Sunday, June 4, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ዓባይ ባንክ ከታክስ በፊት ያስመዘገበው የትርፍ ምጣኔ በ80 በመቶ ማደጉን አስታወቀ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

ዓባይ ባንክ የ2013 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ ትርፍ ምጣኔውን በ80 በመቶ በማሳደግ 1.15 ቢሊዮን ብር ማድረስ መቻሉን አመለከተ፡፡ ባንኩ የ2013 የሒሳብ ዓመት የሥራ አፈጻጸሙን ይፋ ባደረገበት ሪፖርቱ፣ በሒሳብ ዓመቱ ከታክስ በፊት ያስመዘገበው የትርፍ ምጣኔ በ80 በመቶ ማደጉን አመልክቷል፡፡

ባንኩ በሒሳብ ዓመቱ ያገኘው ትርፍ በ2013 የሒሳብ ዓመት የትርፍ ምጣኔያቸውን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ካደረሱ ባንኮች መካከል አንዱ አድርጎታል፡፡ ሌሎች አፈጻጸሞቹን በተመለከተ ከባንኩ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ወንድይፍራው ታደሰ መግለጫ መረዳት እንደተቻለው፣ ባንኩ በሒሳብ ዓመቱ 7.8 ቢሊዮን ብር አዲስ ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰብ ችሏል፡፡

በሒሳብ ዓመቱ ከወለድ ነፃ ያሰባሰበውን ጨምሮ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ መጠኑን 23.9 ቢሊዮን ብር ማድረስ አስችሎታል፡፡ ይህ የተቀማጭ ገንዘብ አሰባሰብ ከቀዳሚው ዓመት 49 በመቶ ዕድገት የታየበት መሆኑንም የሚያመለክት ነው፡፡

ባንኩ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ያሰባሰበው ተቀማጭ ገንዘብ መጠን በተናጠል ሲታይም በ71 በመቶ ዕድገት ታየበት ስለመሆኑ ተገልጿል፡፡ በሒሳብ ዓመቱ መጨረሻ ላይ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የተሰባሰበው የገንዘብ መጠንም 1.3 ቢሊዮን ብር መድረሱ ታውቋል፡፡

በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት 376 ሺሕ አዳዲስ አስቀማጮችን ማፍራት የቻለው ዓባይ ባንክ፣ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ደንበኞቹን ጨምሮ አጠቃላይ የአስቀማጮቹን ቁጥር 1.2 ሚሊዮን ማድረሱንም የባንኩን የሥራ አፈጻጸም በተመለከተ ከተደረገው ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡

እንደ ምክትል ፕሬዚዳንቱ አቶ ወንድይፍራው ገለጻ፣ ዓባይ ባንክ ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች የተሰጠው የብድር መጠን 72 በመቶ ዕድገት በማሳየት 20.1 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡ ከዚህ አጠቃላይ ብድር ውስጥ 19.6 ቢሊዮን ብር የሚሆነው በመደበኛው የባንክ አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን፣ ቀሪው 538 ሚሊዮን ብር ደግሞ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በኩል የተሰጠ እንደሆነ አመልክተዋል፡፡   

በሒሳብ ዓመቱ ካለፈው የ63 በመቶ ብልጫ ያለው ገቢ ማግኘቱን የሚያመለክተው የባንኩ ሪፖርት፣ አጠቃላይ ዓመታዊ ገቢውን 3.4 ቢሊዮን ብር ማድረስ መቻሉን ጠቁሟል፡፡

ዓባይ ባንክ በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ የሀብት መጠኑን 29.9 ቢሊዮን ያደረሰ ሲሆን፣ ይህ የሀብት መጠን ከቀዳሚው ዓመት አንፃር ሲታይ የ9.8 ቢሊዮን ብር ወይም የ48 በመቶ ጭማሪ ያሳያል፡፡

ዓባይ ባንክ በአሁኑ ጊዜ የተከፈለ ካፒታል መጠኑን 2.8 ቢሊዮን ብር፣ የሠራተኞቹን ቁጥር ደግሞ 5,307 አድርሷል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች