Saturday, May 25, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ሁለት ቢሊዮን ዶላር ማስተማመኛ ካፒታል እንዲያስቀምጥ የታዘዘው የቻይና ኩባንያ ትዕዛዙን እንዳልፈጸመ ታወቀ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

በሶማሌ ክልል የተገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ ለማልማት ፈቃድ ያገኘው የቻይና ኩባንያ፣ ፕሮጀክቱን ለማከናወን የሚያስችል የፋይናንስ አቅም ያለው መሆኑን ሁለት ቢሊዮን ዶላር የኢንቨስትመንት ካፒታል ተቀማጭ በማድረግ እንዲያረጋግጥ በመንግሥት ቢታዘዝም፣ ትዕዛዙን እንዳልፈጸመ ታወቀ።

ፖሊ ጂሲኤል የተባለው የቻይና ኩባንያ በሶማሌ ክልል የተገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ለማልማት ፈቃድ ከወሰደ በኋላ፣ ወደ ተጨባጭ የፕሮጀክት ትግበራ መሸጋገር ባለመቻሉ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያና ፕሮጀክቱን ለማከናወን የሚያስችል የፋይናንስ አቅም እንዳለው ለማስተማመን፣ ለፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ ትግበራ የሚያስፈልገውን የኢንቨስትመንት ካፒታል በብሔራዊ ባንክ ተቀማጭ እንዲያደርግ የማዕድን ሚኒስቴር፣ መስከረም 19 ቀን 2014 ዓ.ም. በላከለት ደብዳቤ ትዕዛዝ ሰጥቶት ነበር። 

ጉዳዩን በተመለከተ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የማዕድን ሚኒስቴር ከፍተኛላፊ፣ ኩባንያው የተባለውን ትዕዛዝ እስካሁን እንዳልፈጸመ አረጋግጠዋል። 

ኩባንያው የተጓተተውን የተፈጥሮ ጋዝ ልማት ለማከናወን የሚያስችል የፋይናንስ አቅም ያለው ስለመሆኑ ጥርጣሬ በመኖሩና ባልተጨበጠ አቅም የአገር ሀብት ሳይለማ እንዲያድር መፍቀድና በተስፋ መጠበቅ፣ በተለይ በዚህ ወቅት የማይታሰብ በመሆኑ መሟላት የሚገባቸውን ጉዳዮች የያዘ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ከጊዜ ገደብ ጋር ለኩባንያው መሰጠቱን ኃላፊው አስረድተዋል። 

መሟላት አለባቸው ከተባሉት ጉዳዮች መካከል አንዱ ኩባንያው ቢያንስ የፕሮጀክቱን የመጀመሪያ ምዕራፍ ለማከናወን የሚያስችል የፋይናንስ አቅም ያለው ስለመሆኑ፣ ሁለት ቢሊዮን ዶላር በብሔራዊ ባንክ ዝግሳብ ገቢ በማድረግ ለማዕድን ሚኒስቴር እንዲያሳውቅ የሚል ይገኝበታል።

ይህንንም ... እስከ ዲሴምበር 29 ቀን 2021 ድረስ እንዲፈጽም መታዘዙን የገለጹት ኃላፊው፣ የቻይናው ኩባንያ ፖሊ ጂሲኤል ግን እስካሁን ትዕዛዙን እንዳልፈጸመና ለትዕዛዝ ደብዳቤውም ምላሽ እንዳልሰጠ ለሪፖርተር ገልጸዋል።

ፕሮጀክቱን ለማልማት የሚያስችል የፋይናንስ አቅም ያለው መሆኑን እንዲያረጋግጥ ከመታዘዙም በተጨማሪበፕሮጀክቱ ብሎክ 17 እና ብሎክ 20 ሥ የታቀደውን በተሟላ ሁኔታ ያልፈጸመ በመሆኑ አሥር ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንዲያደርግ፣ እንዲሁም የልማት ፕሮጀክቱ በሚገኝበት አካባቢ ማበርከት የሚጠበቅበትን የማኅበረሰብ ልማት ግዴታ ባለመፈጸሙ፣ ይህንንም በአስቸኳይ ገቢ እንዲያደርግ ታዞ እንደነበር ኃላፊው ገልጸዋል። 

በመሆኑም ኩባንያው በቀረው አጭር ጊዜ ውስጥ የተጠቀሱትን አሟልቶ የማይፈጽም ከሆነ፣ የማዕድን ሚኒስቴር በማስጠንቀቀያ ደብዳቤው እንዳስታወቀውና የኩባንያውን የማዕድን ልማት ፈቃድ የመሰረዝርምጃ እንደሚወስድ የገለጹት ኃላፊው፣ማዕድን ሚኒስቴር የሚወስደውንርምጃ የፍትሕ ሚኒስቴር እንዲያውቀው መደረጉንም ጠቁመዋል። 

በሶማሌ ክልል የተገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ የተወሰነ መጠን በግብዓትነት የሚጠቀም ግዙፍ የእርሻ ማዳበሪያ ፋብሪካ በድሬዳዋ ከተማ በሁለት ቢሊዮን ዶላር ለመገንባት፣ ከሦስት ዓመት በፊት ውል የፈጸመውና ቦታ የተረከበው የሞሮኮ ኩባንያም የተፈጥሮ ጋዝ ልማቱ በመጓተቱ ምክንያት ፋብሪካውን ለመገንባት እስካሁን እንዳልቻለም የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የቻይናው ኩባንያ በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጥ በአዲስ አበባ አድራሻው በኩል በተደጋጋሚ የተደረገው ጥረት አልተሳካም።

የቻይናው ኩባንያ ፖሊ ጂሲኤል በሶማሌ ክልል ካሉብሂላላ በተባሉ አካባቢዎች የተገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት እንዲያለማ ፈቃድ ከወሰደ ስድስት ዓመታት ተቆጥረዋል። 

በተጠቀሱት አካባቢዎች የተገኘው የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ስምንት ትሪሊዮን ኪዩቢክ ጫማ በላይ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ይህ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት የተረጋገጠ በመሆኑ ከኩባንያው የሚጠበቀው የተፈጥሮ ጋዙን በማልማትና የጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧና የማጣሪያ መሠረተ ልማት በመገንባት ምርቱን ለገበያ ማቅረብ ብቻ የሚጠይቅ እንደሆነ ቢገለጽም፣ በሶማሌ ክልል የተገኘው የተፈጥሮ ጋዝን ወደ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም መቀየር ሳይቻል የውጭ ኩባንያዎች ብቻ እየተፈራረቁበት ሁለት አሠርታት መጠበቅ ግድ ሆኗል።

ፖሊ ጂሲኤል በዚሁ በሶማሌ ክልል የፔትሮሊየም ልማት ፈቃድ እንዳለው የሚታወቅ ሲሆንየዛሬ ሦስት ዓመት ገደማ በተጠቀሰው የሶማሌ ክልል የኦጋዴን ተፋሰስ ውስጥ የነዳጅ ዘይት እንዳገኘ ማስታወቁና ይህንንም ተከትሎ በወቅቱ የነበሩ የፌዴራልና የክልል መንግሥታት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተገኙበት ሥርዓት ይፋ መድረጉ ይታወሳል።

በኦጋዴን የነዳጅ ዘይት ክምችት መኖሩ በጥናት ከተረጋገጠ በርካታ አሠርታት የተቆጠሩ ቢሆንም፣ የቻይናው ኩባንያ አገኘ የተባለው የነዳጅ ዘይት መጠን ምን ያህል እንደሆነ ግን በትክክል እንዳልተለየ መረጃዎች ያመለክታሉ።

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች