Monday, March 20, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናእየተቋቋመ ያለውን “አገራዊ ምክክር ኮሚሽን” ያለ መከሰስ መብት የሚሰጣቸው ኮሚሽነሮች እንደሚመሩት ተነገረ

እየተቋቋመ ያለውን “አገራዊ ምክክር ኮሚሽን” ያለ መከሰስ መብት የሚሰጣቸው ኮሚሽነሮች እንደሚመሩት ተነገረ

ቀን:

በኢትዮጵያ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት አገራዊ ምክክር መድረክ እንዲመራና እንዲያሳልጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በመቋቋም ላይ የሚገኘው አገራዊ ምክክር ኮሚሽንን፣ 11 ያለ መከሰስ መብት የሚሰጣቸው ኮሚሽነሮች እንደሚመሩት ተገለጸ፡፡

ከፖለቲካ ወገንተኝነት፣ ከማንኛውም የመንግሥት ወይም ሌላ አካል ተፅዕኖ ነፃ የሆነ ራሱን የቻለ የሕግ ሰውነት ያለው አካል ሆኖ እንደሚቋቋም የተነገረለት የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተቋም ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሐሙስ ታኅሳስ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. ውይይት አድርጓል፡፡

በረቂቅ አዋጁ እንደተገለጸው ለኮሚሽኖቹ የተሰጠው ያለ መከሰስ መብት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤካልተነሳ፣ ወይም እጅ ከፍንጅ ካልተያዙ በስተቀር በኮሚሽነርነት በሚያገለግሉበት ወቅት በወንጀል ያለ መከሰስ መብት አላቸው፡፡

በቅርቡ እንደሚቋቋም ለሚጠበቀው ኮሚሽን ከሕዝብ፣ ከፖለቲካ ድርጅቶችና ከሲቪል ማኅበራት ኮሚሽነር ሊሆኑ የሚችሉ ግለሰቦች ተጠቁመው በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው የሚሾሙ ስለመሆናቸው ተደንግጓል፡፡

የኮሚሽኑ የሥራ ዘመን ለሦስት ዓመታት ሲሆን፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሊራዘም እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

የኮሚሽኑ መቋቋም አስፈላጊነት በዋነኝነት የተለያዩ የፖለቲካና የሳብ መሪዎች እንዲሁም የኅብረተሰብ ክፍሎች መካከል እጅግ መሠረታዊ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ የሆነ የሳብ ልዩነት፣ አለመግባባትና ተቃርኖ የሚታይ በመሆኑ አለመግባባቱንና ተቃርኖውን ለማርገብና ለመፍታት ሰፋፊ አገራዊ የሕዝብ ምክክሮችን አካታች በሆነ መንገድ በማካሄድ አገራዊ መግባባት መፍጠር አስፈላጊ መሆኑ በሰነዱ ተመላክል።

በአገራዊ ምክክሩ ተወያዮችንና የውይይት አጀንዳዎችን ከመምረጥ ጀምሮ፣ በውይይቶቹ የሚገኙ ምክረ ሐሳቦችን በተግባር ላይ ለማዋል የሚያስችል ግልጽና ተጨባጭ የሆነ ዕቅድ መዘጋጀቱን፣ ማረጋገጥና አስፈላጊውን ዕገዛ የማድረግ ኃላፊነቶች ለኮሚሽኑ ተሰጥተውታል፡፡

በሌላ በኩል ለኮሚሽኑ ከተሰጡት ኃላፊነቶች ውስጥ በልሂቃኖች መካከል አገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ያሉትን ልዩነቶች በጥናት፣ በሕዝባዊ ውይይቶች፣ ወይም በሌሎች አግባብነት ባላቸው መንገዶች በመጠቀም፣ በአገራዊ የምክክር ጉባዔ ላይ የሚሳተፉ አካላትን ግልጽ በሆኑ መሥፈርቶችና የአሠራር ሥርዓት መሠረት ይለያል፣ በምክክሮች ላይ እንዲሳተፉም ያደርጋል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም የአገራዊ ምክክር ጉባዔ አጀንዳዎችን፣ የምክክሮቹን ሒደት፣ በምክክሮቹ የተገኙ ምክረ ሐሳቦችን፣ እንዲሁም ምክረ ሐሳቦቹ በተግባር ላይ ሊውሉ የሚችሉበትን ሥልት የሚገልጽ ዝርዝር ሪፖርት በማዘጋጀት ለመንግሥት ያቀርባል፡፡

ኮሚሽኑ እንደሚካሄዱ የታቀዱትን አገራዊ ምክክሮች አካታች፣ ብቃት ባለውና ገለልተኛ በሆነ አካል የሚመሩ፣ የአለመግባባት መንስዔዎችን በትክክል በሚዳስ አጀንዳ የሚያተኩሩ፣ ግልጽ በሆነ የአሠራር ሥርዓት የሚመሩና የምክክሮቹን ውጤቶችን ለማስፈጸም የሚያስችል ዕቅድ ያላቸው እንዲሆኑ የሚሠራ ስለመሆኑ ለፓርላማው የቀረበው ሰነድ ያስረዳል፡፡

የምክር ቤት አባላት የሚመረጡት ኮሚሽነሮች ከአሻጥርና ከወገንተኝነት የፀዱ መሆናቸው ተረጋግጦ እንዲመረጡ አሳስበዋል፡፡

ለአብነትም አንድ የምክር ቤት አባል በብጥስጣሽ አጀንዳዎች የማይሳሳቱ፣ አገርን የሚያስቀድሙ፣ አፍራሽ ያልሆኑና በውሳኔያቸው አገርን መገንባት የሚችሉ አካላት እንዲሳተፉበት ጠይቀዋል፡፡

በፉክክር ሳይሆን በመቻቻል፣ በትብብርና በመከባበር ላይ የተመሠረተ የፖለቲካ ባህልና ሕዝብን ማስቀደምና አገርን መገንባት ላይ የሚያተኩሩ ከመሆንም በላይ፣ ኢትዮጵያ የራሷን ችግር በራሷ መፍታት እንደምትችል ማሳየት የሚችሉ አካላት እንዲሳተፉበት የጠየቁት ደግሞ አቶ አሽኔ አስቴ የተባሉ የምክር ቤት አባል ናቸው፡፡

መሠረት ዘለዓለም (ዶ/ር) የተባሉ የምክር ቤት አባል ከውጭ ከሚመጡ ልምዶች በበለጠ፣ አገር ውስጥ ያለውን ልምድ ዘወር ብሎ መመልከት አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል፡፡

ፓርላማው በረቂቅ አዋጁ ላይ ተወያይቶ ለሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለውይይት መርቶቷል፡፡

 

 

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ዜጎች የተፈተኑበት የኑሮ ውድነት

በኢትዮጵያ በየጊዜው እየተባባሰ የመጣው የኑሮ ውድነት የበርካታ ዜጎችን አቅም...

በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚደረጉ ድጋፎች ዘላቂነት እንዲኖራቸው ተጠየቀ

በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚደረጉ ድጋፎች ዘላቂነት እንዲኖራቸውና በተቀናጀ መልኩ...

ወደ ኋላ የቀረው የሠራተኞች ደኅንነት አጠባበቅ

በአበበ ፍቅር ለሠራተኞች የሚሰጠው የደኅንነት ትኩረት አናሳ በመሆኑ በርካታ ዜጎች...