Tuesday, March 5, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

አዋሽ ባንክ የተከፈለ ካፒታሉን አሥር ቢሊዮን ብር ማድረሱን አስታወቀ

ተዛማጅ ፅሁፎች

አዋሽ ባንክ የባንኩን የተከፈለ ካፒታል አሥር ቢሊዮን ብር ማድረስ መቻሉን አስታወቀ፡፡ ባንኩ የተከፈለ ካፒታሉን 12 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ባስቀመጠው ግብ መሠረት፣ በዚህ ወር አጋማሽ ላይ የተከፈለ ካፒታሉን አሥር ቢሊዮን በማድረስ የመጀመርያው የግል ባንክ ሆኗል፡፡

ይህ የተከፈለ የካፒታል መጠን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነባር ባንኮች የተከፈለ ካፒላቸውን አምስት ቢሊዮን ብር እንዲያደርሱ ከተሰጠው የአምስት ዓመት ጊዜው ሳይደርስ የተጠየቀውን ካፒታል በእጥፍ ማድረስ መቻሉን ያመለክታል ተብሏል፡፡

አዋሽ ባንክ እስከ 2013 የሒሳብ ዓመት መጨረሻ ድረስ የነበረው የተከፈለ ካፒታል መጠን 8.2 ቢሊዮን ብር ነበር፡፡

በአሁኑ ወቅት የተከፈለ ካፒታላቸውን በዚህን ያህል ደረጃ ያደረሱ የግል ባንኮች የሌሉ ሲሆን፣ ሰሞኑን የ2013 የሒሳብ ዓመት አፈጻጸማቸውን ይፋ ካደረጉ ባንኮች መረዳት እንደተቻለው እስካሁን የተከፈለ ካፒታላቸውን አምስት ቢሊዮን ያደረሱ ባንኮች ከሁለት ያልበለጡ ናቸው፡፡

በኢንዱስትሪው ከቆዩ ነባር ባንኮች እስከ 2013 የሒሳብ ዓመት መጨረሻ ድረስ ዳሸን ባንክ 6.1 ቢሊዮን ብር፣ አቢሲኒያ ባንክ 5.18 ቢሊዮን ብር፣ ቡና ባንክ 2.8 ቢሊዮን ብር፣ የኦሮሚያ የኅብረት ሥራ ባንክ 4.65 ቢሊዮን ብር፣ ዘመን ባንክ 2.9  ቢሊዮን ብር፣ ኅብረት ባንክ 3.8 ቢሊዮን ብር፣ ወጋገን ባንክ 3.3 ቢሊዮን ብር፣ አንበሳ ባንክ 2.53 ቢሊዮን ብር፣ ኦሮሚያ ባንክ 3.46 ቢሊዮን ብር፣ ንብ ባንክ 3.4 ቢሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል ማስመዝገባቸው ተጠቅሷል፡፡

በኢንዱስትሪው ውስጥ ከግል ባንኮች ከአዋሽ ቀጥሎ ከፍተኛውን የተከፈለ ካፒታል የያዘውና በቅርቡ ወደ ሥራ የሚገባው አማራ ባንክ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የተከፈለ ካፒታሉ መጠን 7.2 ቢሊዮን ብር ነው፡፡

በብሔራዊ ባንክ መረጃ መሠረት፣ በአጠቃላይ 19ኙ የአገሪቱ የግል ባንኮች በ2013 መጨረሻ ላይ የተከፈለ ካፒታላቸው 153.7 ቢሊዮን ብር መሆኑን ያመለክታል፡፡

ባንኮቹ እስከ ሒሳብ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘባቸው 1.4 ትሪሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ከቀዳሚው ዓመት በ30.3 በመቶ ብልጫ ያለው መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች