Thursday, December 1, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊጦርነቱ በትምህርት ዘርፍ ላይ ያደረሰውን ጉዳት ለማካካስ በርካታ ዓመታት እንደሚወስድ ተነገረ

  ጦርነቱ በትምህርት ዘርፍ ላይ ያደረሰውን ጉዳት ለማካካስ በርካታ ዓመታት እንደሚወስድ ተነገረ

  ቀን:

  በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት በትምህርት ዘርፉ ላይ የደረሰውን ጉዳት ለማካካስ፣ በርካታ ዓመታት እንደሚፈጅ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

  በጦርነቱ ምክንያት የደረሰው ጉዳት ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ ጥናት እየተደረገ እንደሆነ፣ ጠቋሚ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ጉዳቱ በቢሊዮን ብሮች የሚተመን መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስትር ደኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

  በአሁኑ ወቅት እየተደረገ ያለው ውጊያ ቢጠናቀቅ እንኳን የትምህርት ተቋማቱን ለማስጀመር ጊዜ እንደሚወስድ ያስረዱት ሚኒስቴር ደኤታው፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ትምህርት ለማስጀመር በዕቅድ መመራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

  በጦርነት ምክንያት መምህራን ተጎጂ መሆናቸውንና በአጠቃላይ አገር መድማቷን አክለው ገልጸዋል፡፡  በአማራና በትግራይ ክልሎች 15 የዩኒቨርሲቲዎች ካምፓሶች ሙሉ ለሙሉና በከፊል የተጎዱ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ በትግራይ ክልል አራት ዩኒቨርሲቲዎች፣ በአማራ ክልል ወልዲያ፣ ወሎና መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል፡፡

  ሳሙኤል (ዶ/ር) እንዳስረዱት፣ የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ አንድ ካምፓስና የሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች 14 ካምፓሶች በከፊልና ሙሉ በሙሉ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ በትግራይ ክልልና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች በጊዜያዊነት ወደ ተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች መመደባቸውን አስረድተዋል፣ በወሎ ዩኒቨርሲቲም መረጃ የማሰባሰብ ሥራ ሲጠናቀቅ በጊዜያዊነት ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ይመደባሉ ብለዋል፡፡

  በጦርነቱ ምክንያት ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችና ከ40 ሺሕ በላይ መምህራን ከትምህርትና ከሥራቸው መስተጓጎላቸውን ገልጸው፣ ይህ ቁጥር በቅርቡ ጦርነት ሲደረግባቸው የነበሩ ቦታዎች ሳይጨምር ነው ብለዋል፡፡

  በተጨማሪም ትምህርት ሚኒስቴር ኅዳር 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ባሳለፈው ውሳኔ፣ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችና መምህራን የዘማቾችን እህል እንዲሰበስቡና በተለያዩ ተግባራት ሠራዊቱን እንዲደግፉ ለአንድ ሳምንት ትምህርት መዘጋቱን አስታውቀዋል፡፡

  የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)፣ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከክልሎች ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር ኅዳር 20 ቀን 2014 ዓ.ም. በበይነ መረብ ባደረጉት ውይይት መወሰኑን አስታውቀዋል፡፡

  በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጀው የሕወሓት ቡድን በበቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት በግድ ወደ ጦርነት እንደተገባና አገርን የማዳንና የህልውና ትግል መሆኑን ያስረዱት ሚኒስትሩ በዚህም አርሶ አደሮች፣ ሚሊሻዎችና የገጠር ወጣቶች በጦር ግንባር እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ በዚህም በጦር ግንባር ከሚደረገው ፍልሚያ በተጨማሪ በደጀንነት ማበረታትና መደገፍ ለሚፈለገው ድል አስተዋጽኦው ከፍተኛ መሆኑን ያስረዱት ብርሃኑ (ፕሮፌሰር)፣ አገርን በጋራ የማቆም ጉዳይ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

  ከተለያዩ የትምህርት የማኅበረሰብ ክፍሎች በቀረቡ ጥያቄዎች መሠረት ትምህርት ሚኒስቴር ከክልሎች የትምህርት ቢሮዎች ባደረገው ምክክር የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ መምህራንና ሠራተኞች ከኅዳር 27 እስከ ታኅሳስ 3 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ መደበኛው የትምህርት ፕሮግራም መቆሙን አብራርተዋል፡፡

  በዋነኛነት ቅድሚያ የሚሰጠው የዘማቾችን የደረሱ ሰብሎች መሰብሰብ መሆኑን ያስረዱት ሚኒስትሩ፣ እያንዳንዱ ዜጋ በሚችለው ሁሉ ገንዘብ በማዋጣት፣ ደም በመለገስና ስንቅ በማዘጋጀት እንዲሳተፍ ይደረጋል ብለዋል፡፡

  ትምህርት የተዘጋባቸው ቀናት ትምህርት ቤቶች በሚያወጡት የትምህርት ማካካሻ መርሐ ግብሮች መሠረት ይካካሳሉ ብለዋል፡፡

  ተማሪዎች ትምህርት ያቋረጡበት ሳምንት አገራቸው ያለችበትን ሁኔታ እያሰቡ፣ ለወደፊት እንዲህ ዓይነት ጦርነት በምንም ዓይነት ሁኔታ እንዳይደገምና አገራቸውን በመገንባት እንቅስቃሴ ውስጥ እንደሚሳተፉ ቃል የሚገቡበት ታሪካዊ ሳምንት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...