Wednesday, May 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናመንግሥት የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ውሳኔን ፖለቲካዊ ነው አለ

መንግሥት የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ውሳኔን ፖለቲካዊ ነው አለ

ቀን:

መንግሥት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በጄኔቫ ያሳለፈው የውሳኔ ሐሳብ፣ ፖለቲካዊና የቀደሙ ጥረቶችን ከንቱ ለማድረግ የሚደረግ ጥረት ነው ሲል አጣጣለው፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የውጭ ቋንቋዎችና የዲጂታል ሚዲያ ኃላፊ ቢልለኔ ሥዩም ታኅሳስ 12 ቀን 2014 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ መንግሥት የውሳኔ ሐሳቡን ከፀደቀ በኋላ ሳይሆን ከፅንሰቱ እንደማይቀበለው ያሳወቀ እንደሆነ በመግለጽ፣ መንግሥት አልቀበልም እንዳለና መላ ሒደቱን እደሚነቅፈው አስታውቀዋል፡፡

ወዳጅ የአፍሪካና የሌላ አኅጉር አገሮች በዋናነት በአውሮፓ ኅብረት አስተባባሪነት ተረቅቆ የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ውድቅ ማድረጋቸውን በማውሳትና በማድነቅ፣ ኢትዮጵያ ውሳኔውን አልቀበልም ማለቷ በሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ላይ ምርመራ እንዳይደረግ ማገድ ተደርጎ ሊወሰድ አይገባም ብለዋል፡፡

- Advertisement -

ነገር ግን በኢትዮጵያ የሰሜኑ ክፍል ጦርነት ወቅት የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለመመርመር የተቋቋመው ዓለም አቀፍ መርማሪ ኮሚቴ፣ የመንግሥትን ቀደምት ጥረቶች ለማጣጣል ያለመና የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከተመድ  የሰብዓዊ መብቶች ጽሕፈት ቤት ጋር በጋራ ባደረጉት ምርመራ ያስቀመጧቸውን ምክረ ሐሳቦች ወደ ጎን የገፋ ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ጽሕፈት ቤት በጋራ ያደረጉትን ጥናት መንግሥት ከጅምሩ ደግፎ የተወሰኑ ግኝቶችን በመቀበል ፍትሕ ለመስጠት እየተንቀሳቀሰ እንዳለ፣ ለዚህም የሚረዳ የሚኒስትሮች ግብረ ኃይል ተመሥርቶ እየሠራ እንደሚገኝ አውስተዋል፡፡ ይህም የሆነው መንግሥት በሪፖርቱ ላይ ያሉትን ቅሬታዎች አሳውቆ ጭምር እንደሆነ በመጥቀስ፣ አዲስ ምርመራ ለማድረግ የመነሳትን ፍላጎት አጣጥለዋል፡፡

‹‹ይህ ሒደት ሳይቋረጥ ተመሳሳይ ጉዳዮችን የሚመረምርና በተመሳሳይ ጊዜያት ተፈጸሙ የተባሉ ጥሰቶችን የሚያጣራ ሥራን መደገፍ ምንም ስሜት የማይሰጥ፣ በቅርብ የተደረገው ምርመራ ውጤት በጠበቁት መንገድ ስላላገኙት የሆነ ነው፤›› ሲሉም አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ጽሕፈት ቤት በጋራ ባደረጉት ምርመራ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ እንደተፈጸመ የሚያሳይ ማስረጃ አለማግኘታቸውን ያስታወቁ ሲሆን፣ ረሃብ እንደ ጦር መሣሪያ ውሏል መባሉንም በተመሳሳይ ገምግመዋል፡፡ ሆኖም የምርመራ ሪፖርቱ በጦርነቱ የተሳተፉ ሁሉም ወገኖች፣ መደበኛም ሆኑ መደበኛ ያልሆኑ ኃይሎች፣ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ፈጽመዋል በማለት አስታውቀዋል፡፡

የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የመንግሥትን ጥረቶች እንዲቀበልና ለጋራ ምርመራውን ሪፖርትም ዕውቅና እንዲሰጥ እንደሚፈልግ ቢልለኔ አስታውቀው፣ በትግራይ ክልል ተፈጸሙ የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በአማራና በአፋር ክልል ከተፈጸሙት ጋር እኩል ለማየት ሚዛናዊነት ማጣት አለ ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...