Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትሰሞነኛው የፕሪሚየር ሊግ አሠልጣኞች ስንብትና የክለቦች ውሳኔ

ሰሞነኛው የፕሪሚየር ሊግ አሠልጣኞች ስንብትና የክለቦች ውሳኔ

ቀን:

በሦስት ምድብ የተደለደለው የከፍተኛ ሊግ ውድድር ተጀምሯል

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ፣ ከዓምና ጀምሮ በአክሲዮን ተደራጅቶ ራሱን በራሱ እያስተዳደረ ይገኛል፡፡ ሊጉ በዚህ መልኩ ዘመናዊውን የእግር ኳስ ዓለምና አሠራር ለመቀላቀል ጥረት እያደረገ መሆኑም ይታወቃል፡፡ ይህም ግብን ለማሳካት ከሚቀመጡ መለኪያዎች አንዱ ቢሆንም፣ ከዚያ ጫፍ ለመድረስ ግን ሁሉም አልጋ በአልጋ ይሆናል ማለት አይደለም፡፡ እንደዘርፉ ሙያተኞች አገላለጽ መውደቅና መነሳት የሒደቱ አካላት ናቸው፡፡ መውደቅና መነሳት የሌለበት ግብ ደግሞ ያን ያህል አርኪ ነው ሊባል እንደማይችል የሚናገሩት ሙያተኞቹ፣ በዚህ ሁሉ ሒደት ግን ትልቁ ነገር ከውድቀት መማር መቻልና የመሻሻያ መንገዶችን ነድፎ ጉዞን ማቃናት መቻል አለበት ይላሉ፡፡

የሰሞኑ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በዋናነት በአመራሮቹ ዘንድ ሲተገበር የሚታየው፣ ከእግር ኳሳዊው ዕይታ በተቃራኒ፣ እግር ኳሳዊን አስተሳሰብ የሚሰጠውን ዕድል የሚነፍግና ‹‹ሰው ቢሄድ ሰው ይመጣል›› የሚል መርህን ነው፡፡ ይህም በጨዋታ ውጤት ላይ ብቻ የተመሠረተ መሆኑ ሰሞነኛው የአሠልጣኞች ስንብትና የክለቦችን ውሳኔ ተመልክቶ መረዳት ይቻላል፡፡

ይህ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ልምምድ ደግሞ በየደረጃው የሚገኙ ክለቦችን ጨምሮ እስከ ብሔራዊ ቡድኑ ዘልቆ በሳይንሳዊ መንገድ የተቀመረ የሥራ ልኬትን ያልተከተሉ ግብታዊ ውሳኔዎችን ማስተናገዱ አልቀረም፡፡ ይህም ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ትልቅ ተግዳሮት ሆኖ የዘለቀ፣ መፍትሔ ሊበጅለት ያልቻለ፣ አሁንም ድረስ ሥር የሰደደ ሕመም ሆኖ መቆየቱ እየተጠቀሰ ይገኛል፡፡

የክለብ አመራሮች ሽንፈት ሲያጋጥማቸው እግር ኳሳዊ የሙያ ትንተና አስቀምጠው፣ ለውጤቱ መበላሸት ተጠያቂውን አካል ማለትም አሠልጣኝ ወይም ተጫዋች በማለት ትክክለኛውን አካሄድ የሚከተሉ ጥቂት ቢኖሩም፣ የአብዛኞቹ ውሳኔ ግን የክለባቸውን ‹‹ስያሜ›› ከማንነት ጋር በማገናኘት የሚተላለፍ እንደሆነ የሚናገሩ አልጠፉም፡፡

ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ባደረጉት የሰባት ሳምንት ጨዋታ ከግማሸ በላይ ክለቦች የአሠልጣኝ ሹም ሽር ማድረጋቸው ሲታወቅ፣ ከመሪው የፋሲል ከተማ ክለብ አሠልጣኝ ጀምሮ በማስጠንቀቂያ ላይ የሚገኙ የዚያኑ ያህል ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለት የክልል ክለቦችን ማለትም በጅማ አባ ጅፋርና በመቀሌ 70 እንደርታ የዋንጫ ባለቤት መሆን የቻሉት አሠልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ፣ ሰሞነኛው የስንብት ዕጣ ከሚገጥማቸው መካከል ስማቸው በጉልህ እየተጠቀሰ ይገኛል፡፡ ከሲዳማ ቡና ጋር ጥሩ አጀማመር እንደነበራቸው ሲነገርላቸው የሰነበቱት አሠልጣኝ ገብረመድኅን፣ ከሰሞኑ በዓምናው ሻምፒዮን ፋሲል ከተማ የደረሰባቸውን 4ለ0 ሽንፈት ተከትሎ የልቀቁልን ግፊቱ ተጠናክሮ መቀጠሉ እየተነገረ ይገኛል፡፡ በዚያው ሳምንት አንጋፋው ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰርቢያዊ አሠልጣኙን ከሽንፈት ጋር አያይዞ ማሰናበቱ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

