በየዓመቱ በተለያዩ ዋና ዋና ከተሞች የሚከበረው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን፣ ኅዳር 29 ቀን 2014 ዓ.ም. በድሬዳዋ ከተማ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በተገኙበት፣ በተለያዩ መሰናዶዎች ተከብሯል፡፡ ከዋዜማው ጀምሮ የተለያዩ ብሔረሰቦች ባህላዊ ሙዚቃቸውን በሚሌኒየም ፓርክ ለታዳሚያን አቅርበዋል፡፡ የሚቀጥለውን ዓመት የሚያከብረው የሲዳማ ክልል ዋና ከተማ መሆኑ ታውቋል፡፡ ፎቶዎቹ የትርዒቱን ከፊል ገጽታ ያሳያሉ፡፡
- ፎቶ የፌዴሬሽን ምክር ቤት