Thursday, September 21, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ከ32.5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ግብይት የተፈጸመ በማስመሰል የተቀናበረ የግብር ሥወራ አሻጥር ተደረሰበት

ተዛማጅ ፅሁፎች

ሐሰተኛ የካሽሬጅስተር ደረሰኝ የሚያቀርቡ 400 በላይ ድርጅቶች ተይዘዋል

32.5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ግብይት የተፈጸመ በማስመሰል የተቀናበረ የግብር ሥወራ አሻጥር ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችና የሚጠቀሙበት ካሽሬጅስተር ማሽን ከነመረጃው በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ። 

በሐሰተኛ ማንነት (እውነተኛ ማንነታቸውን በመደበቅ) ያወጡትን የንግድ ፈቃድ ተጠቅመውና አድራሻቸውን ሠውረው ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ 63 ድርጅቶች ላይ 20 የካሽሬጅስተር ማሽን ሰሞኑን በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት ኡሚ አባ ጀማል ለሪፖርተር ገልጸዋል።

በቁጥጥር ሥር ከዋሉት የካሽሬጅስተር ማሽኖች መረጃዎች መሰብሰባቸውን የገለጹት ኃላፊዋበተደረገው ምርመራ 32.5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ግብይት እንደተፈጸመ ተደርጎ ደረሰኝ መቆረጡን ገልጸዋል። 

እነዚህ ድርጅቶች በሐሰተኛ ማንነትና አድራሻቸውን በመደበቅ የንግድ ፈቃድ ያወጡ ቢሆንም በንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

ዋና ተግባራቸው ሕግን ተከትሎ በወጣ የንግድ ፈቃድ የተገኙ የካሽሬጅስተር ማሽኖችን በመጠቀም ለሚታወቁ ግብር ከፋዮች ወይም የንግድ ድርጅቶች ግብይት እንደተፈጸመ በማስመሰል ደረሰኝ ቆርጦ ማቅረብ ዋነኛ ሥራቸው እንደሆነ ተናግረዋል።

ሐሰተኛ ግብይት እንደተፈጸመ በማስመሰል ደረሰኝ የሚቆርጡት ማንነታቸውን የሠወሩ ድርጅቶች ከሚታወቁ የንግድ ድርጅቶች ጋር በቁርኝት የሚሠሩ መሆኑም በምርመራ መለየቱን ገልጸዋል።

የሚታወቅ የንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ግብር ከፋዮች ማንነታቸውን ደብቀው በሥውር ከሚንቀሳቀሱት ድርጅቶችሚቆረጥላቸውን ደረሰኝ በመረከብ ግብይት እንደፈጸሙ በማስመሰል በዋነኝነት ቫት የሚያጭበረብሩ ሲሆንበዓመቱ መጨረሻ ላይ የሚጠበቅባቸው የገቢ ግብር መጠን ዝቅተኛ እንዲሆንም የሚገለገሉበት መሆኑን አስታውቀዋል።

በዚህ የግብር አሻጥር ከሚፈጸመው ታክስ ማጭበርበር በተጨማሪ የሐሰተኛ ግብይት መረጃውን (ደረሰኙን) በማቅረብ የቫት ተመላሽ ጭምር ከመንግሥት እንደሚጠይቁ ተናግረዋል። 

ለሐሰተኛ ግብይቱ የተቆረጠላቸውን ደረሰኝ ተጠቅመው ግብይት እንደፈጸሙ በማስመሰል ከሸማቹ የሰበሰቡትን ቫት በማጣጣት ዜሮ የቫት ሪፖርት ለገቢዎች ሚኒስቴር እንደሚያቀርቡና ከሸማቹ የሰበሰቡትን ቫት ለግላቸው እንደሚያውሉት / ኡሚ አስረድተዋል።

የተጠቀሰው 32.5 ቢሊዮን ብር ግብይት እውነተኛ ግብይት እንዳልሆነነገር ግን ለተጠቀሰው የሐሰተኛ ግብይት መጠን ደረሰኝ የተቆረጠ በመሆኑ ደረሰኙ እጃቸው የገባ ግብር ከፋዮች ታክስ ለማጭበርበር ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ገልጸዋል።

ይህንንም ሲያስረዱ ከተጠቀሰው 32.5 ቢሊዮን ብር ሀሰተኛ ግብይት ውስጥ 15 በመቶ የቫት ምጣኔ ሲሰላ 4.8 ቢሊዮን ብር ቫት ሊጭበረበር እንደሚችል ገልጸዋል።

ለተጠቀሰው መጠን ሀሰተኛ ግብይት የተቆረጡ ደረሰኞች መረጃ በተደረገው ምርመራ የታወቀ በመሆኑ እንዚህን ደረሰኞች ይዘው የሚቀርቡ ወይም በነዚህ ደረሰኞች ተጠቅመው ግብር ያጭበረበሩት ተቋማት በዳግም ኦዲት በቀላሉ ሊገኙ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

እንዲህ ዓይነት ግብይት በአብዛኛው የሚከናወነው ግብይታቸውን በደላላ ወይም በማያምኑት ሰው በሚፈጽሙ ግብር ከፋዮች በመሆኑ የንግድ ባለቤቶች ሳያወቁት ወንጀል ውስጥ ተሳትፈው ራሳቸውን እንዳያገኙ ከወዲሁ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መክረዋል።

ሀሰተኛ ደረሰኝ መጠቀም በግብር አዋጁ ከፍተኛ ቅጣት የሚየስቀጣ ተብለው ከተለዩ የወንጀል ዓይነቶች መካከል አንዱ እንደሆነ የተናገሩት ኃላፊዋ እስከ አስራ አምስት ዓመት እስራት የሚያስቀጣ ወንጀል መሆኑን ጠቁመዋል።

የተገለጸው መጠንን የያዙት ሀሰተኛ ግበይቶች መረጃ የተገኘው 20 የካሽሬጅሰተር ማሽኖች ብቻ እንደሆነም ተናግረዋል። 

ይህ ወንጀል የታክስ ስርዓቱ እራስ ምታት እንደሆነም ገልጸዋል።

2011 ዓም ጀምሮ በተደረገ ክትትል ተመሳሳይ ወንጀል ሲሰሩ የነበሩ 400 በላይ ማንነታቸውን የሰወሩ ድርጅቶች መያዛቸውንም ገልጸዋል።

በተያያዘ ዜና ደረሰኝ ሳይቆርጡ ግብይት የፈጸሙ 199 ሰዎች መያዛቸውን የገለጹ ሲሆን በታክስ አስተዳደር ህጉ መሠረት እያንዳንዳቸው ላይ 50 ሺህ ብር አስተዳደራዊ ቅጣት በድምሩ 199 ሰዎች ላይ 1.6 ቢሊዮን ብር ቅጣት መወሰኑን ገልጸዋል።

 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች