Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበአዲስ አበባ ከወቅታዊ ሥጋቶች ጋር በተያያዘ ከ200 ሺሕ በላይ ሰዎች ለፀጥታ ጥበቃ...

በአዲስ አበባ ከወቅታዊ ሥጋቶች ጋር በተያያዘ ከ200 ሺሕ በላይ ሰዎች ለፀጥታ ጥበቃ መሰማራታቸው ተገለጸ

ቀን:

በአዲስ አበባ ከተማ ምሽት ላይ እየተደረገ ባለው የፀጥታ ጥበቃ ከ200 ሺሕ በላይ ሰዎች መሰማራታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡ የከተማ አስተደዳሩ በፀጥታ ጥበቃ ለተሰማሩት ነዋሪዎች ሥልጠና መስጠቱን አስታውቆ፣ በከተማዋ የፀጥታ አካላት ሥር መዋቀራቸውንም ገልጿል፡፡

ሪፖርተር ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ዮናስ ዘውዴ፣ በፀጥታ ጥበቃ የተሰማሩ ነዋሪዎች ከተለመደው ወጣ ያለ እንቅስቃሴ ሲኖርና ‹‹ፀጉረ ልውጥ›› ሲመለከቱ ጥቆማ እንደሚያደርሱ፣ እንዲሁም ከፖሊስ ጋር በመቀናጀት ፍተሻ እንደሚያደርጉ ገልጸው፣ ‹‹ጥበቃው ቀጣና፣ ብሎክና መንደር ድረስ ወርዶ ነው እየተካሄደ ያለው፤›› ብለዋል፡፡

‹‹መንደር›› የሚለው አደረጃጀት ስምንት ቤቶችን የሚያካትት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ከሁለት ሺሕ በላይ መንደሮች በከተማዋ ውስጥ መኖራቸው ታውቋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመጀመሪያ ዙር 27,500 በጎ ፈቃደኞችን ማሠልጠኑን፣  ከሁለት ሳምንት በፊትም ደግሞ ተጨማሪ 121 ሺሕ ነዋሪዎችን ለአካባቢ ጥበቃ አሠልጥኖ ማሰማራቱን ገልጿል፡፡ የመጀመሪያውን ዙር ሥልጠና የወሰዱ ነዋሪዎች በአንድ ብሎክ አራት ሆነው መመደባቸውን፣ ተጨማሪ ነዋሪዎች ከሠለጠኑ በኋላ ግን በአንድ ብሎክ ውስጥ የሚመደቡ ሰዎች ቁጥር ወደ ስምንት ማደጉ ታውቋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በከተማ አስተዳደሩ ሥልጠና ከተሰጣቸው በተጨማሪ ሌሎች ነዋሪዎችም በምሽት የፀጥታ ጥበቃ እየተሳተፉ መሆናቸውንና ይኼም ቁጥሩን ከፍ እንዳደረገው ተጠቁሟል፡፡

በተለያዩ ሽፍቶች የሚደረገው ጥበቃ በመጀመሩ፣ ‹‹ነዋሪው ስለአካባቢው ሁኔታ ንቁ ሆኗል፤›› ያሉት አቶ ዮናስ፣ በዚህ ምክንያት በየቦታው ተጥለው የሚገኙ መሣሪያዎች መኖራቸውን አክለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ፣ የአካባቢ የፀጥታ ጥበቃ ከተጀመረ አንስቶ በሕዝብ ሥጋት ተብለው የተለዩ እንደ ቤት ሰብሮ ስርቆትና የመኪና ስርቆት የመሳሰሉ 11 የወንጀል ዓይነቶች መቀነሳቸውን ገልጿል፡፡ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነትላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ለማሳያነት ባለው ሳምንት ቅዳሜ ኅዳር 25 ቀንን የጠቀሱ ሲሆን፣ በዕለቱ ሌሊት ላይ የተፈጸመው አንድ የቅሚያ ወንጀል ብቻ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ከዚህ በፊት በአንድ ሌሊት ከስድስት በላይ የቅሚያ ወንጀልን ጨምሮ ሌሎች ወንጀሎች ይፈጸሙ እንደነበር የተናገሩት ኮማንደር ፋሲካ፣ ‹‹ካለው የሕዝብ ብዛትና ከፍተኛ እንቅስቃሴ አንፃር አንድ ወንጀል ብቻ ተፈጽሞ ሲያድር ማመን ይከብዳል፤›› ብለዋል፡፡

የምሽት የአካባቢ ጥበቃ ከተጀመረ ወዲህ የጦር መሣርያዎች፣ የእጅ ቦምቦችና ጥይቶች ተጥለው መገኘታቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ወንጀል ፈጻሚዎች እጅ ከፍንጅ በነዋሪዎች እየተያዙ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የምሽት የአካባቢ ፀጥታ ጥበቃ በድጋሚ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር በገቡት የኮምቦልቻና የደሴ ከተሞች ሲተገበር ታይቶ የነበረ ሲሆን፣ ጥበቃው የተጀመረው በከተማ ወስጥ የሚደርስ ጥቃትን ለመከላከል ነበር፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም የጥበቃ ሥራውን ተመሳሳይ ዓላማ በመያዝ እያካሄደው እንደሆነ አስታውቋል፡፡

የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊው አቶ ዮናስ፣ የአካባቢ ፀጥታ ጥበቃው አሁን ያለው ‹‹ሥጋት›› ከተቀረፈ በኋላም እንዲቀጥል የሚበረታታ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው፣ ‹‹አካባቢን መጠበቅ ልምድ መሆን አለበት፣ ሁሉም ነገር በፀጥታ አካሉ የሚሸፈን አይደለም፤›› ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...