Thursday, March 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትወደ ባለሥልጣን ከፍ ያለው የፀረ አበረታች ቅመሞች ጽሕፈት ቤት

ወደ ባለሥልጣን ከፍ ያለው የፀረ አበረታች ቅመሞች ጽሕፈት ቤት

ቀን:

በኢትዮጵያ በየደረጃው ከስፖርት አበረታች ቅመሞች (ዶፒንግ) ነፃ የሆነ ስፖርት እንዲስፋፋና አትሌቶች በትክክለኛው መንገድ ተወዳድረው ውጤታማ የሆኑ ጤናማ ስፖርተኞችን እንዲያፈሩ ለማስቻል፣ መንግሥት በአገር አቀፍ ደረጃ የፀረ አበረታች ቅመሞች ጽሕፈት ቤት አቋቁሞ እየሠራ ይገኛል፡፡

በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 400/2009 የተቋቋመውን ጽሕፈት ቤት ወደ ባለሥልጣን ደረጃ ከፍ እንዲል ተደርጓል፡፡ ዝርዝር አፈጻጸሙን ለመወሰን ይቻል ዘንድ የፀረ አበረታች ቅመሞች የሕግ ማዕቀፎች የመጀመርያ ረቂት ሰነድ ቀርቦ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በትልልቅ ዓለም አቀፍ የውድድር ዓውዶች ላይ የአሸናፊነት ስሜትና ፍላጎት ብሎም በአቋራጭ አሸናፊ በመሆን ዳጎስ ያለ የገንዘብ ሽልማት ለማግኘት ከመፈለግ የተነሳ፣ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ አንዳንድ አትሌቶች ተጨማሪ ኃይል ሰጪ (የአካል ብቃትን የሚጨምሩ) ቅመሞችና ልዩ ልዩ ዘዴዎችን በተለያዩ መንገዶች የሚጠቀሙበት አጋጣሚ መኖሩ ይታወቃል፡፡

በእነዚህና ተያያዥ ምክንያቶች በ2008 ዓ.ም. በአዋጅ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ አበረታች ቅመሞች ጽሕፈት ቤት ችግሩን ለመቆጣጠር በሕግ የተሰጠው ሥልጣንና ተግባር እንደተጠበቀ ቢሆንም በጽሕፈት ቤት ደረጃ ከጉዳዩ ጋር የተያያዙ ውሳኔዎችን ለመወሰን የማይችልባቸው ሁኔታዎች እንደነበሩ ሲነገር ቆይቷል፡፡       

የዓለም አቀፉ የፀረ አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ (ዋዳ) ችግሩን መቆጣጠር ይቻል ዘንድ አስገዳጅ መመርያና ደንቦችን ቢያወጣም፣ ስፖርተኞች ከሌሎች ልቆና መጥቆ አሸናፊ ሆኖ ለመገኘት ከተፈጥሯዊ ክህሎት ባሻገር ተጨማሪ አበረታች ቅመሞችን ለመጠቀም የሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች መልክና ቅርፃቸውን እየተቀያየረ ለቁጥጥርና ክትትል አስቸጋሪ አድርጎት ስለመቆየቱ ጭምር ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ በዚህም አትሌቶች ከተፈጥሮዊ ክህሎታቸው ባሻገር በሳይንሳዊ ሥልጠና ተዘርግቶ በሚሠራ ብርቱ ጥረት የሚገኘው የላብ ዋጋ ላይ ተፅዕኖው የበረታ እንዲሆን ማድረጉ ተነግሯል፡፡

በዘርፉ የቀረቡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣ በችግሩ የሚጠረጠሩ ስፖርተኞች በተለይም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዓለም ላይ ከመጨመራቸው ባሻገር፣ የአበረታች ቅመሞች ወረርሽኝ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ አገሮች ዘልቆ ገብቷል፡፡ ችግሩ አሁን ላይ ኢትዮጵያ በውጤታማ አትሌቶቿ የስኬት ውሎና ታሪኳ ላይ ጥላሸት ለመቀባት እየተፈታተናት ስለመሆኑ ጭምር የሚናገሩ አልጠፉም፡፡ እንዲያውም ዋዳ ከጥቂት ዓመታት በፊት የችግሩ ክፉኛ ተጠቂ አገሮች ይፋ ካደረጋቸው አምስት አገሮች አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗ አይዘነጋም፡፡

ዶፒንግ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ዋና ማነቆ ከመሆኑ ባሻገር፣ በሌሎችም ስፖርቶች በተለይም በዜጎች ላይ ለጤና፣ ለማኅበራዊ፣ ለኢኮኖሚያዊና ለሥነ ልቦናዊ ችግር ተጋላጭ እያደረጋቸው ስለመምጣቱ ጭምር የሚናገሩ አልጠፉም፡፡

ከዚህም በመነሳት በየደረጃው ከስፖርት አበረታች ቅመሞች ነፃ የሆነ ስፖርት እንዲስፋፋና በትክክለኛው መንገድ ተወዳድረው ውጤታማ የሆኑ ስፖርተኞችን እንዲፈሩ ለማስቻል፣ የተቋቋመውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ አበረታች ቅመሞች ጽሕፈት ቤት ደንቡን በማሻሻል ወደ ባለሥልጣን ከፍ እንዲል መደረጉ ከሰሞኑ ተነግሯል፡፡

ባለሥልጣኑ የፀረ አበረታች ሕጉን ጨምሮ ሕጎችና ደንቦች ጋር የተጣጣመና በየደረጃው ችግሩን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ብሔራዊ የፀረ አበረታች ቅመሞች ፖሊሲ፣ የማስፈጸሚያ ሥርዓትና ስትራቴጅ በማዘጋጀት እንዲተገብር ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡

ባለሥልጣኑ በቀጣይ የሚጠቀምባቸውን ፖሊሲና ስትራቴጂ፣ እንዲሁም የፀረ አበረታች ቅመሞች የሕግ ማዕቅፎች የመጀመርያ ረቂቂ ሰነድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ  መስፍን ቸርነት (አምባሳደር)በአዲስ አበባ አዝማን ሆቴልዳር 23 ቀን 2014 .ም. ውይይት አካሂዷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...

አይ የእኛ ነገር!

የዛሬው ጉዞ ከጀሞ ወደ ፒያሳ ነው፡፡ መንገዱ ለሥራ በሚጣደፉ፣...

የዓለም ኢኮኖሚ መናጋት ለወቅታዊው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ነው?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ባለፈው ማክሰኞ መጋቢት 16...