አንድ የጠገበ አህያ ቀንዳም ቀንዳ እንስሳትን እያየ፡- ‹‹ወይኔ! እኔ ብቻ ቀንድ ሳላበቅል ልቀር ነው?›› አለና ቀንድ ለማስተከል ወደ ሌላ ቦታ ሲሮጥ፣ እንደ አጋጣሚ አንድ ገበሬ ምርቱን አምርቶ መጫኛ አጥቶ ሲጨነቅ ያ አህያ እየሮጠ ደረሰለት፡፡ ስለዚህ ይህን የጠገበ አህያ አምጡና እንጫነው ብሎ ጆሮውን ሲጎትተው፣ ያ ጥጋበኛ አህያ አልጫንም ብሎ ለጥ ብሎ ተኛ፡፡ በዚህ ምክንያት ሰውዬው ጆሮ ጆሮውን እያለ ሲደበድበው ከዱላው ብዛት የተነሳ የአህያው ጆሮ ተቆረጠ፡፡ አህያውም እያዘነ ወደ ቦታው ሲመለስ፣ ‹‹ቀንድ አበቅላለሁ ብዬ ሄጄ ጆሮዬን አጥቼ መጣሁ›› አለ ይባላል፡፡
– ዜና ማርቆስ እንዳለው ‹‹ቅኔያዊ ጨዋታ›› (2012)