Monday, March 4, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊአስተዳደሩ ከመሬትና መሬት ነክ አገልግሎቶች ከ660 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማጣቱ ተገለጸ

አስተዳደሩ ከመሬትና መሬት ነክ አገልግሎቶች ከ660 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማጣቱ ተገለጸ

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ከነሐሴ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ የመሬትና መሬት ነክ አገልግሎቶች ላልተወሰነ ጊዜ እንዲታገዱ ውሳኔ ካስተላለፈ በኋላ፣ ከ664 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን ገቢ ሳይሰበስብ መቅረቱ ታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ እንዳስታወቀው የከተማ አስተዳደሩ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ትኩረታቸውን በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ እንዲያደርጉና ወቅታዊ አገራዊ ሁኔታውን ተከትሎ ሕገወጥ ተግባራት ላይ የተሰማሩ አካላትን እንቅስቃሴ ለመግታት፣ የመሬትና መሬት ነክ አገልግሎቶች ታግደው እንዲቆዩ ውሳኔ አሳልፎ ነበር፡፡ ካቢኔው ይህንን ውሳኔ የሚገልጽ ሰርኩላር ለመሬት አስተዳደር ተቋማት፣ ለመሠረተ ልማት ቅንጅትና ግንባታ ፈቃድ ባለሥልጣን፣ እንዲሁም 11 ክፍላተ ከተሞች በማስተላለፉ፣ ከነሐሴ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ አገልግሎቶቹ ተቋርጠዋል፡፡

ዕግዱ ከሚመለከታቸው ተቋማት ውስጥ አንዱ የአዲስ አበባ መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ሲሆን፣ ኤጀንሲው በሚሰጣቸው 16 ያህል አገልግሎቶች ገቢ ይሰበስብ እንደነበር የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተክሌ ዲዱ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ የመሬት ስም ዝውውር፣ ካርታ ለጠፋባቸው የማውጣት የአገልግሎት፣ የይዞታ ይቀላቀልና ይካፈል ጥያቄዎች፣ እንዲሁም ወሰንና ወሰን ችካል የማመላከት አገልግሎቶች ኤጀንሲው ገቢ ከሚሰበስብባቸው አገልግሎቶች ውስጥ ዋነኞቹ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የከተማ አስተዳደሩ በተለይ ከግንባታ ጋር ተያያዥነት ያላቸው አገልግሎቶች ላይ የተጣለውን ዕግድ ከታኅሳስ 12 ቀን 2014 .. ጀምሮ ቢያነሳም፣ የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ገቢ የሚሰበስብባቸው እንደ መሬት መሸጥና መለወጥ ያሉ አገልግሎቶች እስካሁን ዕግዱ አልተነሳላቸውም፡፡

ኤጀንሲው ከነሐሴ 2013 እስከ ኅዳር 2014 ዓ.ም. ባለው የአምስት ወራት ጊዜ ውስጥ 666 ሚሊዮን ብር ገደማ ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ የሰበሰበው ገቢ 1.6 ሚሊዮን ብር አካባቢ ነው፡፡ ይህም የዕቅዱን አንድ በመቶ እንኳን አይሞላም፡፡

ይህ ውሳኔ ከተላለፈበት ጊዜ አንስቶ አገልግሎት ፈላጊዎች ወደ ኢጀንሲው አለመምጣታቸውን የተናገሩት አቶ ተክሌ፣ ኤጀንሲው ዓመታዊ ዕቅዱ ላይ ክለሳ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ኤጀንሲው በበጀት ዓመቱ ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ የመሰብሰብ ዕቅድ መያዙ የተገለጸ ሲሆን፣ የስድስት ወራት አፈጻጸም ግምገማ ለማድረግ ከየክፍለ ከተሞቹ መረጃ እየተሰበሰበ መሆኑ ታውቋል፡፡ ከግምገማው መጠናቀቅ በኋላ ‹‹የታጣው ገቢ በምን ዓይነት መንገድ ይካካስ?››፣  ‹‹ኤጀንሲውስ ምን ዓይነት አካሄድ ይከተል?›› የሚሉት ላይ ውሳኔ እንደሚተላለፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ከታኅሳስ 12 ቀን 2014 .. ጀምሮ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ የተጣለው ዕገዳ የተነሳለት የአዲስ አበባ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን በበኩሉ፣ ከዕግዱ ጋር በተያያዘ ከሐምሌ 1 ቀን እስከ ኅዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ የዕቅዱን 70 በመቶ የሚሆን ገቢ መሰብሰብ አለመቻሉን አስታውቋል፡፡ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ስጦታው አካለ (ኢንጂነር) ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ባለሥልጣኑ በመጀመርያው ሩብ ዓመት 26 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ የነበረ ቢሆንም መሰብሰብ የቻለው የዕቅዱን 30 በመቶ ያህል ነው፡፡

‹‹አገልግሎቶች ከመታገዳቸው በፊት ባለው ሐምሌ ወር ላይ ስለሠራንና አንዳንድ አገልግሎቶች ስላልታገዱ የዕቅድ አፈጻጸሙ ዜሮ አልሆነም፡፡ መሰብሰብ ካለብን 30 በመቶ ሰብስበናል፤›› ብለዋል፡፡ እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ ዕግዱ የከተማዋ ሜጋ ፕሮጀክቶችና የካቢኔ ውሳኔ ያገኙ የኢንቨስትመንት ሥራዎች ላይ ተፈጻሚነት ያልነበረው በመሆኑ፣ ከእነዚህ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች ‹‹በልዩ ሁኔታ›› ሲስተናገዱ ነበር፡፡

የከተማ አስተዳደሩ የግንባታ ማስጀመሪያ የመስጠትና አገልግሎት ክፍያ የመሰብሰብ፣ የግንባታ ማስጀመሪያ ክትትል፣ አዲስ የግንባታ ፈቃድ የመስጠት፣ የፕላን ስምምነት፣ የግንባታ ማሻሻያ መሰል አገልግሎቶች ላይ ዕግዱን አንስቶ አገልግሎት እንዲጀመር የፈቀደ ሲሆን፣ እነዚህ አገልግሎቶች ‹‹ብዙም ችግር ያልፈጠሩ፣ ግንኙነት የሌላቸውና ብዙ ተገልጋይ እየተጉላላባቸው የነበሩ›› መሆናቸውን ስጦታው (ኢንጂነር) አስረድተዋል፡፡

ባለሥልጣኑ በዕግዱ ምክንያት ያልሰበሰበውን ገቢ በቀጣይ ወራት የማካካስ ዕቅድ እንዳለው የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ለዚህም ሲባል አገልግሎቱን አቀላጥፎ በቀን ውስጥ የሚስተናገዱ ተገልጋዮችን ቁጥር የመጨመርና የሥራ ሰዓትን የማራዘም ሐሳብ እንዳለ አስታውቀዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...