Friday, December 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናነፃ በወጡ አካባቢዎች ወድመው የነበሩ መሠረተ ልማቶች አገልግሎት መስጠት እየጀመሩ መሆኑ ተገለጸ

ነፃ በወጡ አካባቢዎች ወድመው የነበሩ መሠረተ ልማቶች አገልግሎት መስጠት እየጀመሩ መሆኑ ተገለጸ

ቀን:

  • ደሴና ኮምቦልቻን ጨምሮ በርካታ ቦታዎች በጥምር ኃይሉ ቁጥጥር ሥር ገብተዋል

ከሕወሓት ታጣቂዎች ነፃ በሆኑ አካባቢዎች ተቋርጠው የነበሩ መሠረተ ልማቶች እየተጠገኑ ወደ አገልግሎት እየተመለሱ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ከደብረሲና ጀምሮ ከሕወሓት ወረራ ነፃ በወጡ የሸዋሮቢት፣ አጣየና ከሚሴ ከተሞች መሠረተ ልማቶች እየተጠገኑ እንደሆነና አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ለመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ነፃ በወጡ አካባቢዎች የሚገኙና ተቋርጠው የነበሩ የኤሌክትሪክ መስመሮች፣ የቴሌኮም ኔትወርክ፣ ውኃና ሌሎች የመሠረተ ልማት አገልግሎቶች ጥገና እየተደረገላቸው እንደሆነ አክለው ገልጸዋል፡፡

ከኅዳር 23 ቀን 2014 .. ጀምሮ በተደረገ የመሠረተ ልማት ፍተሻ 34 በሚሆኑ ታወሮች መካከል በሚገኙ ቦታዎች ላይ 50 የመስመሮች መበጣጠስ፣ ሰባት የድምፅና ዳታ ማስተላለፊያ የኦፕቲካል ፋይበር መቆረጥ እንዲሁም 13 ቦታዎች ላይ ደግሞ መስመር ሳይበጠስ መሠረተ ልማቱ ላይ ጉዳት እንደደረሰ ተመላክቷል፡፡

በተመሳሳይ ከገረገራ እስከ ጋሸና የሚገኝ የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር የመጠገን ሥራ እየተከናወነ መሆኑም ተገልጿል፡፡

የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ወደ መደበኛ ሥራቸው እየተመለሱ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው በኮምቦልቻና ደሴ ከተሞች የትራንስፖርት አገልግሎት እንደተጀመረና የውኃ፣ የቴሌኮምና የመብራት አገልግሎት ከቀናት በኋላም እንደሚጀምር አክለው ጠቁመዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመራው የኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች ጥምረት፣ ደሴ ኮምቦልቻ፣ ባቲ፣ ቀርሳ፣ ገርባን፣ ደጋንና ቃሉ ወረዳን ሙሉ በሙሉ ነፃ ማውጣቱን ይፋ ያደረገው ሰኞ ኅዳር 27 ቀን 2014 ዓ.ም. ነበር፡፡

በተመሳሳይ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ኅዳር 28 ቀን 2014 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ ከ50 እስከ 800 የሚደርሱ ሠራተኞችን ቀጥረው ሲያሠሩ በነበሩ ከ32 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ በሕወሓት ታጣቂዎች ጉዳት እንደደረሰበት ተናግረዋል፡፡

በርካቶቹ ድርጅቶች በምግብና ምግብ ነክ፣ ብረታ ብረት፣ በግብርና ምርቶች ማቀነባበርና በጨርቃ ጨርቅ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ሰለመሆናቸውም ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...