ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የአገር ጥሪን ተቀብለው እየመጡ ላሉት የዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰደ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ረዘም ካለው መልዕክታቸው መካከል፣ ‹‹አንዳንዶች ኢትዮጵያን ለመድፈር በተነሱ ጊዜ፣ ሌሎች የኢትዮጵያን እውነት በውሸት ለመሸፈን በተነሱ ጊዜ፣ የቀሩትም በኢትዮጵያ ላይ ተገቢ ያልሆነ ጫና ለማሳደር በተነሱ ጊዜ፣ ዳያስፖራ ወገኖቻችን ለኢትዮጵያ ሲሉ በአንድነት ቆመዋል። የፖለቲከኞችን በሮች አንኳኩተዋል። አደባባዮችን በሠልፍ አጥለቅልቀዋል፡፡ ታላላቅ ተቋማትን ሞግተዋል፡፡ የመሪዎችን የተሳሳተ ፖሊሲ ተጋፍጠዋል፡፡ ሚዲያዎች የኢትዮጵያን እውነት እንዲያንፀባርቁ ጫና ፈጥረዋል፤›› በማለት አሞካሽተው፣ የዳያስፖራውን አስተዋጽኦ ዘርዝረዋል፡፡