Friday, September 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የተሰጡ ሥልጣኖች እንዲሻሻሉ ተጠየቀ

ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የተሰጡ ሥልጣኖች እንዲሻሻሉ ተጠየቀ

ቀን:

የታቀደውን ሁሉን አካታች አገራዊ ምክክሩን ለመምራት በሚቋቋመው ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የተሰጡልጣኖች የገለልተኝነት ጥያቄ የሚያስነሱ በመሆናቸው እንዲሻሻሉ ተጠየቀ።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተመራው በዚህ ረቂቅ አዋጅ ላይ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ የመጀመሪያ ሕዝባዊ ውይይት ሰኞ ታኅሳስ 11 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደበት ወቅት፣ በተሳታፊነት የተገኙ የዴሞክራሲ ተቋማትና የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች፣ የሚቋቋመው የምክክር ኮሚሽን ገለልተኝነት ላይ አጽንኦት በመስጠት ቢሻሻሉ ያሏቸውን የረቂቅ አዋጁ ይዘቶች አንስተዋል።

ከእነዚህም መካከል አንዱ ለሚቋቋመው ኮሚሽን የሚሰየሙ 11 ኮሚሽነሮች የሚጠቆሙበትና የሚታጩበት ሥርዓት፣ ከመንግሥት ሥራ አስፈጻሚው ውጪ እንዲሆኑ ጠይቀዋል።

በረቂቅ አዋጁ ላይ ኮሚሽነሮቹ በሕዝብና በባለድርሻ አካላት እንደሚጠቆሙ የሚገልጽ ሲሆን፣ የዕጩዎች ጥቆማን የመቀበልና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የማቅረብ ኃላፊነት ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የሚሰጥ ነው። 

የዕጩዎች ጥቆማን የመቀበልና ተጠቋሚዎቹን ለይቶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የማቅረብደት፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መሰጠቱ የገለልተኝነት ጥያቄ የሚያጭር በመሆኑ፣ እንዲሻሻልሳብ ካቀረቡት መካከል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶችና ሕፃናት ኮሚሽነር የሆኑት መስከረም ገስጥ አንዷ ናቸው።

በአማራጭነትም ለኮሚሽነርነት የሚታጩ ግለሰቦችን ጥቆማ የመቀበልና የመለየትደት ገለልተኛ በሆነ ቡድን እንዲከናወን፣ ካልሆነም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኩል ቢከናወን የተሻለ እንደሆነ ገልጸዋል።

ይህንን አስተያየታቸውን ለማጠናከርም እሳቸው ለሚሠሩበት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሚሾሙ ኮሚሽነሮች የሚጠቆሙበትና የሚሾሙበትን ሥነ ሥርዓት ማየት እንደሚቻል ጠቁመዋል።

ለኢትዮጶያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሚሾሙ ኮሚሽነሮች የሚጠቆሙበትደት፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ በሚመራ ኮሚቴ እንደሚመራ ይታወቃል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ተመሳሳይ አስተያየት የሰጡት የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ / ራሔል ባፌ(ዶ/ር) አገራዊ ምክክር ለማድረግ የተፈለገው ሲንከባለሉ የመጡ አገራዊ የፖለቲካ ልዩነቶችን ለመፍታት በመሆኑ፣ ኮሚሽነሮቹ የሚጠቆሙበት ሒደት ከተለመደው አሠራር የተለየ መሆን አለበት ብለዋል።

ይህ ጉዳይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትም ሆነ ከሥራ አስፈጻሚው ውጪ በሆነ ገለልተኛ አካል መመራት እንዳለበት በመግለጽ ማሻሻያ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

ከሲቪል ማኅበራት የተወከሉ አካላትም በዚሁ ጉዳይ ላይ ተመሳሳይ አቋም ያራመዱ ሲሆን፣ አንዳንዶቹ በአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ጽሕፈት ቤት እንዲመራ ጠይቀል።

ግለሰቦች ለኮሚሽነርነት ከሚጠቆሙበትና ከሚታጩበት ሒደት በተጨማሪ የተነሳው የገለልተኝነትን የተመለከተው ሌላው ጉዳይየረቂቅ አዋጁ ማስፈጸሚያ ደንብን የማውጣትልጣን ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መሰጠቱ ነው።

በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት የሰጡት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት /ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የአዋጁን ማስፈጸሚያ ደንብ የማውጣት ሥልጣንን ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መስጠት፣ የገለልተኝነት ጥያቄ ሊያስነሳ እንደሚችል በመግለጽ ማሻሻያ እንዲደረግበት ጠይቀዋል።

በማሻሻያነትም ደንብ የማውጣት ሥልጣን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሰጥሳብ አቅርበዋል።

በረቂቅ አዋጁ ላይ አዋጁን ማስፈጸሚያ ደንብ የማውጣት ሥልጣን ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚሰጥ ሲሆን፣ የሚቋቋመው ኮሚሽን የኮሚሽነሮች ምክር ቤት ደግሞ ዝርዝር መመርያ የማውጣትልጣን እንደሚኖረው ያመለክታል።

በሚቋቋመው የኮሚሽነሮች ምክር ቤት በሚወጣ መመርያ እንደሚወሰኑ ከተገለጹ ጉዳዮች መካከል አንዱበአገራዊ የምክክርደቱ የሚሳተፉ አካላት የሚለዩበትደትና ምክክር የሚደረግባቸው አጀንዳዎችን የመለየትደት ይገኙበታል።

በተነሱት ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ የሰጡት የፍትሕ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) ለኮሚሽነርነት የሚጠቆሙ ግለሰቦች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመቅረባቸው አስቀድሞ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረጉ በረቂቅ አዋጁ ላይ ድንጋጌ መቀመጡን በመጠቆም፣ ይህ የተደረገበት ምክንያት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጠቆሙ ግለሰቦችን አድርገው ከማቅረባቸው በፊት ማንኛውም አካል ያለውንጋትም ሆኑ ጥያቄ እንዲያነሳ እንደሚያስችል ገልጸዋል።

ነገር ግን ከቀረቡት አማራጮች መካከል ጥቆማ የመቀበል ኃላፊነቱ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቢከናወን የሚለውን በአማራጭነት ማየት እንደሚቻል አስረድተዋል።

አዋጁን የማስፈጸሚያ ደንቦችን የሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዲያወጣ የሚደነግገውን አንቀጽ እንዲሻሻል የቀረበውን አስተያየት ተገቢ እንደሆነ የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ደንቦችን የማውጣት ሥልጣን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሆኖ እንደሚሻሻል አስታውቀዋል።

የሚቋቋመው ኮሚሽን ኃላፊነቱን የሚጀምረው ከዜሮ እንደማይሆን በመግለጽከዚህ ቀደም በማይንድ ኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች ተቋማት የተከናወኑ ጥናቶችን እንደ ግብዓት እንደሚወስድ አረጋግጠዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...