Sunday, May 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየኮሮና ክትባትን ኅብረተሰቡ በሚፈለገው ልክ እየወሰደ አለመሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

የኮሮና ክትባትን ኅብረተሰቡ በሚፈለገው ልክ እየወሰደ አለመሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

ቀን:

ከተጀመረ ሁለት ሳምንት ባስቆጠረው አገር አቀፍ የኮሮና ወረርሽኝ መከላከያ ክትባት፣ ኅብረተሰቡ በሚፈለገው መጠን እየተከተበ አለመሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የጤና ሚኒስቴር የብሔራዊ ክትባት አስተባባሪ አቶ ዮሐንስ ላቀው ለሪፖርተር፣ ‹‹ኅብረተሰቡ በተለያዩ የተዛቡ አመለካከቶች የተነሳ የኮቪድ-19 ክትባቶችን ለመቀበል ፈቃደኛ አይደለም፤›› ብለዋል፡፡ በኮሮና ወረርሽኝና በክትባቱ ዙሪያ ብዙ የተዛቡ መረጃዎች ከመውጣታቸው ጋር በተያያዘ ክትባቱን አምኖ ለመከተብ ብዙዎች እንደሚያንገራግሩ የጠቀሱት ኃላፊው፣ ሚዲያውም ሆነ የሃይማኖት ተቋማትና የሚመለከታቸው ማኅበረሰብ አንቂ አካላት ግንዛቤ በመፍጠር ያግዙን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

‹‹በፊት ከ18 ዓመት በላይ የሆናቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ሲከተቡ ቆይተዋል፡፡ አሁን ግን ያመጣነውን የፋይዘር ክትባት ከ12 ዓመት በላይ ያሉ ሰዎች እንዲወስዱ የማድረግ ዕቅድ ይዘን በአገር አቀፍ ደረጃ የክትባት ዘመቻ ጀምረናል፤›› ያሉት አቶ ዮሐንስ፣ ‹‹ነገር ግን ክትባቱን በተመለከተ ከሃይማኖት፣ ከስለላ፣ ከፖለቲካ፣ ከማይክሮ ቺፕና ከሌሎች ነገሮች ጋር የተገናኙ የተዛቡ አመለካከቶች በኅብረተሰቡ ዘንድ ስለተሠራጩ፣ በምንፈልገው ልክ የሚከተቡ የኅብረተሰብ ክፍሎችን እያገኘን አይደለም፤›› ብለዋል፡፡

- Advertisement -

‹‹ይህን መሰል የተዛባ አመለካከት ያለበት ሰውን የጤና ባለሙያዎቻችን ለማሳመን አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል፤›› ያሉት አቶ ዮሐንስ፣ የሃይማኖት ተቋማትም ሆኑ ሚዲያውና የሚመለከታቸው ሁሉ ግንዛቤን በመለወጥ ዙሪያ ያግዙን ሲሉ የክትባት ዘመቻው የገጠመውን እክል አስረድተዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ክትባቱን አስገዳጅ ለማድረግ አሁን የሌሎች አገሮችን ተሞክሮ እያጠና እንደሚገኝ ያመለከቱት አቶ ዮሐንስ፣ ክትባቱን አስገዳጅ ያደረጉና ቅጣት እስከ መጣል የደረሱ አገሮች መኖራቸውን አውስተዋል፡፡ የጤና ሚኒስቴር የኮቪድ-19 ክትባት በኢትዮጵያ አስገዳጅ ማድረግ በሚቻልበት መንገድ ላይ የሚያደርገውን ጥናት እንዳበቃም ጉዳዩን ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ጠቁመው፣ አሁን ከውይይት ባለፈ ክትባቱን በአስገዳጅ ሁኔታ በኢትዮጵያ መስጠት አለመጀመሩን ገልጸዋል፡፡

ወደ አገር ውስጥ ከገባው 14 ሚሊዮን ክትባት ውስጥ እስካሁን ከ9.4 ሚሊዮን በላይ ክትባት ለኅብረተሰቡ መሰጠቱን የተናገሩት የጤና ሚኒስቴር የብሔራዊ ክትባት አስተባባሪው አቶ ዮሐንስ፣ በቅርብ በዓለም ላይ እየተከሰቱ ያሉ በሥርጭትም ሆነ በገዳይነታቸው አደገኛ የሆኑ የቫይረስ ዓይነቶች ክትባትን መውሰድ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን በደንብ እንዳመላከቱ ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም ኅብረተሰቡ አሁንም ቢሆን ወረርሽኙን ለመግታት በፈቃደኝነት ክትባቱን ይውሰድ ሲሉ ምክረ ሐሳባቸውን አቅርበዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች መከፈት አገር በቀል ባንኮችን ለምን አስፈራቸው?

የማይረጥቡ ዓሳዎች የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ሙግት ሲሞገት! - በአመሐ...

የምርጫ 97 ትውስታ!

በበቀለ ሹሜ      መሰናዶ ኢሕአዴግ ተሰነጣጥቆ ከመወገድ ከተረፈ በኋላ፣ አገዛዙን ከማሻሻልና...

ሸማቾች የሚሰቃዩት በዋጋ ንረት ብቻ አይደለም!

የሸማች ችግር ብዙ ነው፡፡ ሸማቾች የሚፈተኑት ባልተገባ የዋጋ ጭማሪ...

መንግሥት ከለጋሽ አካላት ሀብት ለማግኘት የጀመረውን ድርድር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፓርላማው አሳሰበ

የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገልጿል አዲስ አበባ...