Thursday, December 1, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናበኮምቦልቻና በላሊበላ ኤርፖርቶች ላይ የደረሱ ጉዳቶችን የሚያጠና የባለሙያ ቡድን ሊላክ መሆኑ ተገለጸ

  በኮምቦልቻና በላሊበላ ኤርፖርቶች ላይ የደረሱ ጉዳቶችን የሚያጠና የባለሙያ ቡድን ሊላክ መሆኑ ተገለጸ

  ቀን:

  የሕወሓት ታጣቂዎች ለወራት ተቆጣጥረውት በነበረበት ወቅት መውደሙ የተገለጸውን የላሊበላ አውሮፕላን ማረፊያ፣ እንዲሁም የደረሰበት ጉዳት በይፋ ያልተገለጸውን የኮምቦልቻ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ የደረሱ ውድመቶችን የሚያጠና ቡድን በሁለት ቀናት ውስጥ ወደ ቦታው እንደሚላክ ተገለጸ፡፡

  በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ውስጥ የሚሠሩና ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አንድ የሥራ ኃላፊ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ የአውሮፕላን ማረፊያዎቹ ተመልሰው በአፋጣኝ ወደ ሥራ አንዲገቡ ለማድረግ ከሁለም ዘርፍ  የተውጣጣ የባለሙያ ቡድን በአጭር ቀናት ወስጥ ወደ ቦታው ይላካል፡፡

  ከሐምሌ 28 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ለአራት ወራት ያህል በሕወሓት ታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር የነበረችው የላሊበላ ከተማ፣ በአገር መከላከያ ሠራዊት፣ በአማራ ክልል ልዩ ኃይልና ፋኖ አባላት ተመልሳ በቁጥጥር ሥር የገባቸው ከአንድ ሳምንት በፊት ነበር፡፡

  በተመሳሳይ በሕወሓት ታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር የነበሩት የደሴና የኮምቦልቻ ከተሞች በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በሚመራው የፀጥታ ኃይሎች ጥምረት አማካይነት ነፃ መሆናቸው የተነገረው ሰኞ ኅዳር 27 ቀን 2013 ዓ.ም. ነው፡፡

  የሕወሓት ታጣቂዎች በላሊበላ አውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ማድረሳቸውን መንግሥት ያስታወቀ ሲሆን፣ ከሁለት ቀናት በፊት ከታጣቂዎች ነፃ የሆነችው የኮምቦልቻ ከተማ አውሮፕላን ማራፊያ ላይ ስለደረሰ ጉዳት ግን የተነገረ ነገር የለም፡፡

  በሁለቱ አካባቢዎች የሚላከው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የባለሙያዎች ቡድን ደረሰ የተባለውን ጉዳት አጥንቶ እንደጨረሰ፣ ኤርፖርቶቹ አፋጣኝ ጥገና ተደርጎላቸው ወደ ሥራ እንደሚገቡ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

  ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር) ከጥቂት ቀናት በፊት በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው፣ በመላው ዓለም ከሚገኙ የኢትዮጵያ ወዳጆች ወስጥ አንድ ሚሊዮን ሰዎች ለገና በዓል ወደ አገር እንዲገቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

  ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ጥሪ መሠረት በውጭ አገር የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውን የአውሮፕላን ትኬት እየቆረጡ መሆኑን የገለጹት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ደኤታዋ ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፣ ለሚመጡት እንግዶች የሚያስፈልገውን የትራንስፖርትና ሌሎች አገልግሎቶች በቅናሽ እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

  በዚህም በበርካታ ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት የኢትዮጵያን ገጽታ ለማጠልሸት የተሠራውን ደባ ለመቀልበስ፣ የተለያዩ ዝግጅቶች እያደረግን ነው ብለዋል፡፡

  የኢትዮጵያ አየር መንገድ በታኅሳስ ወር መጨረሻ ለሚከበረው የገና በዓል ወደ አገራቸው ለሚመጡ ኢትዮጵውን፣ የ30 በመቶ የበረራ ትኬት ቅናሽ እንደሚያደርግ ከቀናት በፊት ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...