Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየወረርሽኙ ገዳይ ድምፆች ከዴልታ ቫይረስ ወደ ኦሚክሮን

የወረርሽኙ ገዳይ ድምፆች ከዴልታ ቫይረስ ወደ ኦሚክሮን

ቀን:

ከወራት በፊት አዲሱ የኮቪድ-19 ዝርያ የሆነው ዴልታ በኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ   በመሠራጨቱ ለበርካታ ሰዎች ሕይወት ማለፍ ምክንያት እንደነበረ በወቅቱ ተዘግቦ ነበር፡፡  የጤና ሚኒስቴር ከወረርሽኙ ለመጠበቅ መከላከያ ክትባቱን መከተብ አማራጭ እንደሌለው በተደጋጋሚ ማሳሰቡም አልቀረም፡፡ ይሁን እንጂ በተፈለገው መጠን ኅብረተሰቡ እየተከተበ አለመሆኑን የሚያሳየው የተከታቢው ብዛት ዘጠኝ ሚሊዮን እንኳን አለመድረሱ ነው፡፡

የጤና ባለሙያዎቹ የዴልታ ቫይረስ ሊያደርስ ከሚችለው ጉዳት ለመጠበቅ ኅብረተሰቡን ‹‹ተከተብ›› እያሉ በሚያሳስቡበት አጋጣሚ፣ ሌላ አዲስ ዝርያ በደቡብ አፍሪካ መከሰቱና ወደ ተለያዩ አገሮች መዛመቱ ብዙዎችን አስደንግጧል፡፡

ኦሚክሮን ምን መልክ አለው?

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የዓለም ጤና ድርጅት (ዓጤድ) በደቡብ አፍሪካ የተገኘውን አዲስ የኮቪድ-19 ዝርያ ‹‹ኦሚክሮን›› ብሎ የሰየመው ሲሆን፣ አምስተኛው አሳሳቢ የኮቪድ-19 ዝርያ በማለትም መድቦታል፡፡

ይህ የኦሚክሮን ዝርያ አዲስ የኮቪድ-19 ማዕበል ሊያስከትል ይችላል ሲል ዓጤድ ሥጋቱን የገለጸ ሲሆን፣ ይህን ለመግታት ሁሉም አገሮች የኮቪድ-19 የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባራትን አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስቧል፡፡

ኦሚክሮን ከዚህ ቀደም እንደተከሰቱት የኮቪድ-19 ዝርያ ዓይነቶች በፍጥነት ይዛመት ወይም ከባድ ኢንፌክሽን ያስከትል በጥናት የተረጋገጠ መረጃ የለም፡፡ በደቡብ አፍሪካ የተደረገ የመነሻ ጥናት እንዳመለከተው ግን ወደ ሆስፒታል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል፡፡ ነገር ግን ይህ ከኦሚክሮን ጋር በተያያዘ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በኮቪድ-19 ከመያዝ ጋር ሊሆን ይችላል፡፡

በኦሚክሮን የተያዘ ሰው የሚያሳያቸው ምልክቶች ከዚህ በፊት በኮቪድ-19 ዝርያዎች የተያዙ ያሳዩት ከነበረው የተለየ ስለመሆኑም በጥናት የተረጋገጠ ነገር የለም፡፡ የቫይረሱን ጥንካሬ ለማወቅም ቢሆን ሳምንታት ሊወስድ እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡

የጤና ሚኒስትሯ ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) ባለፈው ሳምንት በሰጡት መግለጫ፣ ኦሚክሮን በተለያዩ አገሮች ቢገኝም ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል ወይስ አልገባም የሚለውን ለመለየት የሚረዳ የማጣራት ሥራ እንደሚከናወን፣ የባህሪውን ሁኔታና ሌሎችም የዝርያውን ተያያዥ ነገሮች ለማወቅ የሚያስችል ጥናት በመከናወን ላይ መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል፡፡

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሰሞኑን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳሳሰበው፣ ይህ አዲስ ዝርያ በኢትዮጵያ ጉዳት እንዳያስከትል ኅብረተሰቡ አሁን ላይ ያሉትን ክትባቶች መከተቡ፣ በኦሚክሮን ሊከሰት የሚችልን የከፋ ሕመምና ሞት የመቀነስ አቅም ይኖረዋል፡፡ በመሆኑም  ያልተከተቡ ሰዎች የኮቪድ-19 ክትባትን በፍጥነት እንዲከተቡ ጥሪ አስተላልፏል፡፡

እንዲሁም ከሌላው ጊዜ በበለጠ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክን በአግባቡና ሁልጊዜ መጠቀም፣ እጅን በሳሙናና በውኃ መታጠብ ወይም ሳኒታይዘር መጠቀም፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ፣ አላስፈላጊ መሰባሰቦችን መቀነስ ይገባልም ብሏል፡፡

መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችየሃይማኖት ተቋማት፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶችን በተጠናከረ ሁኔታ በተቋማቸው ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸውም አስገንዝቧል፡፡

እንደቢሮው ማሳሰቢያ፣ ሕግ አስከባሪ አካላት መመሪያ 803/2014 ማስተግበር፣ እንዲሁም የሚዲያ አካላትና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች የኮቪድ-19 የመከላከል ተግባራትን ኅብረተሰቡንማሳወቅናማንቃት መሥራት ይኖርባቸዋል፡፡

አሁናዊ የኮቪድ-19 መረጃ

የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ በኢትዮጵያ በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እስከ ኅዳር 29 ቀን 2014 ዓ.ም. 372,588 ሲደርስ፣ ሕይወታቸው ያለፈው ደግሞ 6,816 ሆኗል። ከበሽታው ያገገሙት 349,978 ሰዎች ሲሆኑ ቫይረሱ ያለባቸው ደግሞ 15,792 ናቸው፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...