Thursday, February 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየሕክምና ዕርዳታ ይዘው ለሚመጡ ዳያስፖራዎች የጭነት ዋጋ ቅናሽ ተደረገ

የሕክምና ዕርዳታ ይዘው ለሚመጡ ዳያስፖራዎች የጭነት ዋጋ ቅናሽ ተደረገ

ቀን:

የሕክምና ዕርዳታ ይዘው ወደ አገር ቤት ለሚመጡ የዳያስፖራ አባላት እስከ 20 በመቶ የጭነት ዋጋ ቅናሽ መደረጉ ተገለጸ፡፡ በእጅ ሻንጣም ሆነ በትልቅ ጭነት ወደ ኢትዮጵያ የጤና ቁሳቁስ የሚያመጡ ዳያስፖራና የኢትዮጵያ ወዳጆችን መጉላላት የሚያስቀር ቀልጣፋ አሠራር መዘርጋቱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የመድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ፣ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣንን ጨምሮ ሌሎች አካላትን ያስተባበረ በጤና ሚኒስቴር የሚመራ የጤና ዕርዳታ የማስተባበር ቅንጅት መፈጠሩን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ባልደረባ አብነት ዘለቀ (ዶ/ር) ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ዳያስፖራው ይዞ የሚመጣውን የሕክምና ዕርዳታ በተቀላጠፈ ሁኔታ ለመረከብና ለማከፋፈል ቀልጣፋ አሠራር ተበጅቷል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

‹‹ዳያስፖራው በተናጠል ይዞ የሚመጣውን የሕክምና ዕርዳታ ኤርፖርት ላይ ለመረከብ ዝግጅት ተጠናቋል፤›› ብለዋል፡፡ ማንኛውም ሰው የጤና ሚኒስቴር ቅድሚያ ቢሰጣቸው ብሎ ያወጣቸውን የድንገተኛ ሕክምና መስጫ ቁሰቁሶች ለአገሩ ይዞ እንዲመጣም ጠይቀዋል፡፡ አገሪቱ ወደ አንድ ሚሊዮን የዳያስፖራ አባላትን ለመቀበል ዝግጅት ማገባደዷንም አክለዋል፡፡ ወደ አገር ቤት የሚገባው ዳያስፖራም ሆነ የኢትዮጵያ ወዳጅ የሕክምና ቁሳቁስ በማምጣት ውለታ እንዲውል ጥሪ አድርግዋል፡፡

በተናጠል በቦርሳ ወይም በማኅበርና በተቋም ደረጃ በትልቅ ጭነት መድኃኒትና የሕክምና ቁሳቁስ ይዘው የሚመጡ አስቀድመው ለጤና ሚኒስትር ማሳወቅ እንዳለባቸው አብነት (ዶ/ር) ያስረዳሉ፡፡ ‹‹በግለሰቦች ተይዞ የሚመጣው ከገባ በኋላ ፎርማሊቲዎችን መጨረስ ቢቻልም፣ በካርጎ ተጭኖ የሚገባውን ግን የ20 በመቶ የመጓጓዣ ቅናሽ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ለማግኘት ቀድሞ ማሳወቅ ግዴታ ነው፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

‹‹የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን አስቀድሞ የማስገቢያ ፈቃድ ይሰጣል፣ የመድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ደግሞ ኤርፖርት ላይ ልገሳውን ተረክቦ ያከማቻል፤›› ብለዋል አብነት (ዶ/ር)፡፡ አሠራሩ ከኤርፖርት ጀምሮ ከአየር መንገድና ከሌሎች አካላት ጋር በቅንጅት ቢሠራም በዋናነት በጤና ሚኒስቴር እንደሚመራ ገልጸዋል፡፡

በምክትል ኮሚሽነር ደረጃ የሚመራ ከኤርፖርት ቅርንጫፍና ከዋና መሥሪያ ቤት የተውጣጣ አንድ ግብረ ኃይል ማዋቀሩን የገለጸው የጉምሩክ ኮሚሽን በበኩሉ፣ ቀልጣፋ አገልግሎት ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ ‹‹የሕክምና ዕርዳታ የሚያመጡ ዳያስፖራና የኢትዮጵያ ወዳጆች የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ሕጎችን በተመለከተ ችግር እንዳያጋጥማቸው፣ ኤርፖርት ላይ ተዘጋጅተን እየጠበቅን ነው፤›› ይላሉ የኮሚሽኑ የለውጥ አማካሪ አቶ መንግሥቱ ተፈራ፡፡

በመደበኛነት የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን በኤርፖርት ተቆጣጣሪዎች እንዳሉትና ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር እንደሚሠራ አቶ መንግሥቱ ያስረዳሉ፡፡ ‹‹ተቋሙ ፈቃድ የሚሰጣቸውን መድኃኒቶችና የሕክምና ግብዓቶች እንዲገቡ መፍቀድ ሥራችን ነው፤›› የሚሉት አቶ መንግሥቱ፣ ‹‹አሁን ደግሞ ከሌሎች አካላት ጋር ተቀናጅተን ሥራውን የምናቀላጥፍበት ወሳኝ ወቅት ነው፤›› ሲሉ ዝግጅታቸውን ተናግረዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር እያስተባበረ ያለው ከዳያስፖራው የሚሰበስባቸው የጤና ቁሳቁሶች ዕርዳታ ሥራ በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲካሄድ፣ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው፡፡ ዕርዳታው  በተለይ በጦርነቱ የወደሙ በአማራና በአፋር ክልሎች የሚገኙ ሕክምና  ማዕከላትን መልሶ ለማቋቋምና ለተጎጂ ማኅበረሰቦች ፈጣን ሕክምና ለመስጠት እንደሚውል ተነግሯል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቤኔ አባል የሆኑት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያዳመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል...

የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት የፈጠሩት አምቧጓሮ

ባለፈው ቅዳሜና እሑድ በአዲስ አበባ የተካሄደው የአፍሪካ ኅብረት 37ኛው...

የብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ትግበራ የፈጠራቸው አሉታዊና አዎንታዊ ጎኖች

የአገሪቱ ንግድ ባንኮች በዓመት የሚሰጡት የብድር መጠን ላይ የኢትዮጵያ...

ቱግ ቱግ!

የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ለመታደም የመጡ እንግዶችን ሸኝተን ከፒያሳ ወደ...