Wednesday, December 6, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትአትሌቲክስ የአገር ውስጥ ውድድር ዛሬ ይጀምራል

አትሌቲክስ የአገር ውስጥ ውድድር ዛሬ ይጀምራል

ቀን:

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በ2014 ዓ.ም. ሊከናወኑ መረሐ ግብር ከወጣላቸው የአገር ውስጥ ውድድሮች መካከል፣ አንደኛው ከዛሬ ረቡዕ ታኅሳስ 13 እስከ 17  ቀን 2014 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ይከናወናል፡፡

ሰኞ ታኅሳስ 11 ቀን 2014 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ የ3,000 መሰናክል፣ የአጭር ርቀት፣ መካከለኛ ርቀት፣ የሜዳ ተግባራትና የዕርምጃ ውድድሮች እንደሚከናወኑ አስታወቋል፡፡

ለአምስት ቀናት በሚከናወነው ሻምፒዮና ላይ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ዕውቅና የተሰጣቸው ክለቦች፣ ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች፣ እንዲሁም የአትሌቲክስ ማሠልጠኛ ማዕከላት አትሌቶች ይሳተፋሉ፡፡ በርቀቱ ላይ ለሚካፈሉ አትሌቶች የውድድር ዕድል ለመፍጠርና ተተኪዎችን ለማፍራት ግቡ ያደረገ እንደሆነ ያብራራው ፌዴሬሽኑ፣ በርካታ አትሌቶች እንደሚጠበቁም አስረድቷል፡፡

በውድድሩ ሁለት ክልሎች፣ አንድ ከተማ አስተዳደር፣ 22 ክለቦችና ተቋማት ተሳታፊ ሲሆኑ፣ 282 ሴቶችና 412 ወንዶች በድምሩ 707 አትሌቶች እንደሚካፈሉ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ አስታወቋል፡፡ በእያንዳንዱ የውድድር ተግባር ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ለሚወጡ አትሌቶች በሁለቱም ፆታ የወርቅ፣ የብርና የነሐስ ሜዳልያ፣ እንዲሁም የገንዘብ ሽልማት ተዘጋጅቷል፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ለሽልማትና ለውድድር ማካሄጃ 522,600 ብር መመደቡንም ጠቁሟል፡፡ ቀድሞ በአዲስ አበባ ሲከናወን የነበረው ውድድሩ ስታዲየሙ ዕድሳት ላይ ስለሆነ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዴሚ ይከናወናል፡፡

በረዥም ርቀት የሚታወቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ በአጭር ርቀት ውጤታማ ጊዜን ማሳልፍ አልቻለም፡፡ በርካታ አትሌቶቹም በረዥም ርቀት ላይ ተወስነው ተሳትፎ ሲያደርጉ ይስተዋላል፡፡

በአንፃሩ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በአጭርና መካከለኛ ርቀቶች ላይ ውጤት የሚያመጡ አትሌቶች እየተስተዋሉ ነው፡፡ ለዚህም በቶኪዮ ኦሊምፒክ በ3,000 ሜትር መሰናከል ርቀት በለሜቻ ግርማ የተገኘው የብር ሜዳልያ ማሳያ ነው፡፡ ከዚያም ባሻገር  በተለያዩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ በመካከለኛ ርቀት ላይ ተሳትፎ እያደረጉ ያሉ ተተኪ አትሌቶችን መመልከት እየተለመደ ከመጣ ሰነባብቷል፡፡

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. ከሜክሲኮ ኦሊምፒክ ጀምሮ በ200፣ በ400፣ በ800 እና በ1,500 ሜትር ርቀቶች ላይ ተሳትፎ ስታደርግ ቆይታለች፡፡ በዚህም ንጉሤ ጋቻሞ፣ ተገኔ በዛብህ፣ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ፣ አማን ወጤና መሐመድ አማን በመካከለኛው ርቀት ስማቸው የሚጠቀስ አትሌቶች ናቸው፡፡ በሴቶች ፈትያ ሐሰን፣ አትክልቲ ውብሸት፣ ትዕግሥት ታማኙ፣ ገንዘቤ ዲባባ፣ እንዲሁም ሀብታም ዓለሙን የመሳሰሉ አትሌቶች በመካከለኛ ርቀት ውስጥ ስማቸው በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...