በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዘጋጅነት ‹‹በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚደርስ ጥቃት ይቁም›› በሚል መሪ ቃል ታኅሳስ 10 ቀን 2014 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ ሕዝባዊ ሠልፍ ተካሂዷል፡፡ ሠልፉ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። የሠልፉ ተሳታፊዎች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ የተባለው የሕወሓት ቡድን በሴቶችና ሕፃናት ላይ ያደረሰውን እጅግ የከፋ ሰብዓዊ ጥቃት አውግዘዋል፡፡ አንዳንድ ምዕራባውያን አገሮች ኢትዮጵያ ላይ እያደረሱ ያለውን ያልተገባ ጫናና ጣልቃ ገብነት በመቃወምም NoMore የሚል መፈክር ይዘው ታይተዋል፡፡
ፎቶ ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሰክሬተሪያት