በመሬትና መሬት ነክ አገልግሎቶች እንዲሁም የመሠረተ ልማት ቅንጅት ሥራዎች ላይ ጥሎት የነበረው ዕግድ ማንሳቱን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣኑ አስታወቀ፡፡፡
ዕግዱ ከታኅሳስ 12 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ መነሳቱን፣ የከንቲባ ጽሕፈት ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ በሆኑት አቶ ጥላሁን ወርቁ ሮቢ ተፈርሞ በወጣ ደብዳቤ የተገለጸ ሲሆን፣ ዕግድ ተጥሎባቸው ከነበሩት ውስጥ በሊዝ ይዞታዎች አዲስ የግንባታ ፈቃድ የመስጠት፣ የፕላን ስምምነት፣ የግንባታ ማሻሻያ፣ ለነባር ይዞታ ካርታ ያላቸው በመልሶ ማልማት ውስጥ (Regulation) የተጠናላቸው፣ የሊዝ ይዞታዎች፣ የምትክ ቦታ መሬት ሲረጋገጥ የአገልግሎት ክፍያ የመሰብሰብ፣ የዕድሳት ፈቃድ መስጠት፣ የግንባታ ማስጀመሪያ የመስጠትና አገልግሎት ክፍያ የመሰብሰብ፣ የግንባታ ማስጀመሪያ ክትትል ውስጥ የነበሩ በዕርከን የአገልግሎት ገቢ የመሰብሰብ፣ ለተለያዩ አካላት የግንባታ መረጃ የመስክ ሪፖርት የመስጠትና የአገልግሎት ክፍያ የመሰብሰብ፣ የሕንፃ መጠቀሚያ ፈቃድ መስጠትና ክፍያ የመሰብሰብ የአገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገልጿል፡፡