Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናመንግሥት ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያላቸው የድንጋይ ከሰል ማዕድን ፕሮጀክቶችን ስምምነት...

መንግሥት ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያላቸው የድንጋይ ከሰል ማዕድን ፕሮጀክቶችን ስምምነት አፀደቀ

ቀን:

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ታኅሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደው ሦስተኛ መደበኛ ስብሰባው፣ በስምንት አገር በቀል ኩባንያዎች የተያዙና በድምሩ ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያላቸው ስምንት የከሰል ማዕድን ፕሮጀክት ስምምነቶችን አፀደቀ፡፡

ስምንቱ ፕሮጀክቶች በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ፣ በኦሮሚያናቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፣ ስምንቱ ኩባንያዎች የተመረጡት ማመልከቻ ካቀረቡ 12 ኩባንያዎች መካከል ለፈቃድ አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችንና ቅድመ ሁኔታዎችን አጠናቀው በማቅረባቸው መሆኑ ታውቋል፡፡

ለአሥር ዓመታት የሚቆይ ሆኖ አፈጻጸሙ እየታየ በየአሥር ዓመቱ የሚታደስ የአገልግሎት ፈቃድ ያገኙት ስምንቱ ማዕድን አውጪ ኩባንያዎች፣ በአሥር ዓመታት ውስጥ ያመርታሉ ተብሎ የሚጠበቀው የድንጋይ ከሰል ምርት የሽያጭ ዋጋ 98 ቢሊዮን ብር ይደርሳል፡፡ መንግሥት ከእያንዳንዱ ፕሮጀክት አምስት በመቶ ነፃ ድርሻ ሲኖረው ክልሎች ደግሞ ሁለት በመቶ የነፃ ድርሻ ይኖራቸዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ስምምነታቸው ከፀደቀላቸው ፕሮጀክቶች መካከል በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞንና አጎራባች ቀበሌዎች የሚገኘውን የድንጋይ ከሰል ለማልማት ፈቃድ ባገኙ ሁለት ኩባንያዎች የቀረበው የ2.3 ቢሊዮን ብር የፕሮጀክት ካፒታል፣ በቀሪዎቹ ክልሎች ከቀረበው የፕሮጀክት ካፒታል ትልቁ ነው፡፡ በካማሺ ዞን የሚንቀሳቀሱት ሁለት አገር በቀል ኩባንያዎች፣ በአሥር ዓመታት ውስጥ ሊያወጡ ያቀዱት የድንጋይ ከሰል ጠቅላላ ያልተጣራ ገቢ በድምሩ ከ45 ቢሊዮን ብር ይልቃል፡፡

ሁሉም ፕሮጀክቶች በ2015 በጀትመት መጀመርያ ሩብመት ድረስ የፋብሪካና ሌሎች ተጓዳኝ ግንባታዎችን ጨርሰው ወደ ምርትራ ይገባሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ኩባንያዎቹ ባስጠኑት የአዋጭነት ጥናት መሠረት ፕሮጀክቶቹ ጠቅላላ ወጪያቸውን ለመመለስ የሚወስድባቸው ጊዜስት ዓመት ነው፡፡ ኩባንያዎቹ ባቀረቡት የፕሮጅክት ዕቅድ መሠረትም በአንድመት ጊዜ ውስጥገራዊ ፍላጎትን ማሟላት የሚችል ምርት ለማምረት ማቀዳቸው ታውቋል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስምምነታቸውን ያፀደቀላቸው እነዚህ ኩባንያዎች በዓመት በአማካይ 4.2 ሚሊዮን ቶን የድንጋይ ከሰል የማምረት አቅም ያላቸው ሲሆን፣ ይኼ ምርት የድንጋይ ከሰልን ለኃይል ምንጭነት የሚጠቀሙ እንደ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች ያሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች፣ የኃይል ፍላጎታቸውን ለማሟላት በግዥ የሚያወጡትን በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር የውጭ ምንዛሪ ያስቀራል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡ ምርቱ የአምራች ፋብሪካዎችን የአቅርቦት ችግር በመፍታት ምርቶቻቸውን በበቂ ሁኔታ ማቅረብ እንዲችሉ ያግዛቸዋል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

በስምንቱ ፕሮጀክቶች የሚመረተው የድንጋይ ከሰል የታጠበ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ምርቱ ለኃይል ፍላጎት ከመቅረቡ በፊት በውስጡ የሚገኙት ሰልፈርና ሌሎች በራዥ ንጥረ ነገሮች በውኃና በሌሎች ኬሚካሎች እንዲፀዱ ይደረጋል፡፡ ይህም ያልታጠበ የድንጋይ ከሰል ለፋብሪካዎችይል ፍጆታ በሚነድበት ወቅት ወደ አየር የሚለቀቁትን ጎጂ ንጥረ ነገሮችን በመቀነሰ፣ በአካባቢ ምኅዳር ላይ የሚኖርን ዓሉታዊ ተፅዕኖ ለመከላከል እንደሚረዳ ተጠቁሟል።

ኩባንያዎቹ  ለማጠቢያናማበልፀጊያ የሚያስፈልገውን ጥሬ የድንጋይ ከሰል በራሳቸው ከሚያመርቱትና የአካባቢው ወጣቶች ከሚያመርቱት በመግዛት የሚጠቀሙ ሲሆን፣ ለማዕድን አካባቢ ወጣቶችና ባህላዊ አምራቾች ሁለት ሺሕ ገደማ ቋሚ የሥራ ዕድል ይፈጥራሉ የሚል ዕቅድ አለ፡፡

የማዕድን ሚኒስትሩ አቶ ታከለ ኡማ የድንጋይ ከሰል ምርት ፕሮጀክቶቹ ስምምነት መፅደቅን አስመልክቶ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ የፕሮጀክቶቹ ወደ መግባት በድንጋይ ከሰል ላይ ከውጭ ጥገኝነት የሚያላቅቅና በተለይም የሲሚንቶ ምርት ዘርፍን ከጥሬ አቅርቦት ችግር የሚገላግል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...