Wednesday, February 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኢሰመኮ በአማራና በአፋር ክልሎች የመብት ጥሰቶችን ለመመርመር ከተመድ ጋር እየመከረ መሆኑን አስታወቀ

ኢሰመኮ በአማራና በአፋር ክልሎች የመብት ጥሰቶችን ለመመርመር ከተመድ ጋር እየመከረ መሆኑን አስታወቀ

ቀን:

በአማራና በአፋር ክልሎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ለመመርመር በዝግጅት ላይ መሆኑን፣ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ፡፡ ምርመራውን ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በጋራ ለማድረግ ንግግር መጀመሩንም ገልጿል፡፡

በአማራና በአፋር ክልሎች ከወራሪ ነፃ በወጡ አካባቢዎች በተደረጉ ቅኝቶች የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀሎች መፈጸማቸውን የሚያሳዩ ምልክቶች መገኘታቸውን ያመለከተው ኮሚሽኑ፣ ጉዳዩን በጠራ መንገድ ለማወቅና ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ ጥልቅ ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ ነው ብሏል፡፡

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ በትግራይ ክልል ከተመድ ጋር በጥምረት ሲያካሂዱት የነበረው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምርመራ ካጠናቀቁበት ጊዜ ጀምሮ፣ በአፋርና በአማራ ክልሎች የምርመራ ሥራውን ቀጥሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት ሁለቱም የመብት ተቋማት የጀመሩት ምክክር ከተጠናቀቀ ኢሰመኮ ከሕወሓት ወረራ ነፃ የወጡ በበርካታ የአማራና የአፋር ክልሎች አካባቢዎች ላይ የጀመረውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምርመራ፣ ከተመድ ጋር በመሆን በጋራ ለማጠናቀቅ ይሠራሉ ብለዋል፡፡

በርካታ አካባቢዎች ከሕወሓት ነፃ በመውጣታቸውና አንፃራዊ መረጋጋት በመታየቱ፣ ምርመራውን በሰፊው ለማካሄድ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር የኢሰመኮ የሴቶችና ሕፃናት ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር መስከረም ገስጥ ተናግረዋል፡፡

‹‹ኮሚሽናችን ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በጋራ ለመሥራት ዝግጁ ነው፤›› ያሉት መስከረም፣ ‹‹አካባቢዎች ነፃ እየወጡ በመሆኑ ለሥራችን አመቺ ነው፤›› በማለት ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ የሁለቱ አካላት የሰብዓዊ መብት ምርመራ መቼ ተጠናቆ ለሕዝብ ይፋ እንደሚሆን ለመገመት አስቸጋሪ መሆኑን ነው መስከረም የጠቆሙት፡፡

በተመሳሳይ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መለሰ በበኩላቸው፣ በሁለቱ አካላት ያለውን ሁኔታ በጋራ ማጥናት አስፈላጊ መሆኑን አስምረውበታል፡፡

‹‹በተናጠል ስንሠራቸው የነበሩ ግምገማዎች አሉ፣ ሥራችንን አላቆምንም፤›› የሚሉት ራኬብ፣ ከዚህ ቀደም ከተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በትግራይን ክልል ማጣራት አድርገው ለሕዝብ ይፋ ማድረጋቸውን አስታውሰዋል፡፡ ሪፖርቱም መንግሥት የተናጠል ተኩስን አቁም እስካደረገበት ጊዜ ድረስ ያለውን፣ እንዲሁም በትግራይ ክልል ውስጥ ብቻ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ያካተተ እንደነበር ጠቅሰዋል፡፡

ሆኖም ግጭቱ መቀጠሉንና አድማሱን ወደ አማራና አፋር ክልሎች ማስፋፋቱን የጠቆሙት ራኬብ፣ የመብት ጥሰቱ በጥልቀት እንሚመረመር ገልጸዋል፡፡

‹‹በተናጠል የክልሎቹን ሁኔታ ስንከታተል ቆይተናል፤›› የሚሉት ራኬብ፣ ‹‹ከተመድ ጋር በጋራ ሥራው ቢከናወን በተሻለ ሁኔታ ውጤታማ ሊሆን ይችላል፡፡ ለዚህ ደግሞ በቅርቡ ያወጣነውና ከዚህ ቀደም የሠራናቸው የጋራ ሪፖርቶች ጥሩ ልምዶችን ሰጥተውናል፤›› ብለዋል፡፡

ከተመድ ጋር በመሆን በአማራና በአፋር ክልሎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ምርመራ ለማድረግ ለተጀመረው ጥረት፣ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንም ሆነ ተመድ በጋራ ለመሥራት ፍላጎት እንዳለቸው ተገልጿል፡፡

ከሰሞኑ የዓለም የሰብዓዊ መብቶች ቀን በኢትዮጵያ ያከበረው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በሦስት ከተሞች የፊልም ፌስቲቫል አካሂዷል፡፡ በሐዋሳ፣ በአዳማና በአዲስ አበባ ከተሞች የቀረበው ፌስቲቫሉ ስለሰብዓዊ መብቶች ግንዛቤ የሚፈጥሩ ፊልሞች የቀረበቡት ነበር፡፡ በሌላ በኩል በዓለም አቀፍ ደረጃ የአንድ ዓመት ሥራ አፈጻጸም ብቃቱ ተገምግሞ ‹A› ደረጃ እንደተሰጠው ተቋሙ በድረ ገጹ ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ ለዚህ ደረጃ ያበቃው ተቋሙ በገለልተኝነት፣ በተዓማኒነትና በሌሎችም የሰብዓዊ መብቶች መገምገሚያ መሥፈርቶች ብቃቱ ተገምግሞ እንደሆነ ተመልክቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የቀረበላቸውን ምክረ ሐሳብ እያደመጡ ነው]

ችግሩ ምን እንደሆነ በትክልል ለይተነዋል ግን ግን ምን? በይፋ መናገር አልነበረብንም። ለምን? ችግሩን...

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትና እንደምታው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የትምህርትን...

ንግድ ባንክ ከቪዛና ማስተር ካርድ ጋር ተደራድሮ ያስጀመረው የገንዘብ ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂና ፋይዳው

ከውጭ ወደ አገር በሕጋዊ መንገድ የሚላክ ገንዘብ (ሬሚታንስ) መጠን...

ይኼ አመላችን የት ያደርሰን ይሆን?

እነሆ ከፒያሳ ወደ ካዛንቺስ። ‹‹አዳም ሆይ በግንባር ወዝ ትበላለህ››...