱ ፓርላማ አሸባሪ ተብሎ የተሰየመውን ድርጅት በመደገፍና ከኋላ በመከተል የቡድኑን ዓላማ ይዞ ቅስቀሳ ማድረግ አግባብ እንደልሆነ ገልጸዋል፡፡

እንግሊዝ በጣሊያን ወረራ ወቅት ለኢትዮጵያ ያደረገችው አስተዋጽኦና ዕገዛ በትልቁ የሚታወስ ቢሆንም፣ አሁን ግን በተቃራኒው ቆማለች ብለዋል፡፡

ለሌሎች አገሮች ጭምር ተምሳሌት ሊሆን የሚችለው የኢትዮጵያና የአሜሪካ ወዳጅነት ኢትዮጵያ ዕገዛ በሚያስፈልጋት በዚህ ወሳኝ ወቅት፣ በተለይም ሕወሓት ይቅር የማይባል በደል ባደረሰበት በዚህ ጊዜ የአሜሪካ መንግሥት ማዕቀብ ሊጥልበት ይገባል ሲሉ አስረድተዋል፡፡ ሕወሓትን ከሕጋዊ መንግሥት ጋር በእኩል በንፅፅር በመመልከት፣ በሰብዓዊነት ሰበብ በኢትዮጵያውያን መሀል ክፍፍል ለመፍጠር የተደረገው እንቅስቃሴ፣ የአጎዋ ዕድልን ከኢትዮጵያ ለመንጠቅ የተሄደበት ርቀትና የተጠና የሐሰት ፕሮፓጋንዳ መንዛት ላይ መጠመድ አላስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ እንዲሁም የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ ላይ ከሕወሓት ያልተናነሰ በደል እያደረሰ ስለመሆኑ ከላይ የተጠቀሱት ማሳያ እንደሆኑ በፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት መግለጫ ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም አሜሪካና እንግሊዝ በአዲስ አበባ ሰላም እያለ ሰላም እንደሌለ በማስመሰል በተደጋጋሚ መግለጫዎችን በማውጣት፡፡ የከተማ ሽብር እየፈጠሩ መሆናቸውን አመላክቷል፡፡

አቶ ሙሉጌታ፣ ‹‹በእርግጥ ኢትዮጵያ በፉጨት የተሰበሰበችና በፊሽካ የምትፈርስ አገር አይደለችም›› ብለው፣ እንዲህ ባለመሆኗም በአዲስ አበባ ከተማ እነዚህ አካላት ብዙ ጥረት ቢያደርጉም አልታሳካላቸውም ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

በመሆኑም የደብዳቤያቸው ዓላማ በከተማው ውስጥ ‹‹ሕዝቡ ወይም መንግሥት የማያውቀው ጉዳይ ካለ ማብራሪያ እንዲሰጡና ውይይት ለማድረግ መሆኑን አቶ ሙሉጌታ አክለው ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...