Friday, December 2, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየንግዱ ማኅበረሰብ  ሰላም ለማስፈንና ግጭት ለመከላከል የጎላ ሚና እንዲጫወት ተጠየቀ

  የንግዱ ማኅበረሰብ  ሰላም ለማስፈንና ግጭት ለመከላከል የጎላ ሚና እንዲጫወት ተጠየቀ

  ቀን:

  የንግዱ ማኅበረሰብ ከትርፋማነቱ ባሻገር ሰላም ለማስፈንና ግጭትን አስቀድሞ ለመከላከል የጎላ ሚና እንዲጫወት ተጠየቀ፡፡

  ይህ የተገለጸው ሰላም ሚኒስቴር ከኢኒሼቲቭ አፍሪካ ጋር በጋራ በመሆን ‹‹ንግድ ለሰላምና ለዘላቂ የኢትዮጵያ ልማት›› በሚል ርዕስ፣ ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር ረቡዕ ታኅሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. በሒልተን ሆቴል በተዘጋጀ የምክክር መድረክ ነው፡፡

  በመድረኩ ላይ የንግዱ ማኅበረሰብ ከትርፋማነቱ ባሻገር በሰላምና ብሔራዊ መግባባት ላይ የጎላ ሚና መጫወት እንደሚገባ የተጠቆመ ሲሆን፣ ከዚህም በሻገር ለግጭት መንስዔ የሆኑትን ሥራ አጥነት፣ የኑሮ ውድነት፣ የኢኮኖሚ አሻጥርና መሰል ድርጊቶችን ከምንጊዜውም በላይ መከላከል እንደሚገባ ተወያዮች አሳስበዋል፡፡

  ግጭት በቀጠለባቸው አካባቢዎች መደበኛ ሥራዎችን ማከናወን በመሰናክሎች የተሞላ ፈታኝ እንቅስቃሴ እንደሆነ በመድረኩ የቀረበ ሲሆን፣ በዚህ ወቅት የሰላም ግንባታ ሥራዎች ማከናወን ለንግዱ ማኅበረሰብ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ ያም ሆኖ ግን ለግጭት ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ግጭትን ከመከላከል አንስቶ እስከ ድኅረ ግጭት መልሶ ግንባታ ላይ ሰፋፊ ጥረቶች ሊደረጉ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

  የንግዱ ዘርፍ የኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ዋነኛ ሞተር እንደ መሆኑ፣ በሰላም ግንባታ እንዲሁም ከዕርዳታ ጥገኝት በራስ አቅም ወደሚመራ ዕድገት የሚደረግ ሽግግርን ለማፋጠን የራሱን ሚና ሊጫወት እንደሚገባ በመድረኩ ተነስቷል፡፡

  በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ እንዳስታወቁት፣ የንግድ ተቋማት የአገር ምሰሶዎች በመሆናቸው  የሰላም ዕሳቤዎችን በሥራቸው ውስጥ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

  ሚኒስተር ዴኤታው አያይዘውም የንግድ ተቋማት የአገርና የማኅበረሰብን ጥቅም ባስቀደመ መንገድ በመሥራት፣ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠርና የማኅበረሰቡን የኑሮ ጫና በመጋራት ሰላምና መረጋጋትን ሊያሰፍኑ ይገባል፡፡

  በሰላም ሚኒስቴር የስትራቴጂክ አጋርነትና የተጠሪ ተቋማት ማስተባበሪያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሻንቆ ደሳለኝ እንዳስታወቁት፣ የንግዱ ማኅበረሰብ የአገሪቱን የሰላምና እንዲሁም ሌሎች ፖሊሲዎችን አውቆ ሊሠራባቸው ይገባል፡፡

  ለአብነትም በሰላም ሚኒስቴር እየተዘጋጀ የሚገኘው ረቂቅ የሰላም ፖሊሲ ከሚያስቀምጣቸው ጉዳዮች መካከል የንግዱ ማኅበረሰብ ሰላማዊ ተቋም ሊሆን እንደሚገባው፣ የፈጠራ አገልግሎቶችን የሚያቀርብ፣ እንዲሁም ማኅበራዊ ኃላፊነቱን የሚወጣ ተቋም እንዲሆን ነው፡፡ የንግዱ ዘርፍ መብቱን የሚጠይቅ፣ ግዴታውን ያለ አስታዋሽ የሚወጣ፣ እንዲሁም በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ኃላፊነቱን የሚወጣ እንዲሆን ማስቻል የኢትዮጵያ የሰላም ፖሊሲው ዋነኛ ዓላማዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

  የምክክር መድረኩን በአወያይነት የመሩት በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ ጥላሁን በጅቷል (ዶ/ር) እንዳስታወቁት፣ ግጭቶች በተደጋጋሚ  የሚነሳባቸው አካባቢዎች ተጋላጭነታቸው እንዲቀንስ የንግዱን ማኅበረሰብ ጨምሮ የሁሉም ርብርብ ያስፈልጋል፡፡ በአንድ አካባቢ ለሚከሰት ግጭት የሚወሰደው ዕርምጃ እሳት የማጥፋት ሳይሆን፣ በጠነከረ መንገድ ግጭቱን ቀድሞ ለመከላከል የሚያስችል ሊሆን ይገባል፡፡

  ሰላምን መገንባት ለመንግሥት ብቻ የተተወ ፖለቲካዊ ሥራ አይደለም ያሉት ጥላሁን (ዶ/ር)፣ የንግዱ ማኅበረሰብ ግጭትን ከማባባስ መቆጠብና ግጭትን መከላከል እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡

  በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ የሰላም ግንባታ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስማ ረዲ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የሰላም ሚኒስቴር ረቂቅ የሰላም ፖሊሲ አዘጋጅቷል፡፡ የሰላም ፖሊሲው በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙትን ከግለሰብ ጀምሮ እስከ ተቋማት ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍሎች የሚያሳትፍ ነው፡፡

  ወ/ሮ አስማ እንዳስታወቁት፣ የንግድ ተቋማት በአንድ አገር ኢኮኖሚ ላይ ከሚኖራቸው ትልቅ ሚና በሻገር በውስጣቸው ካቀፉዋቸው በዙሪያቸው በሚገኙባቸው አካባቢ ከሚኖሩ የማኅበረሰብ ክፍሎች በሚደርጉት ትስስር የራሳቸው የሆነ ሚና ይኖራቸዋል፡፡ የንግድ ተቋማት ግብይት ፈጽመው እንዲያድጉ ሰላም ያስፈልጋቸዋል፡፡ በተረፈም አምራች ለመሆንም በውስጣቸው ያሉት ዜጎች ሰላማዊ አስተሳሰብ ሊኖራቸው እንደሚገባ፣ ለዜጋና ለአገር ቅድሚያ የሚሰጥ የንግድ ሥርዓት ከሌለ በሌብነት የተበላሸ የንግድ ሥርዓት ካላላ፣ እንዲሁም የንግድ አሻጥሮች በብዙ ቁጥር የማኅበረሰቡም እንግልትና መከራ በዚያው ልክ ያድጋል ብለዋል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...