Sunday, December 4, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ኪንና ባህልኢትዮጵያ የተረከበችው በአሠራር ጥበቡ ልዩ የሆነ ጥንታዊ መስቀሏ

  ኢትዮጵያ የተረከበችው በአሠራር ጥበቡ ልዩ የሆነ ጥንታዊ መስቀሏ

  ቀን:

  ኢትዮጵያ በዓለም ገዝፋ እንድትታይ ከሚያደርጓት ፍሬ ጉዳዮች መካከል መንፈሳዊና ቁሳዊ ባህላዊ ቅርሶቿ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ከነዚህ ተርታ በዋናነት የሚሠለፉት ደግሞ ከጥንታዊቷ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን የፈለቁት ሕያው ሀብቶች ናቸው፡፡

  የመንግሥታቱ ማኅበር የባህል ተቋም ዩኔስኮ፣ በማይዳሰሱም ሆነ በሚዳሰሱ ዘርፎች ይሁንታ ሰጥቷቸው ለዓለም ወካይ ቅርስነት ካበቃቸው መካከል የመስከረም 17ቱ  የእውነተኛው የእግዚእ ኢየሱስ መስቀል የመገኘት (Commemoration feast of the finding of the True Holy Cross of Christ) እና የጥምቀት (ኤጲፋኒያ) ክብረ በዓላት፣ እንዲሁም የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያን ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በእነዚህና በሌሎችም ላይ የሚገኘውና የቤተ ክርስቲያኒቱ ምልክት የሆነው ደግሞ ቅዱስ መስቀሉ ነው፡፡ በክብረ በዓላቱ በተንቀሳቃሽነት በካህናት ወገኑ ከሚያዙት የተለያዩ ዓይነቶች የመስቀል ቅርፆች ባሻገር በተለይ በቋሚነት የሚታየው ባለመስቀል ቅርፁ የቅዱስ ላሊበላው ቤተ ጊዮርጊስ ይነሳል፡፡

  በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ያሉት የተለያዩ ቅርፀ መስቀሎች አገሪቱን በተለያየ መንገድ የሚያስተዋውቁ እንደመሆናቸው ከሌሎች ዕንቁ ቅርሶች ጋርም ተዳብለው በተለያየ መንገድ ከአገር የመውጣት አጋጣሚ በተለያዩ ዘመናት ተፈጥሮባቸዋል፡፡ ከጥንት እስከ አሁን በተለያዩ ዘመናት እንደታየው በሕጋዊነት ለተለያዩ ዓላማዎች ከሚወጡት ይልቅ በሕገ ወጥ መንገድ ከዝርፊያ እስከ ስርቆት የሚወጡት የትዬለሌ ናቸው፡፡ የሩቁን ዘመን ትተን የ19ኛውን ምዕት ዓመቱን በእንግሊዞች የተፈጸመው የመቅደላ ቅርሶች ዝርፊያ አንዱ ማሳያ ነው፡፡

  እነዚህን ቅርሶች ለማስመለስ የተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች ከአፍሮሜት ጀምሮ ሲጥሩ ቆይተዋል፡፡ የተወሰኑትንም ቅርሶች አስመልሰዋል፡፡ አሁንም በተለያዩ መንገዶች ይህንኑ ጥረት ቀጥለዋል፡፡ ከእነዚህም አንዱ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃና አስመላሽ ኮሚቴ ነው፡፡ ይኸው ኮሚቴ በአሜሪካ በተለያዩ ግዛቶች ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበር በተለያየ የታሪክ ዘመን  በሕገ ወጥ መንገድ የወጡ ቅርሶች ወደ አገር እንዲመለሱ እየጣረ ይገኛል፡፡

  ከሰሞኑ በአሠራር ጥበቡ ልዩ የሆነውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገልገያ የነበረና በሕገ ወጥ መንገድ ወጥቶ የነበረ ከመዳብ የተሠራ መስቀል ወደ አገር እንዲመለስ አድርጓል፡፡ ቅዱስ መስቀሉ ግሪክ አሜሪካዊ ከሆነው ቀራፂ፣ ሠዓሊና የሥዕል መምህር ቶማስ ዜናኪስ በራሱ ተነሳሽነት ለሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃና አስመላሽ ኮሚቴ መስቀሉን ማስረከቡን የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን (ቅጥጥባ) አስታውቋል፡፡

  የተሠራበት ዘመን ያልተገለጸው የመዳብ መስቀሉታኅሣሥ 6 ቀን 2014 .. በተወካይነት ለቅጥጥባ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው (ረዳት ፕሮፌሰር) ያስረከቡት የኮሚቴው አባል ዮሐንስ ዘለቀ (/ር) ናቸው፡፡

  በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ቅርሶች ጥበቃና አስመላሽ ኮሚቴ ዓብይ ኮሚቴ አባሉ አሉላ ፓንክረስት (ዶ/ር)፣ ‹‹በኢትዮጵያ ጥናት ስብስብ ውስጥ እስካሁን ድረስ ይህን የሚመስል መስቀል አለመኖሩን››  መናገራቸውን ቅጥጥባ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ገልጿል፡፡

  በአገር ውስጥ በአሜሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ የቅርስ ጥበቃና አስመላሽ ኮሚቴ መስቀሉን ለማስመለስ ያደረጉትን የጋራ ጥረትና ሚስተር ቶማስ ዜናኪስ በግል ገንዘባቸው ገዝተው፣ ይህን ውድ ቅርስ በማስረከባቸው ያወደሱት የቅጥጥባ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አበባው አያሌው፣ ባለሥልጣኑ ቅርሶችን የመንከባከብና የመጠበቅ ብቻ ሳይሆን ቅርሶች ለሕዝብ እንዲታዩና እንዲተዋወቁ ኃላፊነት ጭምር የተሰጠው አካል ስለሆነ፣ ከውጭ የተመለሱ ቅርሶችን በቅርቡ ለማኅበረሰቡና ለጎብኚ ይቀርባሉ ብለዋል፡፡

  ‹‹ከኢትዮጵያ በሕገወጥ መንገድ የወጡ ቅርሶች ብዛትና የወጡበት ዘመን አጥንተን አልዘለቅንም፤›› ያሉት ከአሜሪካ የኢትዮጵያ የቅርስ ጥበቃና አስመላሽ ኮሚቴ የተወከሉትና መስቀሉን ያስረከቡት ዮሐንስ ዘለቀ (ዶ/ር) ናቸው፡፡  አሁን የተመለሰው መስቀል ከሚታወቁት ለየት ያለና በብዛት እንደማይገኝ የገለጹት ባለሙያው በሒደት የተለያዩ የጥናት ተቋማት በእንደነዚህ ዓይነት ቅርሶች ላይ የተለያዩ ጥናቶች ሊደረግባቸው እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

  ባለሥልጣኑ ስለተመለሰው መስቀል የታሪክ ዘመንና ልዩ የሆነ የአሠራር ጥበብ በሌላ ጊዜ መረጃዎችን አጠናቅሮ እንደሚገልጽ አመልክቷል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ዳግም ነፍስ የዘራው የተማሪዎች ማርች ባንድ

  የሙያው ፍቅር ያደረባቸው ገና በልጅነታቸው ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመርያ፣ ለቀለም...

  በስንደዶና ሰበዝ የተቃኘው ጥበብ

  በአንዋር አባቢ ተወልዳ ያደገችው መሀል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ነው፡፡...

  አዲስ ጥረት የሚጠይቀው  ኤችአይቪ  ኤድስን  የመግታት  ንቅናቄ

  ‹‹ኤችአይቪ በመላው ዓለም  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ዋነኛ የሕዝብ...

  የኅትመት ብርሃን ያየው ‹‹የቃቄ ወርድዎት›› ቴአትር

  ከአራት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ይታይ...