Tuesday, November 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበጦርነቱ ሳቢያ 5.6 ሚሊዮን የአማራ ክልል ነዋሪዎች ለችግር መዳረጋቸው ተነገረ

በጦርነቱ ሳቢያ 5.6 ሚሊዮን የአማራ ክልል ነዋሪዎች ለችግር መዳረጋቸው ተነገረ

ቀን:

በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በትግራይ፣ በአማራና አፋር ክልሎች በተስፋፋው ጦርነት ሳቢያ 5.6 ሚሊዮን የአማራ ክልል ነዋሪዎች ለችግር መዳረጋቸው ተገለጸ፡፡ በአፋር ክልል ደግሞ 260 ሺሕ ሰዎች ለችግር ተጋልጠዋል ተብሏል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት የውጭ ቋንቋዎችና የዲጂታል ሚዲያ ኃላፊ ቢልለኔ ሥዩም ማክሰኞ ኅዳር 21 ቀን 2014 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት፣ እነዚህ ነዋሪዎች ለችግር የተጋለጡት የትግራይ ክልል ጦርነት ወደ ሁለቱ ክልሎች በመስፋፋቱ ነው፡፡

ከእነዚህ ውስጥ በአማራ ክልል 1.1 ሚሊዮን ዜጎች፣ እንዲሁም በአፋር ክልል ከ100 ሺሕ በላይ ነዋሪዋች የተፈናቀሉ መሆናቸውን ያመላከቱት ቢልለኔ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ድጋፍ እንዲደረግላቸው እየሠራ ነው ብለዋል፡፡

በዚህም መሠረት ባለፈው ሳምንት ብቻ ከ36 ሺሕ ኩንታል በላይ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕርዳታዎች በአደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን እንዲደርስ ተደርጓልም ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ወደ ትግራይ ክልል ድጋፎችን የሚያደርሱ ሁለት የአየር በረራዎች በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አማካይነት መደረጋቸውን በማከል፣ የዕርዳታ ጫኝ ተሽከርካሪዎችም በርካታ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕርዳታ አድርሰዋል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ባለፉት ጥቂት ቀናት ከ100 በላይ ተሽከርካሪዎች በርካታ ዕርዳታ ጭነው ወደ መቀሌ ማቅናታቸውን ተናግረዋል፡፡

ጦርነቱ አሁን በአማራና በአፋር ክልሎች እየተደረገ ሳለ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሆነ ብሎ ትኩረቱን በትግራይ ክልል ብቻ አድርጓል ያሉት ኃላፊዋ፣ ሆን ተብሎ በማኅበራዊና በመደበኛ ሚዲያ ሕወሓትን ተጠቂ አስመስሎ ለማቅረብም እየተሰማ ነው ብለዋል፡፡ ቢልለኔ አክለውም የምዕራቡ ዓለም የከፈተው የሚዲያ ዘመቻ ለዚሁ ዓላማ እየዋለ ነው ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አሀመድ (ዶ/ር) ጦሩን ለመምራት ወደ ግንባር ካመሩ አንድ ሳምንት እንደሆናቸው፣ ይኼም ሆን ተብሎ ተንጋዶ እየቀረበ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጦርነቱንና ግጭቱን ለማባሳስ ሳይሆን ሕገ መንግሥታዊ ግዴታዎችን ለመወጣት በማለም ነው የዘመቱት በማለት አስረድተዋል፡፡ መረጃ ከማንጋደድ በተጨማሪም የኢትዮጵያን ድምፅ የሚወክሉ አቋሞችን የማፈን ሥራዎች ተስተውለዋል ብለው፣ ትዊተርና ሌሎች የማኅበራዊ ትስስር ገጾች በአፍቃሪ ሕወሓት ሠርጎ ገቦች ተይዘዋል ሲሉም አውስተዋል፡፡

ቢልለኔ ለዳያስፖራው ማኅበረሰብ ባቀረቡት ጥሪ፣ ‹‹የአገራችሁ ኑባሬ ከጥያቄ ወድቋልና የፖለቲካና የርዕዮተ ዓለማዊ ልዩነቶቻችሁን ትታችሁ እያደረጋችሁ ያለውን ድጋፍ ቀጥሉ፤›› ብለዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ ሲኒመር ትሬዲንግ...

የባህር በር በቀጣናዊ ተዛምዶ ውስጥ

በበቀለ ሹሜ መግቢያ በ2010 ዓ.ም. መጋቢት ማለቂያን ይዞ ዓብይ አህመድ በጠቅላይ...

ሥጋት ያስቀራል ተብሎ የሚታሰበው የጫኝና አውራጅ መመርያ

በአዲስ አበባ ከተማ በሕገወጥ መልኩ በመደራጀት ማኅበረሰቡ ላይ እንግልትና...

ማወቅ ወይስ አለማወቅ – ድፍረት ወይስ ፍርኃት?

በአሰፋ አደፍርስ ወገኖቼ ፈርተንም ደፍረንም የትም አንደርስምና ለአገራችን ሰላምና ክብር...