Wednesday, December 6, 2023

ጦርነቱ የፈጠረው ኢኮኖሚያዊ ጫናና መልሶ የማቋቋም ፈተና

- Advertisement -spot_img

በብዛት የተነበቡ

በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተቀሰቀሰው ጦርነት አንድ ዓመቱን አገባዶ ወደ ሁለተኛ ዓመት እየተንደረደረ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ የአገሪቱ ኢኮኖሚ ጦርነቱ የፈጠረበት ተፅዕኖ እየከበደው እንደሆነ ምልክቶችን ማሳየት ጀምሯል።

ጦርነቱ የሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ማኅበረሰቦች የመጀመሪያ ገፈት ቀማሽ ቢሆኑም፣ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ጫናው ግን የተቀረውን አካባቢና ማኅበረሰብ ጭምር መንካቱ አይቀሬ ነው።

አዲስ ወግ የተሰኘው የውይይት መድረክ ባለፈው ሳምንት በተካሄደበት ወቅት በተናጋሪነት የቀረቡት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ፣ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ያለውን ጦርነት የገለጹት ‹‹ዘመናትን በፈጀ የአገረ መንግሥት ግንባታ ታሪካችን ውስጥ የገጠመን ትልቁ ፈተና ነው፤›› ብለው ነበር። 

ይህ ጦርነት በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ ጫና ማሳደር እንደጀመረ የተናገሩት ሚኒስትሩጦርነቱ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች ላይ ደግሞ ከፍተኛ ማኅበራዊ መናጋት እንዳደረሰ ገልጸዋል።

‹‹ባለፈው ዓመት የነበረው የኢኮኖሚ ዕድገት ጥሩ ነበርኢኮኖሚው ወደ ስድስት በመቶ ገደማ አድጓል። ነገር ግን ጦርነቱ ተፅዕኖ አልነበረውም ማለት ሳይሆን፣ የነበረው ተፅዕኖው ከፍተኛ ባለመሆኑና ኢኮኖሚው ላለፉት ዓመታት በገነባው አቅም ጫናውን መቋቋም ስለተቻለ ነው፤›› ያሉት የገንዘብ ሚኒስትሩ፣ አሁን ግን ጫናው ከብዶ እንደመጣ አስረድተዋል።

ዘንድሮ በቅርብ ወራት ብቻ መታየት የጀመረው ጫና እጅግ ፈታኝ እንደሆነ ያስረዱት ሚኒስትሩባለፉት አምስት ወራት ለዕለት ደራሽ የምግብና ዕርዳታ ለማቅረብ ብቻ መንግሥት አሥር ቢሊዮን ብር ወጪ ማድረጉን ተናግረዋል።

‹‹ዘንድሮ ጉዳቱ ከፍተኛ ሆኗልጦርነቱ ትልቅ ተፅዕኖ አምጥቷል፤›› ያሉት ሚኒስትሩ፣ ‹‹ተቋማት ወድመዋል፣ ከሁለት ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ተፈናቅሎ ተረጂ ሆኗል፣ መሰብሰብ የነበረበት ያልተሰበሰበ ገቢ አለበመሆኑም ጉዳቱ ትልቅ ነው፤›› ብለዋል።

ጦርነቱ እያደረሰ ያለውን መጠነ ሰፊ ጫና በአጠቃላይ ማክሮ ኢኮኖሚው ላይ ከፍተኛ መዛባት ሳያደርስ በተወሰነ ደረጃ መቋቋም የተቻለው፣ ላለፉት ዓመታት በተገነባው የኢኮኖሚ አቅም እንደሆነ የገለጹት ሚኒስትር አህመድ ሽዴዘንድሮ ግን ኢኮኖሚው ጉልበቱ እየከዳው መሆኑን አመልክተዋል።

ጦርነቱ በኢኮኖሚው ላይ እያደረሰ ያለውን ጫና አስመልክቶ በሰጡት መጠነኛ ማብራርያም፣ በኤክስፖርት ዘርፉ ላይ ከሚታየው የተሻለና ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ በስተቀር ሌሎቹ የኢኮኖሚ ዘርፎች መቀዛቀዝ ውስጥ እንደገቡ ጠቁመዋል።

‹‹ከሥራ ዕድል ፈጠራ አንፃር ዘንድሮ ከፍተኛ ችግር እንደሚኖር አጠራጣሪ አይደለም፣ ከገቢ አንፃርም የተወሰነ መቀዛቀዝ ይኖራልበመሆኑም ዘንድሮ የኢኮኖሚ ዕድገቱ ከፍተኛ ጫና ውስጥ ገብቷል፤›› ብለዋል።

ጦርነቱ ገና ባለመጠናቀቁ ከፍተኛ ወጪ እየጠየቀ እንደሆነ የተናገሩት ሚኒስትሩ፣ በዚህም ምክንያት መንግሥት የዘንድሮ በጀቱን ለማሸጋሸግ መገደዱን ተናግረዋል። በዚህም መሠረት የካፒታል በጀቱ ላይ ትኩረት ተደርጎ የበጀት ማሸጋሸግ ተግባር መከናወኑን የጠቆሙት ሚኒስትሩ፣ ያልተጀመሩ የካፒታል ፕሮጀክቶች እንዲዘገዩ ተደርጎ ለእነዚህ ፕሮጀክቶች የተመደበው በጀት ተሸጋሽጎ ለህልውና ዘመቻው እንዲውል መወሰኑን ገልጸዋል።

ምክንያቱንም ሲገልጹ፣ ‹‹የህልውና ዘመቻው ገና ባለመጠናቀቁ የፀጥታ ኃይሎችን የማደራጀትና የማብቃት ሥራ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ ነው። በመሆኑም ለዘንዶሮ የተመደበውን በጀት ማሸጋሸግ ግዴታ ሆኗልስለዚህ ያልተጀመሩ ፕሮጀክቶች እንዲዘገዩ ተደርጓል፤›› ብለዋል። 

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2014 በጀት ዓመት ያፀደቀው አጠቃላይ በጀት 561 ቢሊዮን ብር ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 200 ቢሊዮን ብር የሚሆነው ትልቁ ድርሻ ለክልሎች በድጎማ መልክ የሚከፋፈል ነው። ከቀሪው የበጀቱ ክፍል ውስጥ 183.5 ቢሊዮን ብር የተመደበው ለካፒታል ወጪ ሆኖ፣ ይህም 2013 በጀት ዓመት 20 ቢሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው የበጀት ሰነዱ ያመለክታል።

ከተከናወነው የበጀት ማሸጋሸግ ተግባር በተጨማሪም የሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ ተጨማሪ በጀት ለመመደብ በሚያስችለው ረቂቅ አዋጅ ተወያይቶ ተጨማሪ በጀቱ እንዲፀድቅለት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መላኩ ታውቋል።

በገንዘብ ሚኒስቴር የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ 122 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት እንዲመደብ የሚጠይቅ ነው፡፡ ተጨማሪ በጀቱ ለአገር ደኅንነት ማስጠበቂያ፣ ለሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት የሚሆን ወጪን ለመሸፈን፣ በጦርነትና ግጭቶች ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ማቋቋሚያ እንዲሁም ለሌሎች አስፈላጊ የመንግሥት ሥራዎች ማስፈጸሚያ የሚውል እንደሆነ ተገልጿል።

ተጨማሪ በጀቱን ማዘጋጀት ያስፈለገው በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በተካሄደው ጦርነት ምክንያት ተጨማሪ ወጪ በማስፈለጉ፣  ‹‹አሁን ያለው የጦርነት ሁኔታ እያስከተለ ያለውን ወጪ መንግሥት በሚሰበስበው ገቢና የበጀት ሽግሽግ በማድረግ ብቻ የክፍያ ወጪዎችን ለመሸፈን አዳጋች ሆኖ በመገኘቱ ነው፤›› በማለት የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ለተጠየቀው 122 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት የሀብት ምንጭ ተብለው ከተለዩት መካከል አንዱ የዓለም ባንክ ለመልሶ ማቋቋሚያ የሚያበድረው 400 ሚሊዮን ዶላር አንዱ ሲሆንበተመሳሳይ ከሌሎች ዓለም አቀፍ ምንጮች ለሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት 350 ሚሊዮን ዶላር እንደሚገኝ ታሳቢ ያደረገ ነው። 

መንግሥት ድጎማ ከሚያደርግባቸው አቅርቦቶች ላይ የተወሰነ ድጎማ በማንሳት የሚገኝ ገቢ፣ ሌላው ለተጨማሪ በጀቱ የገቢ ምንጭ ሆኖ መለየቱን ታውቋል።

መልሶ ማቋቋምና ፈተናዎቹ 

የአማራ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ በጦርነቱ ምክንያት በክልሉ የተፈጠረውን ውድመትና ጉዳት ለመገንባትና መልሶ ለማገገም፣ 30 ዓመታትን ሊወስድ እንደሚችል ባለፈው ወር አስታውቆ ነበር። 

በአማራ ክልል የተደረጉ የዳሰሳ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ እስካሁን ድረስ ብቻ ጦርነቱ በአማራ ክልል ሥር በሚገኙ አካባቢዎች በአጠቃላይ 279.5 ቢሊዮን ብር የሚገመት የንብረት ውድመት አድርሷል።

ይህንንም ተከትሎ የአማራ ክልል ከደረሰበት ጉዳት ለማገገም የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያሻውና የደረሰውን ጉዳት የተመለከተ ጥናት አካሂዶ፣ የድጋፍ ጥያቄ ለፌዴራል መንግሥት እንደሚያቀርብ የአማራ ክልላዊ መንግሥት የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ለሪፖርተር ገልጸዋል።

ክልሉ ቀደም ሲል በጦርነቱ ለቆሰሉና ለተጎዱ የጤና አገልግሎት ለማቅረብ ያወጣው ሁለት ቢሊዮን ብር ወጪ ተመላሽ እንዲደረግለት ለፌዴራል መንግሥት ጥያቄ አቅርቦ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ግዛቸውአሁን ግን አንድን ዘርፍ ብቻ የተመለከተ የወጪ ካሳ ጥያቄ እንደማያቀርብና አጠቃላይ ጉዳቱ ተጠንቶ ጥያቄ እንደሚቀርብ ገልጸዋል።

‹‹የፌዴራል መንግሥት ባለሥልጣናት በጦር ሜዳ አብረውን ነበሩ፣ የደረሰውን ውድመት ተመልክተዋል፡፡ ስለሆነም ምን ማድረግ እንዳለባቸው ያውቃሉ፤›› ያሉት አቶ ግዛቸው፣ ክልሉ ጥናቱ ከተጠናቀቀ በኋላ የበጀት ድጋፍ ጥያቄውን እንደሚያቀርብ ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት በክልሉ ስለደረሰው ጉዳት መጠን ጥናት የሚያደርግ 11 ዘርፎችንና ምሁራንን ያካተተ ቡድን የተቋቋመ ሲሆንቡድኑ በስድስት በተመረጡ ዘርፎች ላይ ጥናት በማካሄድ ጉዳት የደረሰባቸውን ተቋማትና መሠረተ ልማቶችን በመለየት መልሶ ለመገንባት የሚያስፈልገውን የሀብት መጠን በተመለከተ ሐሳብ እንደሚያቀርብ አስረድተዋል፡፡

ጥናቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ክልሉ ያሉትን ሀብቶችና ጉድለቶች በመገምገም አስፈላጊውን ሀብት እንደሚመደብ፣ የተቀረውን ሸክም ደግሞ የፌዴራል መንግሥት፣ ክልሎችና ከተሞች እንዲጋሩ ለማድረግ መታቀዱን ገልጸዋል። በተጨማሪም ከውጭ መንግሥታትና የዕርዳታ ድርጅቶች ድጋፍ ለመጠየቅ ማቀዱን አቶ ግዛቸው ተናግረዋል። 

ጦርነቱ በስፋት የተካሄደው በአማራ ክልል እንደ መሆኑ መጠን ከፍተኛ የንብረት ውድመትና ማኅበራዊ ቀውስ የደረሰውም በዚሁ ክልል እንደሚሆን አጠያያቂ አይደለም። መጠኑ ይለያይ እንጂ ተመሳሳይ ውድመትና ማኅበራዊ ቀውስ በትግራይና በአፋር ክልሎችም ደርሷል። 

ጦርነቱ በፌደራል በክልል መንግሥታት ጥምረት በአንድ በኩልና በትግራይ ክልል በሚንቀሳቀሰው ሕወሓት መካከል በመሆኑ፣ የመልሶ ግንባታና የመልሶ ማቋቋም ተግባርና ሕጋዊ ኃላፊነት ማን ላይ ሊወድቅ ይችላል የሚለው በአሁኑ ወቅት ነጥሮ የወጣ ጥያቄ ባይሆንም፣ አከራካሪና የሕግ ጥያቄ የሚያስነሳ ጉዳይ እንደሚሆን የሕግ ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 94 ድንጋጌው የፌዴራሉ መንግሥትና ክልሎች በሕገ መንግሥቱ የተሰጣቸውን ኃላፊነቶችና ተግባሮች ለማከናወን የሚያስፈልጋቸውን ወጪ በየበኩላቸው የመሸፈን ግዴታ እንዳለባቸው በግልጽ ይደነግጋል። ይሁን እንጂ ማናቸውም ክልል በውክልና ለሚፈጽመው ተግባር የሚያስፈልገው ወጪ ሌላ ስምምነት ከሌለ በቀር፣ ውክልናውን በሰጠው ወገን እንደሚሸፈን በዚሁ አንቀጽ ሥር ተደንግጓል።

በዚሁ አንቀጽ ሥር የተቀመጠው ሌላውንጋጌ ደግሞ የፌደራሉ መንግሥት ለክልሎች የተመጣጠነ ዕድገት እንቅፋት ካልሆነ በስተቀር ለአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ፣ ለመልሶ መቋቋምና ለልማት ማስፋፊያ ለክልሎች ብድርም ሆነ ዕርዳታ ሊሰጥ እንደሚችል ይደነግጋል። 

በመሆኑም የፌደራል መንግሥት ለመልሶ ማቋቋምለመልሶ ግንባታ ኃላፊነት እንዳለበትሙን ነው። ነገር ግን ለመልሶ ማቋቋምና መልሶ ግንባታ የፈዴራል መንግሥት የድርሻ መጠን ምን ያህል ሊሆን ይችላል የሚለው አከራካሪ ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎቹ ይገልጻሉ።

በተመሳሳይ ክልሎች የራሳቸውን የጉዳት መጠን ጥናት በማካሄድ የፈዴራል መንግሥት ማድረግ ያለበትን የድጋፍ ድርሻ ሊወስኑ ይችላሉ? ወይስ የመልሶ ማቋቋምና ግንባታ ሥራው በፌዴራል መንግሥት የመሪነት ሚና የሚከናወን ይሆናል? የሚለውን የሚመልስ ሥልት ነድፎ መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግ ባለሙያዎች ይመክራሉ።

በተጫሪም የመልሶ ግንባታና ማቋቋም ሥራው በዘፈቀደ መከናወን እንደሌለበት፣ እንዲሁም ይህንን ኃላፊነትና ተጠያቂነት የሚወስድ ተቋማዊ አደረጃጀት እንደሚያስፈልግ ይመክራሉ።

በአዲስ ወግ ውይይት ላይ ከተሳተፉ ባለሙያዎች የተለያዩ ጥያቄዎችና ምክረ ሐሳቦች የተነሱ ሲሆን፣ የመልሶ ማቋቋምና ግንባት ሥራ ውስብስብ በመሆኑ ይህንን ተግባር እንዴት መፈጸም እንደሚቻል የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በመቃኘት ግንዛቤ መውሰድ እንዳለበት ገልጸዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የተለመደው ስኬታማ ተሞክሮ የመልሶ ግንባታና ማቋቋም ተግባርን ከዘላቂ ልማት ጋር አቀናጅቶ መፈጸም እንደሆነ የገለጹ አንድ ባለሙያ፣ ይህንን በሚያረጋግጥ መንገድ ለመፈጸም ከሚረዱት አካሄዶች መካከል ደግሞ ሁለት ዓበይት ጉዳዮች ትኩረት እንደሚፈልጉ በመጠቆም ምክረ ሐሳባቸውን አክለዋል።

‹‹እነዚህ ሁለት ጉዳዮች ከባለቤትነት ጋር የሚገናኙ ናቸው። አንደኛው የባለቤትነት ጉዳይ የመልሶ ግንባታ ፕሮጀክት ቀረፃ በሚካሄድበት ወቅት መመለስ እንዳለበት፣ ይኸውም መልሶ ግንባታው የሚመለከተው የአካባቢ ማኅበረሰብና የመንግሥት መዋቅር በፕሮጀክት ቀረፃ ወቅት ተሳታፊ እንዲሆን በማድረግ የባለቤትነት ድርሻውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ሌላኛው የባለቤትነት ጉዳይ የአካባቢውን ሀብት በግብዓትነት መጠቀምና በዚህ ሒደትም ባለቤትነትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ይህንን ማድረግ የመልሶ ግንባታ ሒደቱ ከዘላቂ ልማት ጋር እንዲቀናጅ የሚያደርግ፣ ቀጣይ አቅምን ለመገንባት የሚረዳ በመሆኑ ድምር ውጤቱ ዘላቂ ልማትን ያረጋግጣል፤›› ሲሉ መክረዋል። 

አቶ ግርማ ከበደ የተባሉ ሌላ ባለሙያ በበኩላቸው፣ የመልሶ ግንባታና ማቋቋም ተግባር ከዘላቂ ልማት ጋር ተቀናጅቶ መተግበር አለበት፡፡ ለዚህም ሲባል የትግበራ ፕሮጀክቱን የሚመራ ተቋማዊ አደረጃጀት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡ 

ምክንያታቸውን ሲገልጹም፣ ‹‹20 ዓመታት ሙሉ ዜጎቻችንን በሴፊቲኔት ፕሮግራም ሥር አቆይተን የማኅበረሰቡን ችግር ዛሬም መፍታት አልቻልንም። ከዚህ ትምህርት መውሰድ ያስፈልጋል፡፡ የውጭ እጅ ጥምዘዛው የሚመጣውም ከዚሁ መሆኑን መረዳትና ዕይታችንን ማስተካከል ይኖርብናል፤›› ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት የአማራ ክልል የደረሰውን ጉዳትና ለመልሶ ማቋቋም የሚያስፈልገውን ወጪ የተመለከተ ጥናት እያካሄደ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆንየፌደራል መንግሥት በበኩሉ ሁሉንም አካባቢዎችካተተ አጠቃላይ ጥናት እንደሚያከናውን አስታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪም በፌዴራል መንግሥት ደረጃ የመልሶ ማቋቋም ጽሕፈት ቤት የተቋቋመ ሲሆን፣ በጽሕፈት ቤቱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው የሚያገለግሉ ተቋማትም ተሰይመመዋል። 

እነዚህም ተቋማት የትምህርት ሚኒስቴር፣ የጤና ሚኒስቴር፣ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር፣ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ናቸው፡፡

በአዲስ ወግ የውይይት መድረክ ላይ በተናጋሪነት የተገኙት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ በሰጡት አስተያየት፣  የመልሶ ማቋቋሙን ሥራ በባለቤትነት የሚመራው የፌዴራል መንግሥት እንደሆነ በግልጽ አስረድተዋል።

የመልሶ መማቋቋም ሥራው ብዙ ሀብት የሚጠይቅ እንደሆነና ይህንን ሥራ ለማከናወንም ቢያንስ ሦስት ዓመት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

የመልሶ ማቋቋምና መልሶ ግንባታ ሥራውን ለማከናወን በመጀመሪያ ሁሉን አቀፍ የጉዳት መጠን ጥናት ማካሄድን የሚጠይቅ በመሆኑ፣ መንግሥት ይህንን ጥናት የሚያካሂድ ኮሚቴ እንዳቋቋመም ገልጸዋል።

በቀዳሚነት ትኩረት የሚሻው ጉዳይ በጦርነቱ ለተጎዱ አካባቢዎች ማኅበረሰቦች ዕለታዊ ዕርዳታ ማድረስን ጨምሮ ሁሉን አቀፍ የመልሶ ማገገሚያ ሥራ ማከናወን እንደሆነ፣ በማስከተልም መደበኛ አገልግሎቶችን መልሶ የማደራጀትና መሠረተ ልማቶችን የመጠገን ተግባር እንደሚሆን ገልጸዋል።

‹‹የቅንጅት ሥራ በጣም አስፈላጊ ነው። ክልሎች የሚወስዱት ድርሻ ይኖራልማኅበረሰቡም የሚኖረው ድርሻ አለ። ነገር ግን ዋናው ባለቤትና ሀብት የመመደብ ኃላፊነት የፌዴራል መንግሥት ነው፤›› ሲሉ አቶ አህመድ አስረድተዋል። 

ከሰሜኑ ጦርነት በተጨማሪ በሌሎች አካባቢዎች በነበሩ ተዛማጅ ግጭቶች የተፈናቀሉ የማኅበረሰብ ክፍሎችም፣ በዚህ የመልሶ ማቋቋም ሥራ ውስጥ እንደሚካተቱ ገልጸዋል።

‹‹ይህ የመልሶ ማቋቋም ሥራ በደቡብ በቤኒሻንጉል ጉምዝና በኦሮሚያ አካባቢዎች የተወሰኑ ቦታዎችን የሚያካትት ነው የሚሆነው። ሥራው በአንድ ዓመት ሊፈጸም የሚችል አይደለም፡፡ ቢያንስ እስከ ሦስት ዓመት የሚጠይቅ ነው። ምክንያቱም በማኅበራዊ መሠረት ላይ ከፍተኛ መናጋት ነው የፈጠረው። በአገረ መንግሥት ግንባታ ታሪካችን የገጠመን ትልቁ ፈተና ነው፤›› ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ትኩስ ጽሑፎች

ተዛማጅ ጽሑፎች

- Advertisement -
- Advertisement -