Sunday, June 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊ  የወደሙ የጤና ተቋማትን ለማቋቋም ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ

  የወደሙ የጤና ተቋማትን ለማቋቋም ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ

ቀን:

የጤና ሚኒስቴር በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጀው ሕወሓት፣ በወረራ ይዟቸው በነበሩ አካባቢዎች ከፍተኛ ውድመት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት ለማቋቋምና መልሶ ሥራ ለማስጀመር የሚያስችል ሁሉን አቀፍ የድጋፍ ጥሪ አቀረበ፡፡

በጤና ተቋማት ላይ በተከሰተው መጠነ ሰፊ ውድመት ምክንያት በርካታ ወገኖች አገልግሎት የሚያገኙበት በከፊልና ሙሉ ለሙሉ ተስተጓጉሏል፡፡ በሌላም በኩል ግጭቱ ከተከሰተባቸው አቅራቢያ አገልግሎት የሚሰጡ ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች እንዲጨናነቁና መደበኛ ከሆነው አቅማቸው በላይ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረጉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡  

በመሆኑም ለኅብረሰተሰቡ ቀዳሚነት ያለው አገልግሎት መስጠት እንዲያስችልና አገልግሎቱን ወደ ነበረበት ለመመለስ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆችን ያሳተፈ የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ጥሪ ማድረግና የመልሶ ማቋቋሚያ ሀብት ማሰባሰብ እጅጉን አስፈላጊ ሆኖ እንደተገኘ በታኅሣሥ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. መግለጫው ገልጿል፡፡

ለዚህ አደጋ ምላሽ ለመስጠት እንዲያግዝ ሁሉን አቀፍ ከግጭት ጋር የተያያዘ ድንገተኛ አደጋ የጤና ምላሽ ሥርዓት ተቋቁሞ፣ ዘርፈ ብዙ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ ያመለከተው ሚኒስቴሩ፣ ከተግባራቱም መካከል የመጀመሪያና በአሁኑ ወቅት እየተሠራበት ያለው የተዘረፉና ውድመት የደረሰባቸው ጤና ተቋማት በአገር አቀፍ ደረጃ ካሉ የተለያዩ መንግሥት ተቋማት ጋር በመጣመር መልሶ ለማቋቋምና ሥራ ለማስጀመር እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጿል፡፡

በግጭቱ አካባቢ ፈጣን ዳሰሳ ማካሄዱን ሚኒስቴሩ ጠቁሞ፣ የወደሙትን የጤና ተቋማት መልሶ ለማቋቋምና ሥራ ለማስጀመር እጅግ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ የዳሰሳው ግኝት ማመላከቱን አስረድቷል፡፡

ይህንን ሀብት ለማሰባሰብና ድጋፉን ለማስተባበር የጤና ሚኒስቴር የባለሙያ ቡድን ያቋቋመ ሲሆን፣ በግለሰብም ሆነ በቡድን ድጋፍ ማድረግ ለሚፈልጉ ሁሉ ሚኒስቴሩ አስፈላጊ መረጃና ትብብር ለመስጠት ዝግጁ መሆኑንም ጠቁሟል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ በድረ ገጽ https://www.moh gov.et/site/donations መጠቀም፣ እንደሚቻልም አመልክቷል፡፡

ስለዚህም በአገር ውስጥ ሆነ ከአገር ውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን፣ የኢትዮጵያ ወዳጆች፣ የግሉ ዘርፍ፣ ለጋሽና አጋር ድርጅቶች፣ ሲቪክና የጤና ማኅበራት፣ እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት የወደሙ የጤና ተቋማትን ለማቋቋምና ሥራ ለማስጀመር ሁሉንም ዓይነት ድጋፍ እንዲያደርጉ ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የውድመቱ ገጽታ

ውድመት ከደረሰባቸው ተቋማት መካከል የደሴና የኮምቦልቻ ሆስፒታሎች ይገኙበታል፡፡ የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተኝቶና የፅኑ ሕክምና፣ የአነስተኛና የከፍተኛ ቀዶ ሕክምና ክፍሎች የነበሩት ሲሆን በብዙ ሚሊዮን ብር የተገዙ የትንፋሽ መስጫ (ቬንትሌተሮች) እና አንስቴዢያ ማሽኖች ተዘርፈዋል፡፡ ቀሪዎቹ ደግሞ ሙሉ በሙሉ በመውደማቸው በአሁኑ ወቅት ሆስፒታሉ አገልግሎት መስጠት በማይችልበት ደረጃ ላይ መገኙቱ ተጠቁሟል፡፡

ሆስፒታሉ የ80 ዓመት ታሪክ ያለውና ለትግራይና ለአፋር አጎራባች ክልሎች ጭምር አገልግሎት ይሰጥ የነበረ ሲሆን፣ በዓመት በአጠቃላይ ከ450 ሺሕ በላይ ሕዝብ ይጠቀምበት እንደነበርም ነው የተገለጸው፡፡

ተመሳሳይ ውድመትና ወረራ የተፈጸመበት፣ በደቡብ ወሎ ዞን የሚገኘው የኮምቦልቻ አጠቃላይ ሆስፒታል በ200 አልጋዎች አገልግሎት የሚሰጥ ነበር፡፡

ከኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የደቡብ ወሎ ክልል ቅርንጫፎች መካከል አንዱ የሆነው የደሴ ቅርንጫፍም፣ በወራሪው የሕወሓት ቡድን ዝርፊያና ጉዳት ደርሶበታል፡፡ የጥፋት ቡድኑ መድኃኒቶችንና ሌሎች የሕክምና ግብዓቶች የተቻለውን ያህል የዘረፈ ሲሆን የመሠረተ ልማት አውታሮች ላይ ከፍተኛ ውድመት መድረሱም ተገልጿል፡፡

ቅርንጫፉ ለ27 ሆስፒታሎች፣ ለ303 ጤና ጣቢያዎች፣ ለ60 ወረዳዎች እንዲሁም ከሕግ ማስከበር እስከ የህልውና ዘመቻው ድረስ በከፍተኛ ደረጃ የመድኃኒትና ሌሎች የሕክምና ግብዓት በማቅረብ አገልግሎት እየሰጠ እንደነበር ሚኒስቴሩ አመልክቶ፣ በከፍተኛ ሙዓለንዋይ የተገነባ ግዙፍ የእናቶችና የሕፃናት ክትባት ግብዓት ማከማቻ፣ የማቀዝቀዣ ሰንሰለትና ዋና መጋዘኖችን፣ እንዲሁም ቢሮዎችን፣ የማከማቻ መሠረት ልማት፣ ፎርክሊፍቶች፣ የደኅንነት መቆጣጠሪያና ሥርዓቶችን፣ የቢሮ መሣሪያዎትና ሌሎች ንብረቶች ማውደሙም ታውቋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...