Saturday, April 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኮንፈረንስ በተያዘለት ጊዜ እንዲካሄድ ከአገሮች ጋር እየመከረ መሆኑን መንግሥት...

ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኮንፈረንስ በተያዘለት ጊዜ እንዲካሄድ ከአገሮች ጋር እየመከረ መሆኑን መንግሥት ገለጸ

ቀን:

በመጭው ሰኔ 2014 ዓ.ም. በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውንና በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የሚጠበቀውን ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ልማት ኮንፈረንስ በተያዘለት ጊዜ ለማካሄድ፣ መንግሥት ከአፍሪካ አገሮችና ከዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኅብረት የበላይ ኃላፊዎች ጋር እየመከረ መሆኑን ገለጸ፡፡

በየአራት ዓመቱ የሚካሄደው የዓለም አቀፍ የቴሌኮም ልማት ጉባዔ ለስምንተኛ ጊዜ፣ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ እንድታስተናግድ የተመረጠችው እ.ኤ.አ በ2019 ነበር፡፡

በኮንፈረንሱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ኤጄንሲ የሆነው ዓለም አቀፉ የቴሌኮም ኅብረት፣ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በመተባበበር በሚያዘጋጀው ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ፣ ከ2,000 በላይ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ሚኒስትሮች፣ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢና ተቆጣጣሪ ድርጅቶች እንደሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ባልቻ ሬባ (ኢንጂነር) ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ጦርት ሰበብ በማድረግ ኮንፈረንሱ አንዲቋረጥ በኢትዮጵያ እንዳይካሄድ የሚፈልጉ አንዳንድ የምዕራባውያን የድርጅቱ አባል አገሮች ግፊት እያደረጉ መሆናቸውን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ (አምባሳደር) ታኅሳስ 5 ቀን 2014 ዓ.ም. በሰጡት ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

የተወሰኑ የምዕራባውያን ዓለም አቀፉ የቴሌኮም ኅብረት አባል አገሮች ኢትዮጵያ በጦርነት ውስጥ እንደሆነችና አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ መሆኗን በመጥቀስ በሚያወጡት የፀጥታ ሥጋት፣ ኮንፈረንሱን በኢትዮጵያ ለማዘጋጀት የቀረቡ ጥርጣሬዎች ስለመኖራቸው ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

የፀጥታ ሥጋት ማሳሰቢያውን ተከትሎ ለኮንፈረንሱ ዝግጅት ወደ አዲስ አበባ የሚመላለሱ የኅብረቱ ተወካዮች በቦታው ተገኝተው፣ በኢትዮጵያ ከተቋቋመው ኮሚቴ ጋር ለመነጋገር አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል እየገለጹ ስለመሆኑ አክለው ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ኮንፈረንሱን ለማዘጋጀት ያላትን ቅድመ ዝግጅት እ.ኤ.አ በ2019 እና በ2021 የኅብረቱ የዳሰሳ ቡድን አዲስ አበባ በመምጣት ስለማረጋገጡ፣ እንዲሁም አዲስ አበባ ኮንፈረንሱን ለማዘጋጀት ያላትን ሁለገብ ዝግጅት ተመልክተው እንደሄዱ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የተወሰኑ አገሮች ለአባል አገሮች ምክር ቤት ሥጋታቸውን እየገለጹ ስለመሆኑ ከኅብረቱ ዋና ጸሐፊ በኩል መረጃ እንደረሳቸው የጠቀሱት ባልቻ (ኢንጂነር)፣ ኮንፈረንሱ በኢትዮጵያ ይደረግ ወይም አይደረግ የሚባል ውሳኔ ላይ ባይደረስም በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ኮንፈረንሱን ለማዘጋጀት በሙሉ አቅም ዝግጅት እያደረግን ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በየዓመቱ የአፍሪካ አገሮች መሪዎች የሚገኙበትን አኅጉራዊ የመሪዎች ስብሰባ ያለ ምንም ሥጋት እንደምታዘጋጅ በመግለጽ፣ አሁን የሚፈራው የፀጥታ ሥጋትም አንድም ጦርነቱ ከአዲስ አበባ ርቆ እየተካሄደ በመሆኑ፣ ሌላው ኮንፈረንሱ በሚካሄድበት የሰኔ ወር ጦርነቱ እንደሚጠናቀቅና የሰላሙ ሁኔታ አስተማማኝ እንደሚሆን ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ባልተገባ ሁኔታ የተዛባ መረጃ በመስጠታቸው እንጂ እንደሚባለው የሚያሠጋ ሁኔታ አለመኖሩን የገለጹት ባልቻ (ኢንጂነር) የኢትዮጵያ መንግሥት ከኅብረቱ ዋና ዳይሬክተር፣ ከቴሌኮም ልማት ዳይሬክተርና ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ጋር በመወያየት ኮንፈረንሱን የሚያስተጓጉል ሁኔታ እንደሌለና አሁን በመሬት ላይ የሚታዩ ሥጋቶች አለመኖራቸውን መነጋገራቸውን አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተወግዘው የነበሩ ሦስቱ ሊቀጳጳሳትና 20 ተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ውግዘት ተነሳ

_ቀሪዎቹ ሦስት ህገወጥ ተሿሚዎች የመጨረሻ እድል ተሰጥቷቸዋል ​ ጥር 14...

በሕወሓት አመራሮች ላይ ተመስርቶና በሂደት ላይ የነበረው የወንጀል ክስ ተቋረጠ

በቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤ,(ዶ/ር)ና ባለፈው ሳምንት በተሾሙት...

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...