Saturday, December 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅለዳያስፖራው በተለያዩ ዝግጅቶች አቀባበል እየተደረገ ነው

ለዳያስፖራው በተለያዩ ዝግጅቶች አቀባበል እየተደረገ ነው

ቀን:

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጥሪን ተቀብለው ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አቀባበል በተለያዩ ፕሮግራሞች ታጅቦ እየተከናወነ ነው፡፡ ባገባደድነው ሳምንት ውስጥ ከተከናወኑ የዳያስፖራ አቀባበል ፕሮግራሞችም በእንጦጦ ፓርክ፣ በወዳጅነት አደባባይና በአዲስ የዳያስፖራ ማዕከል የተከናወኑት ይገኙበታል፡፡ ወዳጅነት ፓርክ እና እንጦጦ ፓርክ የገበያ ማዕከላትን ማስጎብኘትና በይፋ ሥራ ማስጀመር፣ ከአዲስ የዳያስፖራ ማዕከል እስከ ወዳጅነት አደባባይ ለዳያስፖራዎች የተደረገው አቀባበልም የሥነ ሥርዓቱ አካል ነበር፡፡ የአዲስ ዳያስፖራ ማዕከል በይፋ ሥራ የጀመረውም በዚሁ ወቅት ነው፡፡ የበዓል ቀናትን ጨምሮ አገልግሎት የሚሰጠው ማዕከል ለዳያስፖራው የኢንቨስትመንት፣ የኢሚግሬሽንና ሌሎችም አገልግሎቶችን በአንድ መስኮት ለመስጠት የሚያስችል ነው፡፡ በአቀባበሉ ላይ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተገኝተዋል፡፡

ለዳያስፖራው በተለያዩ ዝግጅቶች አቀባበል እየተደረገ ነው

ለዳያስፖራው በተለያዩ ዝግጅቶች አቀባበል እየተደረገ ነው

  • ፎቶ መስፍን ሰለሞን
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...