Friday, December 9, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናበደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በተሾሙ የዞን አመራሮች ምትክ አዳዲስ ሹመቶች ተሰጡ

  በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በተሾሙ የዞን አመራሮች ምትክ አዳዲስ ሹመቶች ተሰጡ

  ቀን:

  የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልልን የመሠረቱ ስድስት ዞኖች፣ በክልል ደረጃ ሹመት ባገኙና በተሰናበቱ አመራሮች ምትክ አዳዲስ ሹመቶችን እየሰጡ ነው፡፡ በዚህም መሠረት የካፋ ዞን፣ የቤንች ሸኮ ዞን፣ እንዲሁም የዳውሮ ዞኖች በሹመት ወደ ክልል በሄዱና በተሰናበቱ አመራሮች ምትክ አዳዲስ ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡

  የቤንች ሸኮ ዞን ምክር ቤት ሰኞ ኅዳር 27 ቀን 2014 ዓ.ም. በሚዛን አማን ከተማ ባደረገው ስብሰባ አቶ ቀበሌ መንገሻ በምክትል አስተዳዳሪነት ክልሉን እንዲመሩ የመረጣቸው ሲሆን፣ ሥልጣናቸውን ከተሰናባቹ አቶ ፍቅሬ አማን ተረክበዋል፡፡

  በተጨማሪም የዞን ምክር ቤቱ አቶ ሳሙኤል አሰፋን ምክትል አስተዳዳሪና የፋይናንስ መምርያ ኃላፊ አድርጎ ሾሟል፡፡

  በተመሳሳይ የካፋ ዞን ምክር ቤት ኅዳር 26 ቀን 2014 ዓ.ም. በቦንጋ ከተማ ባደረገው ስብሰባ አቶ እንደሻው ከበደ የዞኑ አስተዳዳሪ አድርጎ የሾማቸው ሲሆን፣ አቶ አሸብር ኢካሎ ምክትል አስተዳዳሪና የከተማና ኮንስትራክሽን መምርያ ኃላፊ፣ እንዲሁም አቶ ንጉሤ ወልደ ጊዮርጊስን የዞኑ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ አድርጎ ሾሟል፡፡

  የካፋ ዞን አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ በላይ ተሰማ የደቡብ ምዕራብ ክልል ምክር ቤት የመንግሥት ረዳት ተጠሪ ሆነው የአደረጃጀት ዘርፍ እንዲመሩ መሾማቸው ይታወሳል፡፡

  የዳውሮ ዞን ምክር ቤትም ኅዳር 22 ቀን 2014 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ አቶ ምትኩ መኩሪያን በምክትል ርዕሰ መስተዳድርነት ዞኑን እንዲመሩ ሲሾም፣ አቶ ታመነ ተስፋዬን ደግሞ ምክትል አስተዳዳሪና የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት መምርያ ኃላፊ አድርጎ ሾሟል፡፡ የዳውሮ ዞን ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት አቶ ተክሌ በዛብህ በአዲሱ ክልል የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ ሆነው በክልሉ አስተዳዳሪ ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) መሾመዋቸው የሚታወስ ነው፡፡

  ከልዩ ወረዳነት ወደ ዞንነት ያደገው የኮንታ ዞን ረቡዕ ኅዳር 29 ቀን 2014 ዓ.ም. ስብሰባውን እንደሚያደርግና ተመሳሳይ ሹመቶችን እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

  የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ኅዳር 12 ቀን 2014 ዓ.ም. በቦንጋ ከተማ በነበረ ሥነ ሥርዓት በይፋ መመሥረቱ የሚታወስ ሲሆን፣ የተለያዩ የክልል አስፈጻሚና የሕግ ተርጓሚ አካላት ሹመቶች ሰጥቷል፡፡ ቅዳሜ ኅዳር 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ክልሉን በርዕሰ መስተዳድርነት የሚመሩት ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፣ ከ70 በላይ ለሚሆኑ የክልል ቢሮዎች ምክትል ኃላፊነትና የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመው ጭፍጨፋና ሥጋቱ

  ኦሮሚያ ክልል ከቀውስ አዙሪት መላቀቅ ያቃተው ይመስላል፡፡ ከ200 በላይ...

  እናት ባንክ ካፒታሉን ወደ አምስት ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ወሰነ

  መጠባበቂያን ሳይጨምር የባንኩ የተጣራ ትረፍ 182 ሚሊዮን ብር ሆኗል እናት...

  ቡና ባንክ ዓመታዊ ትርፉን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ማሻገር ቻለ

  ቡና ባንክ በ2014 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ የትርፍ ምጣኔውን ለመጀመርያ...