Sunday, March 3, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኢዜማ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮች ምልመላና ጥቆማ ሥልጣን ለፕሬዚዳንት እንዲሰጥ ጠየቀ

ኢዜማ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮች ምልመላና ጥቆማ ሥልጣን ለፕሬዚዳንት እንዲሰጥ ጠየቀ

ቀን:

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ፓርቲ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ለማቋቋም በተረቀቀው አዋጅ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጠው የኮሚሽነሮች ምልመላና ጥቆማ ሥልጣን ለፕሬዚዳንት እንዲሆን ጠየቀ፡፡

ይኼንን በተመለከተ ከሪፖርተር ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢዜማ የሥራ አስፈጻሚ አባል ሀብታሙ ኪታባ፣ ፓርቲው ምልመላውና ጥቆማው በጠቅላይ ሚኒስትር እንዲመራ መደረጉን አልተቀበለውም ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆኑ ፓርላማው በአብዛኛው የአንድ ፓርቲ ሰዎች በመሆናቸው፣ ሥልጣኑ ለፓርላማው መሰጠቱን ኢዜማ እንደማይደግፍ ተናግረዋል፡፡ ይሁንና በፕሬዚዳንት ተመልምለውና ተጠቁመው የሚፀድቁ ኮሚሽነሮች ተጠሪነት ለፓርላማው ቢሆን ችግር የለውም ብሎ ፓርቲያቸው እንደሚያምን አስረድተዋል፡፡

ይኼንን በተመለከተ ፓርቲው ሐሙስ ታኅሳስ 14 ቀን 2014 ዓ.ም. ለፓርላማው ባስገባው ደብዳቤ፣ ‹‹የኮሚሽኑ ምክር ቤት አጀንዳን ከማፅደቅ በተጨማሪ ብሔራዊ ምክክሩን ተከትሎ የሚወጡ የውሳኔ ሐሳቦችን ተግባራዊ ማድረግ ያለባቸው አካላት እንዲፈጽሙት ሲያቀርብ፣ የውሳኔ ሐሳቡን የሚቀበሉት የመንግሥት አካላት ተፈጻሚ የማድረግ ግዴታ እንዳለባቸው በሚያሳይ መሆኑ ቢገለጽ፣ በአገራዊ ምክክሩ የሚወጡ የመፍትሔ ሐሳቦች የተፈጻሚነት ዕድላቸውን ይጨምረዋል፤›› ብሎ ያምናል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ኢዜማ እንዲህ ያለውን ምክረ ሐሳብ ሊያቀርብ የቻለው፣ ኮሚሽኑ የሚያቀርበውን ምክረ ሐሳብ የመፈጸም ኃላፊነት በመንግሥት ላይ ተጥሎ፣ መንግሥት ጉዳዩን ለመፈጸም ፈቃደኛ ባይሆንስ በሚል መነሻ እንደሆነ አቶ ሀብታሙ ተናግረዋል፡፡ ስለዚህ የአስገዳጅነት ድምፀት ሊኖረው ይገባል በማለት የቀረበ ምክረ ሐሳብ ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ደንብ የማውጣት ሥልጣን ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መሰጠቱ ነፃነቱን ያሳጣዋል ያለው ኢዜማ፣ ኮሚሽኑ ለሦስት ዓመታት ተመሥርቶ እንደ አስፈላጊነቱ ሊራዘም ይችላል መባሉ ገደብ ሊኖረው ይገባልና እስከ አምስት ዓመት ድረስ ብሎ የሚገምት ድንጋጌ እንዲኖረው መጠየቁንም አቶ ሀብታሙ አክለዋል፡፡ ፓርቲው ይኼንን ያለበት ምክንያት ኮሚሽኑ ተግባሮቹን በአግባቡ መፈጸም ካልቻለ እንደ ልቡ ቆይታው ሊራዘምለት ስለማይገባ ነው በማለት ያብራራሉ፡፡

ከዚህ ባለፈ ምክክር የሚለው ቃል በአዋጁ ትርጉም ሊሰጠው እንደሚገባ በማውሳት፣ ‹‹ኢዜማ ምክክሮች ሕዝባዊ መድረኮች፣ ዜጎች በሙያቸውም ሆነ በሌላ በተደራጁባቸው ማኅበራዊ አደረጃጀቶች የሚሳተፉበት ፍላጎት ተኮር የሆኑ የውይይቶች መድረኮች፣ እንዲሁም በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚደረጉ ድርድሮችን ያቀፈ እንደሚሆን ይረዳል፤›› ሲል ለፓርላማው በላከው ደብዳቤ ተናግሯል፡፡

ረቂቅ አዋጁ አክሎም የኮሚሽኑ ሒሳብና ተያያዥ ሰነዶች ‹‹በዋና ኦዲተር ወይም እሱ በሚሰይማቸው ኦዲተሮች በየዓመቱ ይመረመራሉ›› የሚለው በግልጽ ከሁለቱ አካላት ማን እንደሚመረምረው ተለይቶ ሊቀመጥ ይገባዋል ሲልም የጠየቀው ኢዜማ፣ ለኮሚሽኑ ሥራዎች ማናቸውም ግለሰቦች የመተባበር ግዴታ አለባቸው የሚለው መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላትን ማካተት አለበት ሲልም ሞግቷል፡፡

አቶ ሀብታሙ ከፕሮጀክቱ አስፈላጊነት አንፃር በማየት ጥድፊያው ብዙም አልተመቸንም ብለው፣ የቋሚ ኮሚቴ ስብሰባዎች በአግባቡ ሳይተዋወቁና በርካቶች ሳይሰሟቸውና በቂ ትኩረት ሳያገኙ፣ እንዲሁም የሕዝቡ ትኩረቱ በጦርነቱ ላይ ሳለና ትኩረት ሳይሰበስብ በፍጥነት መካሄዱ እንደሚያሳስባቸው ተናግረዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ሕዝቡ ለጦርነቱ ከሚደረግ ድርድር ጋር እያምታታው ነው ብለዋል፡፡

ከአሁን ቀደም በአገሪቱ የነበረውን የማይንድ ኢትዮጵያ የአገራዊ ምክክር ሙከራ ፓርቲያቸው እንደ አገራዊ ምክክር እንደማይመለከተውና አገራዊ ምክክር በመንግሥት ባለቤትነት የሚከናወን መሆን ይገባዋል የሚሉት አቶ ሀብታሙ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስለገቡበት ‹ተደገፍን› ብለው ሊያስቡ ቢችሉም ለትርፍ ካልተቋቋመ ድርጅት ፕሮጀክቶች አንዱ አድርገው እንደሚመለከቱት አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...