Thursday, November 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር በአቶ እስክንድር ነጋ ጉዳይ ፍርድ ቤት...

የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር በአቶ እስክንድር ነጋ ጉዳይ ፍርድ ቤት ተጠሩ

ቀን:

አቶ እስክንድር ነጋ ታስሮ በሚገኝበት ማረሚያ ቤት በሌላ ታራሚ ደርሶብኛል ስላለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አጣርቶ ሪፖርት እንዲያደርግ ፍርድ ቤት ሰጥቶ የነበረውን ትዕዛዝ ተግባራዊ ባለማድረጉ ምክንያት  ለምን እንዳላጣራ ቀርቦ እንዲያብራራ ተጠራ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ አቶ እስክንድር ነጋ ከአገር ውጭ የሚገኙ ቤተሰቦቹን በሳምንት አንድ ጊዜ በስልክ እንዲያገኛቸው ፍርድ ቤት የሰጠውን ትዕዛዝ  የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ትዕዛዙን ባለመፈጸሙ፣ ለምን እንዳልፈጸመ የማረሚያ ቤቱ የእስረኞች ኃላፊ ቀርበው እንዲያስረዱም ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

ፍርድ ቤቱ ትዕዛዙን የሰጠው አቶ እስክንድር ቀደም ባለው የችሎት ሒደት ለፍርድ ቤቱ አቅርቧቸው በነበሩት አቤቱታዎች፣ ፍርድ ቤቱ ሰጥቷቸው የነበሩት ትዕዛዞች አለመፈጸማቸውን ለችሎቱ በማስረዳቱ ነው፡፡

ትዕዛዙን የሰጠው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደ የፀረ ሽብርና የሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ሰኞ ታኅሳስ 11 ቀን 2014 ዓ.ም. ነው፡፡

ፍርድ ቤቱ በዕለቱ ቀጠርቶ ሰጥቶ የነበረው ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ በእነ አቶ እስክንድር ነጋ (አራት ተከሳሾች) ላይ ቀሪ ምስክር ለመስማት ቢሆንም፣ ቀድሞ በነበረው ቀጠሮ ችሎት ቀርቦ ማንነቱን አስመዝግቦና በቀጠሮው ቀን እንዲቀርብ በፍርድ ቤቱ ተነግሮት የነበረ አንድ ምስክር ሳይቀርብ ቀርቷል። በመሆኑም ዓቃቤ ሕግ በዕለቱ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው አቤቱታ ግለሰቡ መተማመኛ ላይ ከፈረመ በኋላ በአድራሻው ሊያገኝው አለመቻሉን በመግለጽ፣ ታስሮ እንዲቀርብ ትዕዛዝ እንዲሰጥለት አመልክቷል::ሌላ አንድ ቀሪ ምስክርም መጥሪያ እንዲደርሳቸው በድጋሚ ትዕዛዝ እንዲሰጥለት ጠይቋል።

ፍርድ ቤቱ ዓቃቤ ሕግ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ኃላፊ ምስክርነት ተቆጥሮና እንደሚቀርብ ፈርሞ የቀረበውን ግለሰብ 48 ሰዓት ውስጥ አስሮ እንዲያቀርብ፣ ለሌላው ምስክር ደግሞ መጥሪያ እንዲደርሳቸው ትዕዛዝ ሰጥቶ ለታኅሳስ 15 ቀን 2014 .ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

አቶ እስክንድር ነጋ፣ አቶ ስንታየው ቸኮል፣ ወ/ሮ ቀለብ ሥዩምና ወ/ሮ አስካለ ደምሌ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1)()() 35 38 እና 240 (1)() እንዲሁም የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀጽ  6(2) በመተላለፍ፣ የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን ሞት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በኦሮሞና በትግራይ ብሔር ተወላጆች፣ አንዲሁም በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም በማዘዝ፣ በማደራጀትና በመምራት  ባነሳሱት ወንጀል ሰኔ 23 እና 24 ቀን 2012 . በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠረ የእርስ በርስ ግጭት 14 ሰዎች ሕይወት እንዲያልፍና 187 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት አንዲወድም በማድረግ፣ አንድ ወገን በሌላው ላይ የጦር መሣሪያ አንዲያነሳ በማነሳሳት፣ በመንግሥት ላይ የሚደረግ ወንጀልና የፖለቲካ ርዕዮተ ዓላማቸውን በኃይል ለማራመድ ሕዝብን አነሳስተዋል በሚል ወንጀል መከሰሳቸው አይዘነጋም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...