የአሠልጣኞችን ስንብት አስመልክቶ ምንጮች ለሪፖርተር እንደሚገልጹት ከሆነ፣ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ ፕሪሚየር ሊጉን በ14 ነጥብ በመምራት ላይ የሚገኘው የፋሲል ከተማው ቡድን ዋና አሠልጣኝ ሥዩም ከበደ፣ እንዲሁም በስምንት ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቡናው ካሳዬ አራጌ እና ሌሎችም በርካታ አሠልጣኞች ማስጠንቀቂያ ከደረሳቸው አሠልጣኞች ይጠቀሳሉ፡፡

ከኢትዮጵያ ቡና ቀጥሎ ሰባት ነጥብ በመያዝ ተከታዩን ደረጃ ይዞ የሚገኘው አዳማ ከተማ፣ በተመሳሳይ ሰባት ነጥብ በጎል ክፍያ ተበልጦ ቀጣዩን ደረጃ የያዘው ሐዋሳ ከተማ፣ እንዲሁም የስንብታቸውን ደብዳቤ እየተጠባበቁ የሚገኙት የሲዳማ ቡናው አሠልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ በጎል ክፍያ ተበልጠው በተመሳሳይ ሰባት ነጥብ፣ ሰበታ ከተማ በአራት ነጥብ፣ ሐድያ ሆሳዕና በሦስት ነጥብና አንድም ጨዋታ ሳያሸንፍ በዜሮ ነጥብ የመጨረሻውን ደረጃ ይዞ የሚገኘው ጅማ አባ ጅፋር ናቸው፡፡ 

በሌላ በኩል የከፍተኛ (ሱፐር) ሊግ ክለቦች የጨዋታ መርሐ ግብር ባለፈው ቅዳሜ በሦስት ከተሞች ተጀምሯል፡፡ በሦስት ምድብ ተከፍሎ በ2015 የውድድር ዓመት ወደ ፕሪሚየር ሊግ የሚያድጉትን ሦስት ክለቦችን ለመለየት በሚደረገው የጨዋታ መርሐ ግብር በአጠቃላይ 30 ክለቦች ተሳታፊ መሆናቸው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ይፋ አድርጓል፡፡

እንደ ፌዴሬሽኑ መግለጫ ከሆነ፣ በምድብ አንድ ገላን ከተማ፣ አምቦ ከተማ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ ሻሸመኔ ከተማ፣ ሐላባ ከተማ፣ ጌድዖ ዲላ፣ ባቱ ከተማ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ጋሞ ጨንቻና አርሲ ነገሌ ሲሆኑ፣ በምድብ ሁለት ስልጤ ወራቤ፣ ለገጣፎ ለገዳዲ፣ ቡታጅራ ከተማ፣ ካፋ ቡና፣ ቤንቺ ማጅ ቡና፣ ቡራዩ ከተማ፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ ሰንዳፋ በኬ ከተማ፣ ከምባታ ሽንሽንቾ እና ኮልፌ ቀራኒዮ ሆነዋል፡፡ በምድብ ሦስት ሐምበርቾ ዱራሜ ከተማ፣ ፌዴራል ፖሊስ፣ ኢትዮጵያ መድን፣ ነቀምት ከተማ፣ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፣ የካ ክፍለ ከተማ፣ ደቡብ ፖሊስ፣ ወላይታ ሶዶ ከተማ፣ ጅማ አባ ቡና እና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ መሆናቸው ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

‹‹በየቦታው ምርት እየገዙ የሚያከማቹ ከበርቴ ገበሬዎች ተፈጥረዋል››

አቶ ኡስማን ስሩር፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር...

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...