Sunday, June 16, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ቡና ባንክ ለገና አገር ቤት ለሚገቡ ዳያስፖራዎች አጓጊ ሽልማት ማዘጋጀቱን አስታወቀ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

ቡና ባንክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ባደረጉት ጥሪ መሠረት ወደ አገር ቤት ለሚገቡ ዳያስፖራዎች የያዙትን ገንዘብ በባንኮች ብቻ እንዲመነዝሩ ለማበረታታት ልዩ የባንክ አገልግሎት እንዳመቻቸና ‹‹አጓጊ›› ያለውን ለመሸለም ማቀዱን አስታወቀ፡፡

ባንኩ የውጭ ምንዛሪ ‹‹ይቀበሉ ይሸለሙ›› መርሐ ግብር ማጠናቀቂያን ምክንያት በማድረግ እንዳስታወቀው፣ ለገና በዓል ወደ አገር የሚገቡ ዳያስፖራዎችን ለማበረታታ ልዩ የባንክ አገልግሎት ከማመቻቸቱም በላይ በልዩ መንገድ ተጠቃሚ የሚያደርጋቸውን ‹‹አጓጊ›› ነው ያለውን ዕድል ማመቻቸቱንም አስታውቋል፡፡

የባንኩ የኢንተርናሽናል ባንኪንግ ዳይሬክተር አቶ ጠና ኃይለ ማርያም እንደገለጹት፣ በተለይ በአሁኑ ወቅት የምዕራባውያን መንግሥታት በሚያስተላልፏቸው ኢፍትሐዊ ውሳኔዎች ያሳድሩብንን ጫና ለመቋቋም አንዱ መንገድ ዳያስፖራዎች ገንዘባቸውን በሕጋዊ መንገድ መመንዘር የሚኖርባቸው መሆኑን ነው፡፡

ለገና በዓል ወደ አገር ቤት የሚገቡ ዳያስፖራዎች ይህንን በማድረግ በተለያዩ ተፅዕኖዎች ኢኮኖሚያችን ላይ የሚያደርሰውን ጫና ለመቋቋም የሚያስችል ስለሆነ፣ ዳያስፖራው በውጭም ሆነ በአገር ውስጥ ባለበት ወቅት ገንዘብ ለመመንዘርም ሆነ ለመላክ ሕጋዊ መንገድን እንዲጠቀም ባንኩ ጠይቋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም ባንኩ አገራዊ ጥሪውን ተከትለው ለገና በዓል ወደ አገር ለሚገቡ የዳያስፖራ ማኅበረሰብ፣ የያዙትን ገንዘብ በባንክ እንዲመነዝሩ ለማበረታታት አዳዲስ የባንክ አገልግሎት ማዘጋጀቱን ገልጿል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም በባንክ በመመንዘራቸው ብቻ በልዩ ልዩ መንገድ ተጠቃሚ የሚያደርጋቸውን ‹‹አጓጊ›› የሽልማት ዕድሎችን ያዘጋጀ ሲሆን፣ ከእነዚህም አጓጊ ያላቸውን ዕድሎች ይዞ አገልግሎቱን በቅርቡ እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች